ደቡብ አፍሪካ ከዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት መውጣቷን አስታወቀች
#SouthAfrica #AUSummit #ICC2016 #VOAAmharic
የደቡብ አፍሪካ የፍትህ ሚኒስትር ሚካኤል ማሱታ ዛሬ ዐርብ በሰጡት ቃል ሀገራቸው የሮማውያንን ህግ ከሚተገብረው ፍርድ ቤት እንድትወጣ የሚያስችላትን ደንብ ለማጽደቅ ምክር ቤታቸው እንደሚወያይበት ገልጸዋል።
የደቡብ አፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት /አይ ሲ ሲ/ የመውጣት ውሳኔ ከዚህ ቀደም የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር አል-በሽር በአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመካፈል ደቡብ አፍሪካ በመሄዳቸው ምክንያት የተነሳውን ውዝግብ ያስታውሳል።
በዚህ የሮማው ህግ መሠረት፣ በሰው ልጅ ፍጡር ላይ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉት ፕሬዚደንት በሽር በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት /አይ ሲ ሲ/ ይፈለጉ ስለነበር፣ ደቡብ አፍሪካ ልታስራቸው በተገባ ነበር ማለት ነው፤ ፕሬዚደንት አል-በሽር ግን፣ ያን ክስ አስተባብለዋል።

No comments:
Post a Comment