Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 21, 2016

በስደት የሚገኘው ሕጋዊው ሲኖዶስ እና የአትላንታዋ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በተመለከተ መግለጫ አወጣ



holy sinod excile
ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ እና የአትላንታ ቅድስት ማርያም ምእምናን ያወገዙት የቦርድ ሊቀመንበሩ ምግባር።
ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 16 ዕለት የአትላንታ ቅድስት ማርያም ምእመናን ያለ ህዝብ እውቅና የቦርዱ ሊቀመንበር ከጓደኞቹ ጋር ተማክሮ ቤተክርስቲያኗን ከሃያ ዓመታት በላይ ያገለግሉት አባት በህገወጥ መንገድ ለማባረር ያደረገውን ሙከራ በአጽንዖት ሲቃወሙ ውለዋል። የቤተክርስቲያኗን ህገ ደንብና የውስጥ መመሪያ እንዲሁም ቀኖና ቤተክርስቲያንን የጣሰው መመሪያ ማህበረ ምእመናን ቅዳሴውን አቋርጦ በዝማሬ በጨዋ መልኩ ተቋውሞው ሲያሰማ አርፍዷል። የቤተክርስቲያኑ ህገ ደንብ ማህበረ ምእመናኑ በአወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቦርዱ እና በካህናት ላይ አለመግባባት ሲኖር የማህበረ ምእመናን ውሳኔ የመጨረሻው ቢልም የተወሰኑት የቦርድ አባላት በማን አለብኘነት ሊቀ ጳጳስን የማባረር ሙከራ አድርገዋል። ምእመናን እጅጉን ያስደመመው ነገር ቦርዱ በሌለው ስልጣን ሊቀ ጳጳስን ለማባረር መወሰኑ ብቻ ሳይሆን ማኀበረ ምእመናኑ ሳያጸድቀው የስንብት ደብዳቤ መጻፉ ነው። ይህ አድራጎት የህዝብ መብት ረግጠው እኛ እናውቅልሃለን እንደሚሉት የሃገራችንን አምባገነን መሪዎች ምሳሌዎች ናቸው።በአሁኑ ወቅት እነዚህ አምባገነን በህዝባችን ላይ የሚያደርሱትን ሰቆቃ እንዲቆም ተሰባስበን የምንጸልይበትን የጋራ ቤታችን ለማፍረስ ያደረጉት ሙከራ አሳዛኝ ነው። ከሁሉም በላይ ምእመናን እጅግ በካህናቱ ሲያዝኑም ተሰምተዋል። ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ድርጊቱ አውግዞ ቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈረሰ መሆኑን ገልጾ ያለ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ የሚካሄደው ስርዓት ተቀባይነት እንደሌለው ለካህናቱ በደብዳቤ ቢያሳውቅም የክህነታቸው ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ጥሰው የምእመኑን የአቶ አባተ ትእዛዝ ሲፈጽሙ ውለዋል። ሆኖም አብዛኛው ምእመናን የእለቱን አገልግሎት አልተቀበለውም ወደፊትስ ከነዚህ ካህናት እንዴት ነው የምንቀበለው መስቀላቸውን እንዴት ነው የምንሳለመው ሲሉም ተደምጠዋል። ለማንኛውም የህጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ ለቦርዱ የጻፈውን ደብዳቤ እንደሚከተለው ያንብቡ።
ተክለጊዮርጊስ ዘአትላንታ

No comments:

Post a Comment

wanted officials