Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 14, 2016

ህወሃት 250 ሚሊዮን ራንድ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ ሊያሸጋግር መሆኑን ምንጮች አስታወቁ!

ጥብቅ መረጃ . . .
ለደቡብ አፍሪካና አካባቢዉ ለመላዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ....
ህወሃት የሚመራዉ ወንጀለኛ ቡድን 250.000.000 Rand ሁለት መቶ ሐምሳ ሚሊዮን ራንድ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ ሊያሸጋግር መሆኑን ምንጮች አስታወቁ!
በደቡብ አፍርካ ከሚኖሩ የህወሃት ቀንደኛ ደጋፊዎች መካከል ዋናዉና ግንባር ቀደሙ ሳሚ ብርሐን ሲሆን አጋሮቹ ወንደሰን አለሙ እና ደምሴ ( ፒተር ) በሚል ስም ይታወቃሉ።
ሳሚ ብርሐን ከግብረ አባሮቹ ጋር በ14.000.000 Rand አስራ አራት ሚሊዮን ራንድ የሚገመት ህገ ወጥ የንግድ እቃዎችን ሲያዘዋዉር በደቡብ አፍሪካ ኬፕተን ፓርክ የተባለ ስፍራ ከነ ሙሉ መጋዘኑ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ዉሎ የነበረ ሲሆን፤
በወቅቱ በወያኔ ሲኖዶስ የሚመራዉን የመድሐኒያለም ቤ/ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ከሚመሩ ቤተሰቦቹ ጋር በመመሳጠር የምእመናኑን ንብረት ለህገ ወጥ ንግድና ለመንቀሳቀሻ መጠቀሙን የሚያመልክቱ ማስረጃዎች ተይዘዉ ይገኛሉ።
ይህ ግለሰብ በኤርትራና በኢትዮጵያ ፓስፖርት የሚንቀሳቀስ ሲሆን የገድዩ እና ወንጀለኛዉን የህወሃት ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ በማገዝ ባስመሰከረዉ ማንነቱ ምክንያት ኢትዮጵያ ዉስጥ የወገኖቻችን ደም እንደጅረት በፈሰሰባት ቢሾፍቱ ወይም ደብረ ዘይት አካባቢ ትልቅ የብረታ ብረት ማቅለጫ እና ማምረች በመክፈት ለገዳዩ ህወሃት ቡድን የጦር መሳሪያ እና ጥይት ማምረቻ አቅርቦቶችን በመስጠት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ሳሚ ብርሐን እና ህወሃታዊያን የደቡብ አፍሪካ ዲያስፖራዎችን በመሰብሰባን በማስፈራራት እንዲሁም በማግባባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ትልቅ የንግድ መእከል ለመስራት በሚል ሰበብ ሁለት መቶ ሐምሳ ሚሊዮን ዶላር ተሰብስቦ በግለሰቦቹ የግል አካዉንት ዉስጥ እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን ገንዘቡ በህገ ወጥ የንግድ ሰበብ ወደ ዱባይ እና ቻይና ተልኮ ከዱባይ እና ከቻይና በእቃ ግዥ ተቀይሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚዘዋወርበት መንገድ እየተሰናዳ ሲገኝ የእቃ ግዢዉን በመፈጸምና በማከናወን የትግራይ ክልሉ መስፍን ኢንጂነሪንግ ከነሳሚ ብርሐን ጋር በፈጸመዉ ዉል መሰረት የሚከናወን ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የንግድ መአከሉን ለማስፈጸም በሚል ምክንያት በቢሊዮን የሚገመት ብር ለሳሚ ብርሀን እንደሚያበድር ቃል ተገብቶለታል።
ዉድ ወገኖቻችን ዛሬ በመላዉ ሐገራችን ላይ የሚኖሩ ወገኖቻችን በህወሃታዊያን ጥይት እየታደኑ ለመሞታቸዉ ምክንያት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከሚጠቀሱ የመሳሪያ ብረት አምራቾች መካከል ሳሚ ብርሐንና ወንደሰን አለሙን በጥብቅ እንድትከታተሉ እያሳሰብን የነዚህን ግለሰቦች ማንነት በምን አይነት የመኖሪያ ወረቀት እንደሚገለገሉ የት እንደሚኖሩ እና በፎቶ የተደገፈ ዝርዝራቸዉን እምናሰራጭ መሆኑን እናሳዉቃለን ።
( ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ )

No comments:

Post a Comment

wanted officials