ሕዝባዊው አመጽ ለ4 ኪሎው ቤተመንግስት 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ደረሰ – የአቃቂ ቃሊቲ ሕዝብ ተነሳ – መርካቶ ሱቆች እየተዘጉ ነው
በዛሬው እለት በሃገሪቱ እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ቁጣ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት እየተጠጋ ነው:: በአቃቂ ቃሊቲ እጅግ በረካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ አደባባይ በመውጣት እምቢተኝነቱን እያሳየ ሲሆን መንገዶች ሁሉ እየተዘጋጉ ይገኛሉ::
ከ4 ኪሎው ቤተመንግስት 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ ሕዝብ አንገዛም ከማለቱ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ንግድ እና ትምህርት ቤቶች መዘጋጋታቸው ተሰምምቷል:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሕዝብ ላይ እርምጃ ቢወስድም ሕዝቡ ግን በጥንካሬ ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ ይገኛል::
ይህ ሕዝባዊው አመጽ ወደ ሃና ማሪያም እና መርካቶ አካባቢም የተዳረሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመርካቶ ሱቆች በመዘጋጋት ላይ ይገኛሉ:: በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ያለው ሕዝባዊ አመጽ ከትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ቁጥጥር ውጭ እየሆነ መሆኑን የሚገልጹት የዜና ምንጮች በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ቦታውን ለቆ ካልወጣ መፍትሄ እንደማይገኝ ይናገራሉ::
No comments:
Post a Comment