Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 13, 2016

የኢትዮጵያ መንግስት ለኤምባሲዎችና አለም አቀፍ ተቋማት ሰለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብራሪያ መስጠቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ መንግስት ሰለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብራሪያ መስጠቱ ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009)
መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ኤምባሲዎችና አለም አቀፍ ተቋማት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ማብራሪያ መስጠቱ ታውቋል።
በተያዘው ሳምንት ሰኞ የአዋጁ መውጣት ስጋት ያሳደረባቸው እነዚሁ ተቋማት ለመንግስት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ምንጮች ለኢሳት ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር ውይይትን ያደረጉት አምባሳደሮች በአዋጁ አስፈላጊነት ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ታዬ አጽቀ-ስላሴ አዋጁ ተግባራዊ የተደረገው በሃገሪቱ ያሉ ችግሮችን ለመቆጣጠርና የጸጥታ ሃይሉን በአንድ እዝ ስር ለማደራጀት እንደሆነ ገልጸዋል።
አምሳሳደሮቹ ወደ ክልሎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴና በማህበራዊ ድረገጾች መዘጋትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ማቅረባቸውም ታውቋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials