Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 8, 2016

በህዝባዊ ተቋውሞ የተወጠረው ወያኔ በጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ ሜርክል ጫና ሊገጥመው ነው

በህዝባዊ ተቋውሞ የተወጠረው ወያኔ በጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ ሜርክል ጫና ሊገጥመው ነው 


ለተጠናከረው ዘገባ ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን
http://www.addis-abeba.diplo.de/
የጀርመኑዋ መርሃ መንግስት አንጌላ መርክል (Chancellor Dr. Angela Merkel) በ 11/10/ 2016 እኤአ ( 30/ 01/ 2009 ዓም) ይፋዊ የሰራ ጉብኝት በኢትዮጵያ እንደሚያደርጉ ታወቀ። የወያኔ መንግስት በአገር ውስጥ በከፍተኛ የህዝብ ተቋውሞና አልገዛም ባይነት ተወጥሮ ባለበት ባአሁኑ ወቅት እንደዚህ ያለው ጉብኝት ከወዳጆቹ ምእራባውያን ለተጨማሪ ነቀፌታ እንዲሁም ጠጠር ላለ ጫና ሊዳርገው ይችላል። በቢሾፍቱ የኢረቻ በአልን ለማክበር በወጡት ኢትዮጵያውያን ላይ የወያኔ መንግስት በተጠቀመው የአስለቃሽ ጢስ ጥይት ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ወደ 680 በደረሰበት ፣ በመላው የአማራ ተወላጅ ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት በታወጀበት ፣ በአፍሪቃ መቀመጫና የተለያዩ አገራት ኤምባሲ በሚገኝባት በአዲስ አባባ የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያዎች በተዘጉበት በዚህ ጊዜ ወያኔ እንኩዋን በቀጠናው በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ማስፈን እንደተሳነው እንዴት አድርጎ ለጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ መርክል ማስረዳት እንደሚችል ትልቅ የቤት ስራና የራስ ምታት ሆኖበታል። በአዲስ አበባ የጀርመን ኤምባሲ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት የአንጌላ መርክል የስራ ጉብኝታቸው ዋናው ምክንያት በቀድሞ የታንዛኒያ መሪ በነበሩት ጁሊዬስ ኔሬሬ (Julius Nyerere) ስም የተሰየመውን አዲሱን የሰላምና ደህነት ህንጻ ለማስመረቅ እንደሆነ መረዳት ተችሏል። ካንስለር ሜርክል በዚሁ ህንጻ ንግግር እንደሚያደርጉም መግለጫው ጠቅሱዋል። ይህ ህንጻ በጀርመን መንግስት የገንዘብ እርዳታ እንዲሁም የጀርመን ተቋራጭ የተገነባ መሆኑን ኤምባሲው በመግለጫው አስፍሯል። የመላ ኢትዮጵያውያንን ሰላምና ደህንነት እየነፈገ አምባገነኑ የወያኔ መንግስት በቀጠናው ሰላምን አሰፍናለሁ በሚል ሰበብ የስልጣን እድሜውን ለአንድም ቀን ብትሆን ለማራዘም ለምእራብያውያን ጉዳይ አስፈጻሚና ሎሌ ከሆነ ሁለት አስርተ አመታት አልፈውታል። በርግጥም የወያኔ መንግስት ለውስጥ (ለህዝቡ) ቀካ ለውጭ አልጋ ነው። የጀርመን መንግስት በከፍተኛ ገንዘብ ይህንን ህንጻ ያሰራው ገና ለገና ወያኔ ደሃውን የኢትዮጵያ ሰራዊትን( የተደላደሉትን የአጋዚ ወታደሮችን አያካትትም ) በሱማሌ ይገብርልናል በሚል እሳቤ እንጂ እውነተኛ ሰላምን ደህንነትን እንዲሁም ዲሞክራሲን አስቦ እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል። ለዚህም ማስረጃ በወያኔ መንግስት ትእዛዝ የአጋዚ ወታደሮች በኦርምያ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በጎጃም፣ በኮንሶ፣ በጋምቤላ እንዲሁም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ያደረሱትን አረመናዊ የሆነ ግድያ መመልከት በቂ ነው። ወያኔ የበግ ለምድ ለብሶ ተኩላ መሆኑን( እንኩዋን አሽባሪን ሊዋጋ እራሱ አሽባሪ መሆኑን) በሰላማዊ መንገድ ተቋውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ በወጡ ንጹሃን ዜጎች ላይ እየወሰደ ባለው ግድያ፣ አፈና፣ እስራትና ድብደባ በተግባር ለአለም አረጋግጧል።
angela
ምእራብያውያኑ አፍሪቃን የመቀራመት አባዚያቸው በአሃጉሪቷ ውስጥ በከፍተኛ ተቀባይነት እንቅስቃሴ በምታደርገው ቻይና ምክንያት እንደገና እያገረሸባቸው ይገኛል። 200 ሚሊዮን
ዶላር በማውጣት የቻይና መንግስት በ 2012 እኤአ የአፍሪቃ ህብረት ህንጻን በስጦታ መስጠቱ ምእራባውያንም አትኩሮታቸውን ወደ አፍሪቃ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል። ለዚህም ይመስላል የጀርመን መንግስት ይህን በጁሊዬስ ኔሬሬ ስም የተሰየመውን አዲሱን የሰላምና ደህነት ህንጻ ፈንድ በማድረግ ያሰራው። ከጸጥታና ደህንነት በተጨማሪ የካንስለር አንጌላ መርክል የኢትዮጵያ ጉብኝት የስደተኛ ጉዳይን ይጨምራል ተብሎ ይገመታል። በ 11/ 10/ 2016 የጀርመን ኤምባሲ ከአለም የምግብ ፕሮግርም(WFP) ጋር በመሆን ባወጣው ጥምር ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑት ዮሃም ሽሚትስ (JoachimSchmidt) የስደተኛ ጉዳይ በጀርመን ውስጥ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል(http://www.wfp.org/news/news-release/germany-provides-more-critical-support-refugee-food-assistance-ethiopia) ። የወያኔ መንግስት ቁንጮ የሆኑት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ በአየር መዛባት ወይም ኤል- ኒኖ መንስኤ ተከስቶ በነበረው የረሃብ ችግር በኢትዮጵያ ውስጥ ተጠልለዋል ያሉትን የደቡብ ሱዳን፣የኤርትራንና የሶማሌን ስደተኞችን እንደ ምክንያት ማቅረባቸው ይታወሳል(http://www.aljazeera.com/news/2016/03/ethiopia-calls-international-drought-bites-160317142601295.html ) ። እነዚህ ስደተኞች ወደ አወሮፓ እንዳይመጡ ለመከላከል ምእራባውያኑ ለወያኔ ዳጎስ ያለ ገንዘብ በየአመቱ እንደሚለግሱት ቢታወቅም በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ በሚያደርገው የመብት ጥሰትና ግድያ ምክንያት ያቀደውን የገንዘብ እርዳታ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ በ 06/ 09/ 2016 እኤአ መወሰኑ ይታወሳል(https://www.euractiv.com/section/development-policy/news/weds-no-emergency-trust-fund-money-goes-to-ethiopian-government-commission-stresses/ ) ።የጀርመን መንግስት እነዚህ ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆዩ ከ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ በ 2016 እኤአ ለግሷል። ይህን የካንስለር አንጌላ መርክልን የኢትዮጵያ ጉብኝትን በመቃወም በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቋውሞ ሰልፍና የፔትሽን ፊርማ ማሰባሰብ ፕሮግራሞችን አድርገዋል።sources http://www.addis-abeba.diplo.de/https://www.euractiv.com/section/development-policy/news/weds-no-emergency-trust-fund-money-goes-to-ethiopian-government-commission-stresses/ http://www.aljazeera.com/news/2016/03/ethiopia-calls-international-drought-bites-160317142601295.html http://www.wfp.org/news/news-release/germany-provides-more-critical-support-refugee-food-assistance-ethiopiaBy Zerihun Shumete/ from Germany

No comments:

Post a Comment

wanted officials