ኢትዮጵያ በአለማችን መረጋጋት ከሌለባቸው አስር ሃገራት መካከል አንዷ ሆና ተፈረጀች
(ጥቅምት 11 ፥ 2009)
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተግባራዊ አድርጋ የምትገኘው ኢትዮጵያ በአለማችን መረጋጋት ከሌለባቸው አስር ሃገራት መካከል አንዷ ሆና መፈረጇን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ ማድረጉን ኒውስዊክ መፅሄት ዘገበ።
በሃገሪቱ ያለው የአፈናና ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ኢትዮጵያን በአለማችን ካሉ ያልተረጋጉ አስር ሃገራት መካከል አንዷ እንድትሆን ማድረጉን አሜሪካን ኢንተርፕራይስ ኢንስቲቲዩት የተሰኘው ተቋም በሪፖርቱ አስፍሯል።
ኢትዮጵያ ያልተረጋጉ ተብለው ከተፈረጁት አስር ሃገራት መካከል በአራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ ሃገሪቱ መረጋጋት የሌለባቸው ተብለው ከተቀመጡ ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗንም ኒውስ ዊክ መጽሄት የተቋሙን መረጃ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
ማልዶቭስ፣ ሞሪታኒያ፣ አልጀሪያ፣ ኢትይዕጵያ፣ ናይጀሪያ፣ ቱርክ፣ ሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስና ቻይና አስሩ አለመረጋጋት የሌለባቸው የአለማችን ሃገራት መሆንቸውን መጽሄቱ አስነብቧል።
አስሩ ሃገራት በዜጎቻቸው ላይ የተለያዩ አፈናዎችን የሚያካሄዱ መሆናቸውን ያመለከተው የጥናቱ አቅራቢ ተቋም በተለየ መልኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የፖለቲካ ስርዓት የሚታይበት መሆኑን አመልክቷል።
በኢትዮጵያ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ የፖለቲካ ውጥረቶችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ሃገሪቱ ወደ ባሰ አለመረጋጋት ሊወስዳት ይችላሉ ተብለው ከተቀመጡ አበይት ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ሆነዋል።
በቅርቡ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራትና አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በሃገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊባባስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛል።
የአዋጁ መውጣትን ምክንያት በማድረግ ወደ 2ሺ አካባቢ የሚጠጉ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን መንግስት መግልጹ ይታወሳል።
ይሁንና የፓርቲ አመራሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በአግባቡ እንደማይታወቅና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

No comments:
Post a Comment