Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 28, 2016

የአጋዚ ጦር እየተበታተነ ነው ተባለ

የአጋዚ ጦር እየተበታተነ ነው ተባለ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በቅርቡ አጋዚ ክፍለጦርን ለቀው የወጡ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት ጦሩ ከምንጊዜው በላይ እየተበታተነ ይገኛል። አብዛኛው የሰራዊቱ አባል በክፍለጦሩ ውስጥ የሚታየውን ፍጹም ዘረኝነት በመጥላት እየጠፋ ፣ ክፍለጦሩን አመናምኖታል። በአሁኑ ሰአት 2 ሺ የሚሆኑ አባላት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ ከ2007 ዓም ጀምሮ እስካሁን ወደ 3 ሺ የሚደርሱ የአጋዚ ወታደሮች ጥለው ጠፍተዋል። በተለይ ጦሩ ሶማሊያ ገብቶ ከወጣ በሁዋላ አብዛኛው የሰራዊት አባላት አጋጣሚውን ተጠቅመው ጥለው ጠፍተዋል። በእያንዳንዱ ቲም ውስጥ ቀደም ብሎ 10 ወታደሮች የነበሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት 3 ብቻ ይገኛሉ።
አብዛኞቹ የአጋዚ ጦር አባላት በአብዛኛው በኦሮምያ ሻሸመኔ አካባቢ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የአጋዚ ጦር አባላት ቁጥር መመናመኑን ተከትሎ ከአጋዚ ጦር ውጭ ያሉ ወታደሮች እንዲመደቡ መደረጉንም ገልዋጸል። የአጋዚ ጦር አባላት ሁኔታዎች ቢመቻችላቸው ሁሉም ከሰራዊቱ ለመልቀቅ ፈቀዳኛ ናቸው የሚሉት አባላቱ፣ በአሁኑ ጊዜ አጋጣሚውን እየፈለገ የሚወጣውን ወታደር ለመተካት አዲስ ምልምል ወታደሮችን ማግኘት አልተቻለም ይላሉ።
በሶማሊያ በአጋዚ ጦር አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ወታደሮቹ ተናግረዋል። ሶማሊያ ገብተው ከፍተኛ መስዋትነት ቢከፍሉም፣ በመልሱ ምንም ጥቅም አለማግኘታቸውን ተናግረዋል። ከዚህም በላይ ከሻለቃ በላይ ያሉት አዛዦች ከአንድ ብሄር የተውጣጡ በመሆናቸውና ትእዛዝ የሚሰጡትም እነሱ በመሆናቸው፣ ተራው ወታደር ሊቃወም ቢሞክር በቀጥታ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ ኢሳት በቡድን ያነጋገራቸው አባላቱ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials