በባህርዳር ዙሪያ ጢስ አባይ ሁለት የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገለጹ
ኢሳት (ጥቅምት 11 ፥ 2009)
በአማራ ክልል የባህር ዳር ዙሪያ ከተማ በሆነችው ጢስ አባይ በአንድ ጊዜያዊ ካምፕ ላይ ራሳቸውን ያደራጁ ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ሁለት የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገለጹ።
ሃሙስ ምሽት በወታደራዊ ጣቢያው ላይ የተቃጣውን ጥቃት ተከትሎ ወደ ጢስ አባይ ከተማ ተጨማሪ የመንግስት ታጣቂ ሃይል በመሰማራት ላይ መሆኑን ከዜና ጋር ቃለምልልስን ያደረጉ ምንጮች አስረድተዋል።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ወደ 30 የሚደርሱ ወታደሮች በስፍራው እንደነበሩ የተናገሩት ምንጮች ጥቃቱን ከፈጸሙት አካላት በኩል አንድ ታጣቂ ጉዳት እንደደረሰበት ተመልክቷል።
ራሳቸውን አደራጅተዋል የተባሉ ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ሁለት የአጋዚ ወታደሮች በጊዜያዊ ወታደራዊ ካምፑ ቅጥር ግቢ መቀበራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አስረድተዋል።
ሃሙስ ምሽት ለአንድ ሰዓት ያህል ጊዜ የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ያሉ የገዥው ስርዓት ሃይሎች ወደ ጢስ አባይ እንዲሰማሩ መደረጉም ታውቋል።
መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ገለሰቦች በእጃቸው የሚገኝ የጦር መሳሪያን እንዲያስረክቡ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።
ይሁንና በርካታ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች መንግስት ትጥቅ ለማስፈታት የያዘውን እቅድ በመቃወም መሳሪያቸውን አናስረክብም ሲሉ ቆይተዋል።
ከሃምሌ ወር ጀምሮ በአማራ ክልል የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተለያዩ ስፍራዎች በመንግስት ታጣቂ ሃይሎችና በታጠቁ ሃይሎች መካከል ግጭቶችን ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
በተያዘው ሳምንት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ ዋጅ በመቃወም ለሶስት ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ሲገልጹ ቆይተዋል።
ድርጊቱን ሲያስተባብሉ የቆዩ የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው በአድማው ተሳታፊ ነበሩ የተባሉ ወደ 30 አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከቀናት በፊት ይፋ አድርገዋል።

No comments:
Post a Comment