Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 28, 2016

ወታደራዊ ምዝገባ ለማካሄድ ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው


ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰራዊቱ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም እየጠፋ በመምጣቱ የሃይል መሳሳት ያጋጠመው አገዛዙ፣ ወጣቶችን ወደ ውትድርና ስልጠና ለመውስድ አዲስ ማስታወቂያ እያስነገረ ቢሆንም፣ ጥሪው ተቀባይነት አላገኘለትም። በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ወጣቶች እንዲመዘገቡ የሚያሳስቡ ማስታወቂያዎች እንየተነገሩ ነው። ቀደም ብሎ በግልጽ ይወጣ የነበረው የወታደር የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት ማጣቱ በሚዲያ ከተዘገበ በሁዋላ፣ አገዛዙ ቅጥሩን በተለዬ መንገድ ለማስፈጸም እንቅስቃሴ ጀምሯል። ወጣቶቹ የትምህርት ስልጠና እንደሚሰጣቸው እየተነገራቸው እንዲመዘገቡ በማድረግና ስልጠናውን በአዋሽና በሌሎችም ቦታዎች እንዲካሄዱ በማድረግ፣ ወጣቶችን ወደ ውትድርና የማስገባት እቅድ መነደፉን ምንጮች ገልጸዋል።
የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ አዲስ ባወጣው አዋጅ ፣ አዋጁ እስከሚነሳበት ጊዜ ድረስ ወታደሮች የስራ መልቀቂያ ወይም የእረፍት ፈቃድ መጠየቅ አይችሉም። በዚህ ውሳኔ ከ7 ሺ ያላነሱ 7 አመታት አገልግለው የስራ መልቀቂያ የጠየቁ ወታደሮችን አግቶ ለመያዝ እንዳስቻለው ምንጮች ገልጸዋል። የ7 አመታት ግዴታቸውን ፈጽመው የስራ መልቀቂያ የሚያቀርቡ ወታደሮች መበራከቱን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ በአዳዲስ ምልምል ወታደሮች ለመተካት ቢያልምም ይህም እቅዱ አልተሳካም።
ሰራዊቱ በህጋዊ መንገድ ስንብት ሲጠይቅ “በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ እና በመለስ አጽም” እየተባለ ይለመን የነበረው አሰራር ዋጋ አልባ መሆኑን ተከትሎ፣ የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን በድፍረት ሲያቀርቡ የነበሩ በርካታ ወታደሮች ታስረዋል። በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ተቃውሞ ተከትሎ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የጠፉ ሲሆን፣ ብዙዎች መሳሪያቸውን እየሸጡ ከህዝብ ሲቀላቀሉ ሌሎች ደግሞ የነጻነት ሃይሎች ተቀላቅለዋል።
በሌላ በኩል አገሪቱን የሚገዛው ወታደራዊ እዙ ወይም ኮማንድ ፖስቱ ከ800 በኦሮምያና አማራ ክልሎች ከወታደሮች የተቀሙ ከ 513 ጠመንጃዎች ከ300 በላይ የሚሆኑትን አስመልሻለሁ ብሎአል።
የተባለው አሃዝ ትክክል ይሁን አይሁን ማረጋጋጥ ባይቻልም፣ ወታደሮች አሁንም ድረስ መሳሪያቸውን እየያዙ እንደሚጠፉ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የሚጠፉ ወታደሮች የተሻለ አቀባባልና አያያዝ እንደሚደረግላቸው የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መገልጻቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials