Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 7, 2016

የወልቃይት የማንነት ጥያቄ እና የኢሳት ሚና (ከጎሹ ገብሩ)




ከጎሹ ገብሩ
በሦስተኛ ክፍለ ዓለም ዙሪያ የሚፈጠሩት አምባ ገነን መሪዎች ከተዋጊ የጦር ጀቶች፣መድፍና ታንክ በበለጠ የሚያስፈሯቸው ነገሮች ቢኖሩ ነፃ ሚዲያና የሕዝብ ነውጥ እምቢተኝነት ብቻ ነው።The case of Welkait Tsegede and ESAT
ለዚህ ምክንያት ነው ሚድያውን በቁጥጥር ስር በማዋል የውሸት ቱልቱላቸውን ነጋ ጠባ በመደጋገም ህዝቡን በማሰልቸት የግዛት እድሜያቸውን ለማራዘም ያለ የለለ ሀይልና ገንዘብ በማባከን ሚድያን በማፈን ግዚያዊ እፎይታ በማግኘት የሚፅናኑት።
ጭቆናና የግፍ አስተዳደር ሞልቶ በመፍሰሱ ያሚያንገበግባቸው አካላትም እንዲህ አይነቱን አፈናና እመቃ ሰብረው ለመውጣት ሲሉ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የመታገያ ስልቶች በመጠቀም የዲሞክራሲ መብታቸውን ለማስከበርና ከለውጥ ፈላጊው ወገን ጋር ለመናበብ ተጨማሪ ርቀት በመጓዝ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ዋነኛው የመታገያ ስልት ሚድያ በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው።
የጨለማው ዘመን ለአምባ ገነን መሪወች ሽፋን በመሆን የግዛት እድሜያቸው እስከ ህልፈተ ሞታቸው መንገዱ አልጋ ባልጋ እንዲሆንላቸው ተቃዋሚዎችንና አገር ወዳዱን የተለያዩ ምክኒያቶች በማሳበብ ዘር መንዘሩን ከምድረ ገጽ በማጥፋት የሚፈፅሟቸው ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች አፈትልከው ወጥተው የዓለም ህብረተሰብ እንዳያውቅ አፋኝ ጓድ በየ ኮርነሩ በማሳለፍ ሰጥ ረጭ በማድረግ በሃገሪቱ ውስጥ የሚፈፅሟቸው በደሎች መክነው እንዲቀሩ በማድረግ ራሳቸው በሚቆጣጠሩት ሚዲያ ግን ምን ያህል ህዝብ እንደሚወዳቸውና አብዛኛው የአገሪቱ ዜጋ ለቀን ከሦስት ጊዜ በላይ በልቶ የሚጠግብበት አገር እንደሆነች አስመስለው በማውራት የዓለምን ህብረተሰብ በውሸት ቀልቡን በመሳብ በጆንያ ዶላር በመቀበል ሕዝብና አገር ከሌላው ክፍለ ዓለም እንዳይገናኝ ላንቃውን ዘግተውት ይኖራሉ። የሰባአዊ መብት ተሟጋች ሃይሎች ይህንን ሁሉ ውሸት ለማጋለጥ የሚወስድባቸው ጊዜ ግማሽ ህዝብ ካለቀ በኋላ ነበር።
እንደ እኔው ግምት አንድን የአምባ ገነን ሥርዓት ገርስሦ ለመጣል ብዙ አመታት ከሚፈጅባቸው የዓለማችን ሃገራት መካከል በዋናነት የምትጠራ አገር ኢትዮጵያ ናት ብል የተጋነነ መስሎ እንዳይሰማችሁ። ይህን ስል ማስረጃን በማስደገፍ ነው። በእኔው የትውልድ ዘመን እንኳ ሦስቱ ሥርዓቶች በተፈራራቂ ወቅት የባላባታዊው ሥርዓት ንጉሱ ለ40 አመት፣ የፋሽሽቱ ደርግ 17 አመትና የፋሽሽቱ ወያኔ 25 አመትና በመቀጠል ላይ ያለው እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ይህ ሊሆን የቻለው ደካማ የመገናኛ መረጃ በመኖሩ የህዝብ ትግል አንድ እርምጃ ወደ ፊት እንዳይሄድ ገድቦት ቆይቷል።
ወደ ተነሳሁበት ልመለስና በኢትዮጵያችን ታሪክ ውስጥ የመገናኛ ተቋማት ለአምባ ገነን መሪወች ከማገልገል አልፈው የህዝብን የልብ ትርታ መሰረት በማድረግ ሳይሸማቀቁና ነፃ ሁነው በአገር ቤት ውስጥ ሊያገለግሉ ቀርቶ ከአገር ዉጭ ሆነው ለታፈነው ወገናቸው ማወቅ የሚገባውን ዜና እንዳያገኝ በአንደኛ ደረጃ ከሚታፈኑ የሚድያ ተቋማት መካከል ቀዳሚ ሆኖ የሚጠቀስው ኢሳት ነው። ያም ሆኖ ግን ነፃነት በጠማው ህብረተሰብ የሚረዳ ተቋም እንደ መሆኑ መጠንና ተመክሮ ያካበቱ ብርቅየና በእሳት ተሞክረው ያለፉ ባለሞያዎች የሚመራ በመሆኑ የደደቢት ሽፍቶች ጥይት ተኩሰው ያልታጠቀ ሴትና ሕፃን ከመግደል ባለፈ የማሰብ ሽሎታ የላቸውም። በአሁኑ ስዓት የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጀሮ በመሆን ለህዝብ የቆመ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን የደደቢት ዲቃላ ፋሸሸት ወያኔ ኢትዮጵያን ለ50 አመት አንበርክካ ለመግዛት የነደፈችው ሃሳብ በአጭሩ ተኮላሽቶ እርቃኗን እንድትቀር ያደረገ የሚድያ ተቋም ቢኖር አሁንም ኢሳት ብቻ ነው።
ይህን ልል የቻልኩበት ምክንያት ከ1972 አ.ም ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በፋሽሽቷ ሕወሓት የአረመኔወችና የወሮበላዎች ስብስብ ድርጅት ተከዜን በመሻገር የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝብን አፍና ዘሩን በመምተር፡ተፈጥሮ የለገሰለት ለም መሬት በመንጠቅ፡ ከሞቀው ቤቱ ገፍትራ በማስወጣት፤እስር ቤት እና ስደት መዳረሻው እንዲሆን፣ ሴት እህቶቻችን ሳይፈልጉ ገና ለአቅመ ሄዋን ሳይደርሱ አስገድዶ በመድፈር ይህ ነው ተብሎ ሊገመት የማይችል በደልና ሰቆቃ ስታደርስ በርቀት ያለው ኢትዮጽያዊ ይቅርና በጉርብትና የሚኖረው ወገናችን ሊደርስልን ያልቻለበት ምክንያት የሚወጡና የሚገቡ ዜናወችን ወያኔ ቀፍድዳ ወደ ህዝቡ እንዳይደርስ አፍና በመያዟ ነው። ያም ሆኖ ጀግናው የወልቃይት ጠገዴና የጠለምት ህዝብ ለመብቱ፣ ለነጻነቱና ለማንነቱ ቆርጦ በመነሳት ያሳዬው እልክ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትግል ለሰላሳ ሰባት ዓመት አጋር አልባ ብቻውን ደሙን እንደ ነሃሴ ዝናብ ሳያቋርጥ በማፍሰስ፣የእስር ሲቃና የስነ ልቦናዊ ጦርነቶች እንደ አመጣጣታቸው በማስተናገድ አሁን ለደረሰበት ብሩህ የነፃነት ጎህ ቀዳጅ ተስፋ መቃረብ ሊደርስ የቻለው በማይበገረው የሞራል ፅናቱ ለመሆኑ ሊካድ የማይቻል እውነታ ነው።
ወልቃይት ጠገዴ የዕልፍ አዕላፍ የጀግኖች እናት የነበረች ነገር ግን በተለያዩ የአገዛዝ ሥርዓቶች በሚፈጠሩት የለዉጥ ማዕበሎች አጋር ልጆችዋ የገበረች ብትሆንም አሁንም የማህጸኗ ፍሬ ጀግኖች ከማምረት አልተቆጠበም እስቲ ያለፉትን ለታሪክ በመተው በቅርቡ በታሪካዊቷ ክፍለ አገር ጎንደር ከተማችን ጨለማን ተገን በማድረግ በአሸባሪዋ ወያኔ እብሪተኝነት የተቀነባበረዉ የንቀት ድራማ ለማክሸ በግሉ መሳርያ ራሱን ተከላክሎ ብዛት ያላቸው የአጋዚ ቅልብ ወታደሮች አደራርቦ በማጋደም የኢትዮጵያ ልጅ ሞትን እንጅ እጅ መስጠት አልተማረም በማለት የቅድመ አያቶቹንና ወላጆቹን ስም ዳግም ያስጠራው ከድሃዋ የአማራ ማህጸን የወጣው ወጣቱ ኮረኔል ደመቀ ዘውዱና አጋሮቹ ናቸው። ባለፉት ምዕት አመታት የኮሶ ሻጭ ተብሎ ተንቆ የነበረዉ መይሳዉ ካሳ ተበታትና የነበረችዉን ኢትዮጵያ አንድነቷን አስከብሮ ለትዉልድ እንዳስተላለፈልን ዛሬ ደግሞ ዳግማዊዉ መይሳ ኮረኔል ደመቀ ዘዉዱ በወልቃይት ጠገዴ ልዩ ስሟ ጠለሎ ከተባለችዉ መንደር እነ ደጃዝማች ደስታ ማሩ እንደ አሁኖቹ ወያኔዎች በዝያን ግዜ ልባቸው በተዕቢት የተወጠረው የፋⶥቷ ጣልያን ወራሪ ሃይል መፈጠሩ እስኪጠላ አባረው አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ካባረሩበት ቦታ ተወለዶ ያደገ ጀግና እንኳንስ ለራሱ ለ25 ዓመታት በፍራት ቆፈን አንገቱን በፋሽሽቷ ወያኔ ተንኮልና የሃሰት ፕሮፖጋንዳ አንገቱን ያጎነበሰዉ ሕዝባችን ዳግም ቀና ብሎ በኩራት እንዲራመድ ያደረገ ለመሆኑ በአራቱ ማዕዘናት የሚኖረው ኢትዮጵያዊና የዓለም ሕብረተሰብ የመሰከረለት የዘመኑ ጀግናችን ነው።
ወያኔ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የፈፀመችዉ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከሁሉም ነገር ቅድሚያ በመስጥት በግንባር ቀደም ለሚመለከትው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ፣ለዓለም ለፖለቲካ ድርጅቶች፣ለሊሕቃንና ተቆርቋሪ ሃይሎች ታማኝ ማስረጃ በማስደገፍ ሃያ አራት ስዓት ሙሉ ያለ እረፍት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ እስከ አሁን ድረስ አብዛኛው ግዚያቸው ለዚህ ተግባር በማዋል በወያኔ ተዳፍኖ የኖረውን በደል ከተቀበረበት ቆፍረው በማዉጣት አጋር የሆነው የአማራው ወገኑና ኢትዮጵያዊ በፍጥነት ደርሶ ከጥፋት እንዲያድነው ካደረጉት የሚድያ ተቋማት በአንደኛ ደረጃ የሚጠቀስ ኢሳት ሲሆን በተለይ ደግሞ ከአካባቢው አብራክ ተወልደው ያደጉ በልሳነ ጉፏአን ድርጅት ጥላ ስር በመደራጀት ለወገን አጋርነታቸው ቅድምያ በመስጠት የተካኑ አገር ወዳዶች ጋር አብሮ በመስራት ትልቁን የአምበሳ ድረሻ ከወሰዱት ጋዜጠኞች መካክከል፦
1ኛ/ አቶ አበበ ገላው በአሁኑ ስዓት የኢሳት ዳሬክተር።
2ኛ/ አቶ ሲሳይ አጌና አንደበተ ሙሉ ብስለትና ጥንካሬ የተላበሰው።
3ኛ/ አቶ መሳይ መኮነን በአቀራረቡና በድምጹ እንደ M29 ተዋጊ አውሮፕላን የጠላትን ልብ ሰንጥቆ የሚጥልና ሌሎች ብርቅዬ የኢሳት ባልደረባዎች በሙሉ ታሪክ በነቂስ እስኪ ዘክራችሁ ድረስ የግሌ ምስጋናና አድናቆት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ እንድያውቅልኝ በዚች አጭር የጫርኳት መጣጥፍ መስጋናየን አቅርባለሁ።አውቅለሁ ለአገሩና ለወገኑ በፈቃደኝነት የሚሰራ ከማንም ምስጋናን አይሻም የጉዳዩ ጠንሳሽ ባለቤቶች ናችሁና።
ሌሎቹም በዚሁ ጉዳይ ለተባበሩን የሶሻል ሚድያወች፣ድህረ ገጾችና የመገናኛ ተቋማት እንደ የአመሪካና የጀርመን ሬድዮ ደምፅ የመሳሰሉ በወቅቱ በተፈጠረው በደል በአካባቢው ከሚኖረው ሕዝብ ጋር በስልክ በመገናኘት በምድር ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ጠይቀው ለአየር በማብቃት በመላው ዓለም ጀሮ እነዲደርስ በመተባበራቸው የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል።
ወያኔ ገና ህዝብ ሳይነቃና ሳይጠረጥር 25 ዓመት ሙሉ ስልጣን ኮረቻ ላይ ቁብ ብሎ እንዲቆይ ምክንያት የሆነው ቅራቃምቦ ውሸቱ በሚነዛበት የሕዝብ ሀብት በሆነው ሚድያ ነበር። ውሸቱን የሚያጋልጡት የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ከተቋቋሙ ጀምሮ ግን የውሸት ቱልቱላው ተጋለጦ እርቃኑ ቀርቶ ተደብቆ መግደልና ሕዝበን በዘር ከፋፍሎ በማናቆር የፖለቲካ ቁማር መጫወት እንደ ሙዝ ልጣጭ ተበልቶ የተጣለ ግዜው የረፈደበት የደደቢት ሽፍቶች ሥልት ነው። ጎበዝ ወደ አይቀሬው ነፃነታችንና ዲሞክራስያዊው መብታችን ለመረከብ አስራ አንድ ሥዓት ላይ ደርሰናልና የሕብ ዐይንና ጀሮ የሆነውን ኢሳትን እስከ የነፃነታችን ማግስት ድርስ ከጎኑ እንሰለፍ።
ኢሳት አውነትም የነበልባል እሳት
የወያኔ የራስ ምታት
ለኢትዮጵያውያን የጨለማ መብራት
ገደል የማይከትረው ዓቀበት
ድብቁ የወይኔን ሴራ ለማጋለጥ
የቁርጥ ቀን ልጆች የተሰበስቡበት
ከጎኑ አንቁም በሀብረት
እሰከ የወያኔ ግብአተ መሬት።
ጨለማ መጋረጃው – ሓሰት መሳርያው
ደም የጥም ማርክያው – ጭካኔ ሞያው
ታሪክ በራዡ ወያኔ አረመኔው
ዘርን አንደ ባቄላ ፈልፍሎ ጨረስው።
ከዓርባ ዓመት በፊት የጠነሰሱት ተንኮል
በዘር ከፋፍሎ ኢትዮጵያን ለመግደል
ሀብቷን ወረው ለወርቃማው በማደል
ሌላው ለሆዱ በቻ አያሰበ አንዲኖር።
ወያኔ ዘር ማጥፋቱ ሀ በሎ የጀመረው
ወልቃይት ጠገዴ-ኢትዮጵያዊውን ነው
ሌላው ወገኑ አንዳይሰማ
ላንቃውን ዘግቶ እንደ አሳማ
ባዶ ሰደሰት ላይ አጎረው ወገን አንዳይሰማ።
አረ ሥንቱ ወላድ – የደም አንባ አነባ
አረ ሥንቱ የሴት አመቤት- ተደፈረች ተገዳ
እረ ሥንቱ ጎበዝ በዱላ ተመታ
በወያኔው ቅልብ የደደቢት ባንዳ፡፡
በጥበንጃ ጋጋታ በማሰፈራራት
አነዱን ዘር አጥፍቶ ሌላ መተካት
መፍትሄ አይሆንም-ግዜ ለመግዛት።
ብዙሃንን ሰጥ አድርጎ ለመግዛት
በጠበንጃ ሳይሆን – በማግባባት
በመተላለክ ሳይሆን-በብልሃት
በመናናቅ ሳይሆን- በመወያየት
በማፈን ሳይሆን-በግልፅነት
በማለያየት ሳይሆን-በማገናኘት
በማስፈራራት ሳይሆን-በትዕግስት
ለሳን በመዝጋት ሳይሆን በመክፈት
አንዲሕ ከሆነ ደንብና ሥርዓት
ተፋቅረን አንኖራለን ሁላችን በህብረት።
ዘርን አንደ ባቄላ ፈለፍሎ ማጥፋት
ለኛ አይበጅም አንዲህ ዓይነት ሥራዓት
ወያኔን ማስወገድ ነው – ከሥር መስረት።
ሞት ለሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ
ኢትዮጵያ ለዘል ዓለም ትኑር።
መስከረም 28 2009

No comments:

Post a Comment

wanted officials