Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, October 11, 2016

አሳዛኝ ዜና 50 የሚሆኑ ዐማሮች በአፋር ክልል ፖሊስ ተገደሉ፤

አሳዛኝ ዜና
50 የሚሆኑ ዐማሮች በአፋር ክልል ፖሊስ ተገደሉ፤
በአፋኙ የወያኔ መንግሥት ትምህርታቸውን 10ኛ ክፍል በላይ እንዳይቀጥሉ የተፈረደባቸው የዐማራ ወጣቶች ዛሬ ደግሞ በአፋር ፖሊስ በጥይት ተጨፍጭፈው መገደላቸውን ከወልዲያ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያረጋግጣል።
ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው፤ በአገራቸው ባይተዋር የሆኑት ከተለያዩ የወሎ አካባቢዎች የተሰባሰቡት ወጣቶች ለስደት ወደ ሰው አገር ተነሱ። 200 የሚሆኑ ወጣቶች በኮንቴነር እንደ እቃ ታሽገው በሚሌ በኩል አልፈው ወደ ጅቡቲ ብሎም ወደ አረብ አገር ለማቅናት ነበር እቅዳቸው። በልጅነት ከትምህርት ገበታቸው የተባረሩት እነዚህ ወጣቶች በአገር ላይ ተስፋ ቢያጡ ነበር እንዲህ ለስደት መውጣታቸው።
ነገር ግን ሕልማቸው አልተሳካም፤ የሌላ አገር ድንበርም አላቋረጡም። የአፋር ፖሊስ በዐማራ ፖሊስ የታጨቀውን ኮንቴነር በጥይት በዳደሰው። የመኪናውን ጎማም እንዲሁ። 200 ዐማራ ወጣቶችን የያዘው ኮንቴነር ተገለበጠ። ያልፍልኛል ብለው የወጡት ወጣቶች ፈቅ ሳይሉ ሕይወታቸውን አጡ። 50 የሚሆኑት ወዲያውኑ ሲሞቱ ከ100 በላይ ደግሞ በከፍተኛ አደጋ በወልዲያ ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ።
በሆስፒታሉ ከፍተኛ የሆነ የደም እጥረት እንዳለም ሰምተናል፤ የወልዲያ ወጣቶች ደም በመለገስ ወንድሞቻችን ትታደጉልን ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን//
ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials