Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 13, 2016

ታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል



በታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል
ከትናንት ጀምሮ በታችና ምዕራብ አርማጭሆ የተለያዩ አካባቢዎች የዐማራውን መሣሪያ መቀማት በሚል የወያኔ ጦር በዐማራው ገበሬ ላይ ይፋ ጦርነት ገጥሟል፡፡ በታች አርማጭሆ ዶጋው አካባቢና በምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ከ50 በላይ የወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡
አበራ ጎባው እና ደጀኔ ማሩ የተባሉ አርበኞችን ቤት በድንገት በመክበብ ለመግደል ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በአካባቢው ተሰልፎ የነበረው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ መውደሙን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አንድ አርበኛ ከዶጋው አካባቢ ጉዳዩን አስመልክተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የዛሬው ከበድ ያለ ጦርነት ነበር፤ 8፡00 አካባቢ መጥተው የደጀኔ ማሩን ቤት ከበው ለማፈን ባደረጉት ሙከራ የወያኔ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ አመድ ሆነዋል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሞቱ የጠላት ወታደሮችን በተመለከተ ደግሞ ‹‹ኧረ የሚሞተውን ወታደር በተመለከተማ ስንቱን ቆጥረነው! በየጫካው አይደል ተፈንድሶ ተፈንድሶ የምታገኘው! እንዴው ገምት ካልከኝ አሳንሼ ቁጥሩን ከ50 ይበልጣል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በጎንደርና በጎጃም የዐማራ አካባቢዎች በተወሰነ መልኩ ሰላማዊ የሆነ ቢመስልም ወያኔ የገበሬውን መሣሪያ እቀማለሁ በማለቱ ምክንያት እንደገና ሰላሙ ደፍርሷል፡፡ በሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ፣ የጠገዴና የወልቃይት አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩን ነው ምንጭቻችን የሚገልጹት፡፡
የመሣሪያ ትጥቅን ማስፈታት በተመለከተ በወያኔ መንግሥት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዋናነት የአርማጭሆና የወገራ አካባቢዎችን ቁጥር አንድ አድርጎ ፈርጇቸዋል፡፡
(ዝርዝር መረጃዎችን በየጊዜው እየተከታተልን ማቅረባችን ይቀጥላል)
ሙሉቀን ተስፋው
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!!
ግናዉ አበራ ጎባዉ ዛሬ ወደቀ
ዛሬ በታች አርማጭሆ ዶጋዉ ላይ ትጥቅ ሊያስፈታዉ የመጣዉን የትግሬ ወያኔን ጦር ገጥሞ ከ12 በላይ ከረፈረፈ በኋላ ከጀርባ በድንገት በደረሰ ልዩ ኮማንዶ ተመቶ ወድቋል። ጓዶቹም በተመሳሳይ የተጋድሎ አዉድ ከ 50 የሚልቁ የህዉሓት ወታደሮችን አጋድመዋል።
የጀግና ሰዉ ሞቱ እረፍቱ ነው

No comments:

Post a Comment

wanted officials