ደራሲ ኃይሉ ፀጋዬ በEBC ቀጥታ ፕሮግራም ላይ በአርሂቡ ላይ ቀርቦ ስለ ወቅታዊ ፓለቲካ ተጠይቆ በድፍረት መንግስትን ተች ቶዋል !!!
<<አሁን ለተፈጠሩት ችግሮ ሁሉ ትልቁን ኃላፊነት መውሰድ ያለበት መንግስት ነው :: እኔ በናዝሬት (አዳማ) ነው ተወልጄ ያደኩት የኦሮሞ ሕዝብ ምን ስጠይቅ እንደነበር በደንብ ተከታትያለው ፣ ህገመንግስታዊ ጥያቄ ነው የጠየቀው :: በአማራው ክልል የወልቃይት የህዝብ የጠየቀውም ህገመንግስታዊ ጥያቄ ነው :: መንግስት በሕዝብ ተመረትኩ እያለ ለሚንሱት ጥያቄዎች ሕሉ ጥይትን መፍትሄ ካደረገ እንዴት ይሆናል :: ሕዝቡን ማዳመጥ አለበት :: በጉልበት በመተኮስ የትም አይደረስም :: ዓለም ላይ ትላልቅ ቀውሶች ችግሮችን በግዜ መፍታት ካለመቻል የመጡ ናቸው ::
እውነት እንነጋገር ከተባል እዚች ሀገር በጣም ብዙ ልያሳምፁ የሚችሉ ችግሮች አሉ ፣ ሕዝብ በጣም ለብዙ ዓመት ታግሶ ታግሶ የሚሰማው ስላጣ ነው ወደዚህ አይነት አደገኛ ሁኔታ የገባው :: ሙስናው ፣ መልካም አስተዳደሩ በጣም በጣም የከፋ ደረጃ ደርሶዋል :: የህዝብ ምሬት እውነትነት አለው :: ሕዝብ ለትንሽ ነገር አያምፅም ከአቅሙ በላይ ሲሆን እንጅ ::
ሌላው ሁሉ ቢቀር በየሚድያው የሚወራው አንድ አይነት ድምፅ ነው ሕዝብ ሬታዉን ችግሩን የሚተነፍስበት ሚድያ ያስፈልገዋል :: ሀገር በደዚህ አይነት ሁኔታ አትቀትልም :: አሁንም ችግሩን በትዘላቂነት ለመፍታት ትናንች ለውጦችን ማድረግ ሳይሆን የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ ተገንዝቦ በአግባቡ መመለስ ያስፈልጋል :: ይህን የማድረግ ትልቁ ኃላፊነት ደግሞ የመንግስት ነው :: ትልቅ ኃላፊነት አለበት ::>>
No comments:
Post a Comment