Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 22, 2016

ኢንተርኔት የተቋረጠባቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ተቋማት አገልግሎት ሳያገኙ ክፍያን እንዲፈጽሙ መጠየቃቸው ተገለጸ

ኢንተርኔት የተቋረጠባቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ተቋማት አገልግሎት ሳያገኙ ክፍያን እንዲፈጽሙ መጠየቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 11 ፥ 2009)
የአስቸኳይ ጊዜ ዋጁ ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠባቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ተቋማት አገልግሎት ሳያገኙ ክፍያን እንዲፈጽሙ መጠየቃቸው አግባብ አለመሆኑን አስታወቁ። 
በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር በሚል መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ ይታወቃል። 
ይሁንና ለአገልግሎት ከፍተኛ ክፍያን የሚከፍሉ ደንበኞች አገልግሎት ባላገኙበት ወቅት ጭምር ወርሃዊ ክፍያን እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። 
መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት አለም አቀፍ ተቋማት ተመሳሳይ ቅሬታን አለማቅረብ አቤቱታቸውን ባለፈው ሳምንት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ማቅረባቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት አገልግሎት መቼ እንደሚቀጥል ማረጋገጫን ባለመስጠታቸው ምክንያት የዴንማርክና የሌሎች ሃገራት አምባሳደሮች ተቃውሞ እንዲቀርቡ አፍሪካ ኒውስ ከቀናት በፊት ዘግቧል።
ተመሳሳይ ቅሬታን ማቅረብ የጀመሩ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ድርጅቶች ኢትዮ-ቴሌኮም ያልሰጠውን አገልግሎት እንዲከፍሉ በማስገደድ ላይ መሆኑ አግባብ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አስረድተዋል።
ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሲል የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔትና ሌሎች የመረጃ መለዋወጫ አማራጮች ላይ እገዳ መጣሉን ዘግበዋል።
በመደበኛ ስልክ የሚደረጉ የኢንተኔት አገልግሎቶች በአንዳንድ አካባቢዎች መስራት ቢጀምሩም አሁንም ድረስ በልዩ ክፍያ የሚያስተናግዱ እና የእጅ ስልክ ተጠቃውሚዎች አገልግሎቱን እያገኙ እንዳልሆነ ለመረዳት ተችሏል።
አማራጭ እንደሌላቸው የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎች እገዳው የሃገሪቱን ኢኮኖሚና ገጽታ ክፉኛ ሊጎዳ እንደሚችልም አስታውቀዋል።
ኢትዮ-ቴለኮም ከደንበኞቹ እየቀረበ ባለው ቅሬታ ዙሪያ ምላሽን ባይሰጥም የመንግስት ባለስልጣናት ሃገሪቱ ወደ መረጋጋት እስከምትመለስ ድረስ አገልግሎቱ ተቋርጥ እንደሚቆይ ገልጸዋል።
አንድ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በማቋረጧ ምክንያት ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን ሃሙስ ይፋ አድርጓል።


No comments:

Post a Comment

wanted officials