Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, October 31, 2016

የፍራንክፈርት ከተማና የአካባቢያዋ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ወደ 15 ሺ ይሮ የተጠጋ እርዳታ አሰባሰቡ !



የፍራንክፈርት ከተማና የአካባቢያዋ ኗሪ ኢትዮጵያውያን ወደ 15 ሺ ኤዉሮ የተጠጋ እርዳታ አሰባሰቡ ! በፍራንክፈርትና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፈዉ ቅዳሜ ኦክቶበር 29 ቀን ባደረጉት ስብሰባ በሕዝባዊ እምቢተኝነቱ አመጽ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የቤተሰብ አባላት ወደ 15 ሺ ኤዉሮ የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻላቸዉን አንድ የእርዳታ አሰባሰቢው ግብረ ሃይል ቃል አቀባይ አስታውቑል። በጀርመን የትብብርና ውይይት መድረክ ማዕከልነት በፍራንክፈርት ከተማና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ አሰባሳቢ ልዩ ግብረ ሃይል በመፍጠር ባጭር ጊዜ ውስጥ በተደረገ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ርብርቦሽ በዚህ ዜና ርዕስ ላይ የተጠቀሰዉ የገንዘብ መጠን ሊገኝ ችሏል።

ይህም ገቢ ሊገኝ የቻለዉ፣ በዋናነት ከመግቢያ ቲኬት፣ ከቶምቦላ፣ከጨረታ ዉድድር እንደሆነ በተጨማሪ ተገልጿል። በተለይ በጨረታዉ ዉድድር፣ የአንዳርጋቸዉ ፅጌ፣ የመምሕር በቀለ ገርባ እና የኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ ፎቶዎች መቅረብ መቻላቸዉ የብዙዎቹን የስብሰባዉን ታዳሚዎች ቀልብ የሳበ ሲሆን፣ ከፍተኛ ውድድር የታየበትና የማይናቅ የገቢ መጠንምአስገኝቷል። በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመዉ ግፍና ሰቆቃ አንድ ሊያደርገን ካልቻለ ምንጊዜም አንድ ያለ መሆን አባዜ ሊጫወትብን ይችላልና ይህን የፈተና ጊዜ አንድ ሆነን ማሳለፍና ችግሩንም ባጋራ መቑቑም እንዳለብን በመድረኩ በግልፅ ተንፀባርቑል። በተለይም በአሁኑ ሰዓት በሃገሪቱ በሁሉም ማዕዘናት ለነፃነቱና ለመብቱ ደሙን እያፈሰሰ ከሚገኘዉ ወገናችን ጎን መቆም ለነገ የማይባል የዛሬ ተግባራችን መሆን እንደሚገባዉ በስብሰባዉ ታዳሚዎች በትኩረት ተወስቷል። ደሙ በየመንገዱ እየተዘራ ሕይወቱ ለሚያልፈዉ ቀሪ ቤተሰብ የአቅምን እርዳታ መለገስ ሰብዓዊነት እንጂ ከፖለቲካ ጋር የሚያቆራኘዉ አመክንዮም ሰለሌለ፣ ለወደፊቱም ይህ ዓይነቱ ተግባር በተከታታይ መቀጠል እንዳለበት ተሰምሮበታል። ትግል ሳይቸግረዉ፣ ድል ያልሰመረለት ይህ የተካደ ትውልድ ሕልሙና ራዕዩ እዉን እስኪሆን ድረስ ሁሉም በዚህ ታሪካዊና የፈተና ጊዜ ዚግነታዊ አሻራዉን ጥሎ እንዲያልፍ እናት ሀገሩ ጥሪ አያደረገችለት መሆኑን ሊገነዘበዉ እንደሚገባ፣ የስብሰባዉ ታዳሚዎች በቃላት ሳይሆን በዓይን ተናበዋል። በፕሮግራሙ ላይ አጫጭር ግጥሞችም ቀርበዉ በንባብ ተደምጠዋል። እንደ ጴጥሮስ ያችን ሰዓት የመሳሰሉ ምንጊዜም ሀገራዊ መልዕክታቸዉን ጊዜ ያማይሽረዉ ቲያትር ለስብሰባዉ ከጊዜ አንፃር ተቀነባብሮ አሰልቺ ባልሆነና ትምሕርት ሊሰጥ በሚችል መልኩ ቀርቦም ታይቷል። በተለይ በፕሮገራሙ መጨረሻ ላይ መድረኩ ለግልጽ ውይይት ክፍት ሆኖ፣ መነቃቀፍ ከሌለ መተማመን ስለማይኖር፣ እየተነጋገርን በመተባበርና በመተማመን ስንሞት እሬሳችን እየተላከ የምንቀበርባት ሀገር ሳትሆን በሕይወታችንም በቁም የምንኖርባት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር የየድርሻችንን አገራዊ ዕዳ መክፈል እንደሚኖርብንና ማንነቱን ለማስከበር ደሙን እየገበረ ከሚገኘዉ ወገናችን ጎን ለመቆም የዛሬ እንጂ የነገ ቀጠሮ ያማያስፈልገዉ የቤት ሥራችን መሆን እንዳለበት በተማመን ተለያይቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials