Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 8, 2016

በ2009 የትምህርት ዓመት የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች: ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን !!

የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች: ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን !!ከዶ/ር ታደሰ ብሩ !!
በ2009 የትምህርት ዓመት በመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ የሕዝባዊ አሻጥር ዓይነቶች
1. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ስለሰብዓዊ መብቶች ሉዓላዊነት እና ስለ ሰለሰው ልጆች ክብር አስተምሩ፤ በተግባርም አሳዩ። የትምህርቱ መርሀግብር (curriculum) አይፈቅድልኝም የሚለውን ሰበብ አስወግዱ። ራሱ “ትውልድን ገዳይ“ የሆነው ካርኩለም ላይ ነው አሻጥር መሥራት ያለባችሁ።
2. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተማሪዎች እውነትን ራሳቸው እንዲሹ፣ ብዙ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እንዲመራመሩ፣ እንዲሞግቱ አበረቷቷቸው። የትምህርት ቤቱ ህግ ባይፈቅድም ተማሪዎች የተሰማቸውን በነፃነት እንዲናገሩ፣ እንዲጽፉ፣ እንዲዘምሩ ፍቀዱላቸው።
3. ተማሪዎች “እኔ ማነኝ?” “ማንን መምሰል እፈልጋለሁ?” “ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብለው እንዲጠይቁና ራሳቸው ፈልገው እንዲያገኙ፤ እያንዳንዳቸው Potentially ዓለምን መቀየር የሚችሉ ሰዎች መሆናቸውን እንዲረዱ አበረቷቷቸው።
4. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተማሪዎች ከግላቸው አልፈው ስለማኅበረሰብ እንዲያስቡ “ይህች አገር የማናት?” “ማን ጠግቦ፤ ማነው የሚራብባት?” “ማን ዘፍኖ ማነው የሚያለቅስባት?” “መጪው 20, 30, 50 ምን ሆኖ ማየት እንፈልጋለን?” “የምንፈልገው እንዲመጣ አሁን ምን ማድረግ እንችላለን?” ብለው እንዲጠይቁ አበረቷቷቸው።
5. በትምህርት ወቅት የምትሰጧቸው ምሳሌዎች ሁሉ አገራዊና ወቅታዊ ይሁኑ። ለምሳሌ በሂሳብ ክፍለ ጊዜ የ EBC “ልማታዊ ዜና” ውሸትነት በቀላል ሂሳብ ማረጋገጥ በመልመጃነት ይቅረብ (ለዚህ የሚሆን ማስረጃ በገፍ ነው ያለው)።
6. ምሳሌዎቻችሁና ቀልዶቻችሁ የህወሓት አገዛዝ ብልሹነት ቢቻል በቀጥታ ካልሆነም በተዘዋዋሪ የሚገልጹ እንዲሆኑ አድርጉ።
7. በፓሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በወታደር፣ በደህነት (ጆሮ ጠቢዎች)፣ በምርጫ ቦርድ፣ በእምባጠባቂ፣ በ EBC፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ በ EFFORT ... ወዘተ ቀልዱ። በእነዚህ ተቋማት ላይ እንዲቀለድ አበረታቱ።
8. በዘር፣ በፆታ፣ በሀይማኖት መተራረብና መከፋፈል ጊዜ ያለፈበት አስተሳሰብ እንደሆነ አስተምሩ። ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ የሚመሩት የኢህአዴግ ካድሬዎች መሆናቸው አስረዱ።
9. ኢህአዴግን ከወቅቱ ጋር መቀየር ባለመቻሉ ከጠፋው ዳይኖሰር ጋር አመሳስሉት፤ በ 2009 የትምህርት ዘመን ዳይኖሰሩ ይጠፋል ብላችሁ አስተምሩ።
10. የትምህርት ቤቱ አፋኝ ደንቦችን በእናንተ ክፍል ውስጥ ተግባራዊ አይሁኑ። በአገሪቱ ያሉ አፋኝ ህጎችም በእናንተ ክፍል ውስጥ ይጣሱ።
11. ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለተሻሻለ የትምህርት ሥርዓት፣ ለመምህራን መብት፤ ለተሻለ ክፍያና የደረጃ እድገት እድሎች ታገሉ። በወያኔ የተጠለፈውን የመምህራን ማኅበርን አውግዙ፤ የራሳችሁን ነፃ ክበባት ፍጠሩ።
12. ከለውጥ ፈላጊ ተማሪዎች ጋር አብሩ፤ በሃሳብ፣ በቁሳቁስ፣ በተግባር እርዷቸው። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ፀረ ህወሓት/ኢህአዴግ ምስጢራዊ ድርጅት አቋቁሙ።
13. ተማሪዎች የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የነፃነት፤ የማኅበራዊ ወይም የፓለቲካ ጥያቄዎች ሲያነሱ ከጎናቸው ቁሙ።
14. የኅበረተሰቡን የነፃነት፣ የፍትና የእኩልነት ጥያቄዎች በመደገፍ ታገሉ፤ ለትግሉ የሙያ ድጋፍ ስጡ።
15. የአቃጣሪ ተማሪዎችና የካድሬ መምህራንን የሞባይልና የቤት ስልኮችን ለምስጥራዊ ድርጅታችሁ ስጡ።
16. በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ፌስቡክ፣ ቱተር፣ ኢንስታግራም፣ ዩቱብ) የአቃጣሪ ተማሪዎች፣ የካድሬ አስተማሪዎችና ሠራተኞች ስብዕና የሚያንቋንሽሹ ጽሁፎችንና ምስሎችን አሰራጩ።
17. የነፃነት ታጋዮችን የሚያሲዙ ካድሬ መምህራንና ተማሪዎችን ተግባር ከትምህርት ቤታቸው አልፎ የሰፈራቸው ሰዎች እንዲያውቁ አድርጉ። እንዴት ክፉ ሰዎች እንደሆኑ ወንድሞቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ ልጆቻቸው፣ ሚስቶቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸው እንዲያውቁ አድርጉ።
18. የተለያዩ የተቃውሞ መግለጫ መንገዶችን በማስተዋወቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ግምባር ቀንበር ሁኑ።
19. "ቀበሌና ፓሊስ ትምህርት ቤታችንን አይርገጥ” በሉ።
20. የትምህርት ቤቱን የተለያዩ ክበባት ተማሪዎችን ለትግል ማዘጋጃነት አውሉ። ሚኒ ሚዲያ፣ ድራማ፣ ስነጽሁፍ፣ ቅርፃ ቅርጽ፣ ስፓርት፣ ሙዚቃ፣ ... የሂሳብና የፊዚክስ ክበባት ሁሉ ሳይቀሩ ተቃውሞ ማሳያዎችና አሻጥር መሥሪዎች ይሁኑ።
21. ተማሪዎች በግጥም፣ በልበወለድ ታሪኮች፣ በድራማዎች፣ በዘፈኖች፣ በስዕሎች ... የተቃዉሞ መልክቶቻችሁን እንዲያስተላልፉ አስተባብሩ፤ እናንተም ተሳተፉ።
22. የስፓርት ሜዳዎች የትግል ሜዳዎች ይሁኑ። የስፓርት ሜዳ መዝሙሮች ፀረ-ህወሓት/ኢህአዴግ የትግል መዝሙሮች ይሁኑ። የስፓርት ክበባት የአሻጥር ጥናትና ሙከራ ማዕከላት ይደረጉ።
23. የነፃነት ታጋዮች የሚያትሟቸው ወረቀቾችን በትምህርት ቤት ውስጥ አሰራጩ።
24. የነፃነት ታጋዮችን ስም አወድሱ። በእስር ላይ የሚገኙ፤ በትግል ላይ የሚገኙ ብሄራዊ ጀግኖችን አወድሱ። በአንፃሩ፣ የኢህአዲግ ሹማምንትን አራክሱ።
25. በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ ወረቀት፣ ኮምፒውተር፣ ማባዣ እና የመሳለሉትን ውሰዱና የነፃነት ትግል መልዕክት ማባዣ አድርጓቸው።
26. የኢሳትና የ OMN ቴሌቪዥኖች ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን ተከታተሉ፤ በየትምህርታችሁ መሀል የኢሳትና OMN ዜናዎች በማንሳት የሰማችሁ ላልሰሙት አዳርሱ።
27. ስለ እውነትና ውሸት ስትናገሩ ምሳሌዎቻችሁ EBC እና ኢሳት ይሁኑ። ውሸት እና EBC አቻ ቃላት ይሁኑ። የውሸት ማምረቻዎች በተማሪዎች ተለይተው እንዲታወቁ አድርጉ: የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ የጠቅላይ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶች፣ EBC፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ የክልል መንግሥታት ቢሮዎች ...
28. ፓሊሶች ሰው ሲደበድቡ፣ ሲያንገላቱ፣ የድሆች ቤቶች ሲፈርሱ፣ ፍትህ ሲጓደል አይታችሁ ዝም አትበሉ፤ ተማሪዎቻችሁን አስተባብራችሁ ጩኹ።
29. ማኅበረሰቡ በሚያደርገው ተቃውሞ - ሰልፍ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የግዢ ማዕቀብ ... ወዘተ. - በንቃት ተሳተፉ።
30. ተቃውሞዎች ሲበስሉ ከምን በላይ ነፃነት ነውና ትምህርት በማቆም አምባገነኑን ሥርዓት ለማንበርከበብና የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ለማምጣት ግንባር ቀደም ሁኑ።
31. 2009 የትምህርት ዓመት የውጤታማ ፀረ-ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል ዓመት እንዲሁን ትጉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials