Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 29, 2016

ጥይት ፋብሪካው ወደ እስር ቤት ተለወጠ

ጥይት ፋብሪካው ወደ እስር ቤት ተለወጠ

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአምቦ እና አካባቢዋ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሚታሰሩ ወጣቶች ቁጥር በመጨመሩ፣ ከአምቦ ወጣ ብሎ የሚገኘው የጥይት ፋብሪካ ወደ እስር ቤት መለወጡን ምንጮች ገልጸዋል።
በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በጥይት ፋብሪካው ግቢ ታስረው የሚገኙ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል።
በሌላ በኩል መንግስት የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎችን “በመሰብሰብ ህዝባዊ ተቃውሞው እንዲበርድ አስተዋጽኦ አድርጉ ፣ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ግን በተናጠል እርምጃ እንወስዳለን፣ መንገዶች የሚዘጋጉ ከሆነ አውሮፕላን እንጠቀማለን ” እያሉ በማስፈራራት ላይ መሆናቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
harar

አርበኞች ግንቦት በበርን ስዊዘርላንድ የተሳካ ህዝባዊ ውይይት አደረገ

አርበኞች ግንቦት በበርን ስዊዘርላንድ የተሳካ ህዝባዊ ውይይት አደረገ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው አመራር የሆኑት አርበኛ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው ፣ የኢሳት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የጀርመን ሃገር ቃል አቀባይ ሃይሉ ማሞ፥ ተቀማጭነታቸው በስዊዘርላንድ የሆኑ የሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የስዊዘርላንድ ከተሞችና ከሙኒክ ጀርመን ከተማ በመጡ ሃገርወዳድ ኢትዮጵያውያን በታደሙበት በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ውይይት ላይ የወቅቱ የሃገራችን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል እንቅስቃሴ ፣ ላለፉት 4 ወራት በመላው የኦሮሚያ ከተሞች እየተካሄደ ስላለውና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ የኦሮሞ ተማሪዎች፣መምህራና ሰራተኞች ክቡር ህይወት መጥፋትን ስላስከተለው የህዝብ እምቢተኝነት ፣ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ስለታሰበውና ርዝመቱ ክ 1600 ኪሎሜትር በላይ ስለሆነው መሬት ፣ የነፃነት ታጋዩ አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ወቅታዊ ሁኔታና የሱን ፈለግ ስለመከተልና ሰለሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የእለቱን ረዘም ያለ መርሃ ግብር የሸፈነው ተሰብሳቢዎች ካለምንም ገደብ ለአርበኛ ኤፍሬም ማዴቦ የንቅናቄያቸውን የፖለቲካ አካሄድና ፕሮግራም በተመለከተና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለሚሰነዘሩ ጥያቄዎች መልስ የሰጡበት ነበር።
ተሰብሳቢው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለሚሰነዘሩላቸው ጥያቄዎች በሙሉ ለሚሰጧቸው ማብራሪያዎችና ገለፃዎች እንዲሁም እራሳቸውም ከሌሎች የትግል ጓዶቻቸው ጋር በመሆን እየከፈሉት ላለው እልህ አስጨራሽ መስዋእትነት ያለውን አክብሮት ገልፆ፤ የሞቀ ቤታቸውን፣ ልጆቻቸውንና ቤተሰባቸውን ትተው በርሃ ለወረዱ የነፃነት ታጋዮች የአብረናችሁ ነን መልእክት እንዲያደርሱላቸውም ጠይቀዋል።
ማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ ካለሴቶች ተሳትፎ እውን እንደማይሆን ሁሉ ፣ ላለፉት በርካታ አመታት በስዊዘርላንድ ውስጥ በሚካሄዱ ህዝባዊ ተሳትፎዎች ከፍተኛ አስተዋፅ ላደረጉ ሴቶች የዝግጅቱ መሪዎች ያዘጋጁላቸውን የምስክር ወረቀት ከአርበኛ ኤፍሬም ማዴቦ እጅ ተቀብለዋል።
በመጨረሻም ለነፃነት ታጋዩ አንዳርጋቸው ፅጌ 61ኛ አመት የልደት በአል የተዘጋጀውን ኬክ የትግል አጋራቸው አርበኛ ኤፍሬም ማዴቦና በስዊዘርላንድ ከ3 አስርት በላይ የሰብአዊ መብት ታጋይ በሆኑት ወይዘሮ መሰረት ሃይሌ በጋራ በመቁረስ ፥ በአቶ አንዳርጋቸው የተደረሰውን የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል መዝሙር በመዘርመር ፥ እንዲሁም ለዝግጅቱ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ወገኖች በማስመስገን ተፈጽሟል።


በአዲስ አበባ የሚካሄደው የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ እንደቀጠለ ነው



የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 
የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አሽከርካሪዎች ጥፋት ሲያጠፉ ፈቃዳቸውን እስከመሰረዝ የሚያደርሰውን ከበድ ያለ ቅጣት የያዘውን ህገደንብ በመቃወም በአ/አ ከተማ የተጀመረው የታክሲ ማቆም አድማ የቀጠለ ሲሆን ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ታክሲ በመጠበቅ ላይ የነበረው ህዝብ ሆን ብሎ መንገዶችን በመዝጋት፣ ሌሎች የግል፣የንግድና የመንግስት ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲታወክ በማድረግ ተቃውሞውን ተቀላቅሏል።
ተቃውሞውን ተከትሎ የመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ደንቡ አሁን ተፈጻሚ እንደማይሆንና ከሶስት ወራት በሁዋላ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢገልጽም፣ አሽከርካሪዎች መግለጫውን ባለመቀበል ተቃውሞአቸውን ቀጥለዋል።
የታክሲ እጥረቱን ተከትሎ የመንግስት መስሪያ ቤት መኪኖች በትእዛዝ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።ይህም ሆኖ በርካታ የመንግስትና የግል ድርጅት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ መገኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።
በሜክሲኮ፣ በቄራና አየር ጤና አካባቢዎች ህዝቡ መንገድ በመዝጋት ጭምር ተቃውሞውን አሳይቶአል።በአውቶቡስ ተራ፣ አድማውን ወደ ጎን በማለት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መኪኖች ተሰባብረዋል።በአየር ጤና የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ተቃውሞ ለማሰማት ሲንቀሳቀሱ በፖሊሶች ተበትነዋል።ተመሳሳይ ተቃውሞ በአውቶቡስ ተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ተጀምሮ፣ ፖሊሶች በአካባቢው ደርሰው ተቆጣጥረውታል። የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ ሌሎች ዜጎችንም አካትቶ ወደ አጠቃላይ የመብት ጥያቄ እንዲሸጋገር የሚጠይቁ ጽሁፎች በብዛት እየተበተኑ ነው።
የታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች እንዲሁም አድማውን የሚመራው አስተባባሪ ኮሚቴ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ በመጀመሪያው ቀን ውጤታማ ሆኗል ብለዋል ። በአሽከርካሪዎችና በህዝቡ መካከል ያለውን የመንፈስ አንድነትም አድንቀዋል።
ደህንነቶችና ትራፊክ ፖሊሶች በጋራ በመሆን መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ታክሲዎች ታርጋ ሲፈቱ አርፍደዋል። በአዲስ አበባ አጎራባች ቀበሌዎች የሚሰሩ ” ኦሮ” የሚል ታርጋ የተለጠፈባቸው በኦሮምያ ክልል ብቻ እንዲሰሩ የተፈቀደላቸው ታክሲዎች፣ ችግሩን ለመቅረፍ በሚል ወደ መሃል አዲስ አበባ ገብተው እንዲሰሩ ቢፈቀድላቸውም፣ ከህዝቡ የሚወሰድባቸውን እርምጃ በመፍራት እና አድማውንም በመደገፍ ብዙዎቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የአዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮች መብት አስከባሪ ኮሚቴ ከሰዓት በሁዋላ ባወጣው መግለጫ ” መንግስት ታርጋ እንፈታለን፣ ሾፌሮችን እና ባለንብረቶችን እናስራለን” በማለት የሚያሰማው ዛቻ እና ማስፈራሪያ መፍትሄ ሊሆን የማይችል መሆኑን ገልጿል። ህጉን ለሶስት ወራት እናዘገያለን የሚለው ማታለያ ተቀባይነት እንደሌለውና መንግስት በአስቸኳይ ህጉን ሙሉ በሙሉ በአዋጅ ካልሻረና ያለአገባብ ንሮ የሚገኘውን የነዳጅ ዋጋ ከአለም ገበያ ዋጋ ጋር ካለስተካከለ ፣ የስራ ማቆም አድማው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አስጠንቅቋል። በአገሪቱ ያሉ ሹፌሮች አድማውን እንደሚቀላቀሉ ፣ መንግስት ፍትሃዊ ጥያቄውን በሃይል ለማፈን ከሞከረ ከስራ ማቆም አድማ አልፈው በመኪኖቻቸው መንገዶችን በመዝጋት ማንኛውንም የተሽከርከሪዎች እንቅስቃሴ ለማገት መዘጋጀታቸውንም በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በመላው አገሪቱ የሚደረጉ ተቃውሞዎች በአይነትና በስፋት እየጨመሩ ሲሆን፣ በኦሮምያ፣ በአማራና አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ያሉት ተቃውሞዎች፣ የህዝቡን አጠቃላይ የለውጥ ፍላጎት እንደሚያመለክቱ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። በኦሮምያ የሚካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት የተቃውሞው አንድ ምክንያት ነው የተባለውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንደሰረዘው ሁሉ፣ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ተቃውሞአቸውን ከቀጠሉ መንግስት ይህንን ደንብም ሊሰርዘው ይችላል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
በተመሳሳይ ዜና በአዲስ አበባ የሚታየው የነዳጅ እጥረት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ። ከዚህም በላይ ባለ ታክሲዎች የትራፊክ ፖሊሶች በሚወስዱት እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ ሲማረሩ መቆየታቸው ተቃውሞውን ለማስነሳት አንድ ምክንያት ሆኗል።

በኦሮምያ ተከታታይ ተቃውሞዎች እንደሚቀጥሉ ከያካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል

በኦሮምያ ተከታታይ ተቃውሞዎች እንደሚቀጥሉ ከያካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 
ገዢው ፓርቲ የአጋዚ ወታደሮችን በየቦታው አሰማርቶ ግድያና እስሩን አጠንክሮ ቢቀጥልም፣ በሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችን ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። በተለይ የሻኪሶ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የጉጂ ዞን አካባቢዎች ጠንካራ ተቃውሞች እንደሚካሄዱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በቦረና ዞንም እንዲሁ ተቃውሞዎች እንደሚቀጥሉ የአካባቢዎች ነዋሪዎች ተናግረዋል። በምእራብ ሃረርጌ ዛሬም የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሄድ ውሎአል።
በጉጂ እና በቦረና ዞኖች ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታስረዋል። ብዙዎችም የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ሲሉ ጫካ ገብተዋል። ይሁን እንጅ የተለያዩ የማህበረሰቡ አባላት ባደረጉት ውይይት ተቃውሞአቸውን አጠናክረው እንደሚገፉበት ስምምነት ላይ ደረሰዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የፍርሃት ድባብ መኖሩን ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።
ክልሉ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ባነገቡ ወታደሮች እና ተሽከርካሪዎች ተሞልቷል። በየአካባቢው የሚካሄደው ተከታታይ ፍተሻ እና እንግልት ነዋሪውን በእጅጉ አስመርሯል።
“በምሽት ብትወጣ ፣ ፖሊስ ያስርሃል። ወረቀቶችህንና ስልክን ይፈትሻሉ። ከተቃውሞው ጋር የተያያዙ ፎቶዎች ከተገኙብህ ከፍተኛ ችግር ላይ ትወድቃለህ። ” ሲል አንድ የጊንጪ ወጣት ለኤ ኤፍ ፒ ተናግሯል። ሌላ እናት ደግሞ “ለልጆቼ እፈራለሁ። ሌሊት መተኛት አቁሜአለሁ። ኑሮአችን ሲኦል ሆኗል። ህይወት ትርጉም አጥቷል። ” ማለታቸውን የዜና ድርጅቱ ዘግቧል። በአምቦ አንዳንድ ሱቆች ቢከፈቱም፣ ትምርትቤቶችና ሆስፒታሎች ካለፉት 3 ወራት ጀምረው እንደተዘጉ ነው።
ኤፍ ፒ ያነጋገረው አንድ የባንክ ሰራተኞች ፣ በአምቦ “የፖሊስ ቁጥር ከኮብልስቶን ቁጥር ይበልጣል” ብለዋል።
የሁለት ልጆች እናት የሆኑ ሴት፣ እነዚህ ወታደሮች የእኛን ቋንቋ አይናገሩም። ከእነሱ ጋር መግባባት አልቻልም። የእነሱ ብቸኛ ቋንቋ የጦር መሳሪያቸው ነው” ብለዋል።
በኦሮምያ የሚደርሰው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆም የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች በጋራ በመሆን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ደብዳቤ ጽፈዋል። ድርጅቶቹ በጋራ በጻፉት ደብዳቤ በኦሮምያና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚወሰደው የሃይል እርምጃ እንዲቆም፣ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እንዲሁም ተቃውሞ ሲያሰሙ የታሰሩት በሙሉ እንዲፈቱ፣ የተፈጸሙትን ግድያዎች የሚመረምር ነጻና ገለልተኛ መርማሪ አካል እንዲወቋቋም፤ ሰብአዊ መብቶችን በመጣስ የሚወነጁ ባለስልጣት አለማቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ፍርድ ቤት እንዲዳኙ ጠይዋል።
ጥያቄውን በጋራ ያቀረቡት የሰብአዊ መብት ማህበር በኢትዮጵያ፣ ሲቪከስ፣ ሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ፣ ዲፌንድ ዲፌንደርስ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክት፣ ፍሮንት ላይን ዲፌንደር፣ ሂውማን ራይትስ ወች እንዲሁም አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ፌዴሬሽን ናቸው።
አሜሪካ፣ ኖርዌይና እንግሊዝ ዜጎቻቸው ወደ ተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቀዋል።
የእንግሊዝ መንግስት ዜጎቹ ወደ ዝዋይ፣ አዳሚ ቱሉ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ ሰራሮ፣ ኮፈሌ፣ ዶዶላ፣ ኮኮሳ ወረዳ እና ላንጋኖ እንዳይጓዙ ሲያስጠነቅቅ፣ የአሜሪካ መንግስት ደግሞ ዜጎቹ በሻሸመኔ ሞጆ መንገድና አምቦ መንገድ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።

ኢሳትበሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ያሳፈረ ተሽከርካሪ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት ደረሰበት

በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ያሳፈረ ተሽከርካሪ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት ደረሰበት




(የካቲት 15 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ ወታደሮች አሳፍሮ በደቡባዊ ሶማሊያ ይጓዝ የነበረ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት እንደደረሰበት የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘገቡ።
ሊጎ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው የቦንብ አደጋ በርቀት መቆጣጠሪያ የተቀነባበረ መሆኑና በተሽከርካሪው ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱን ራዲዮ ሸበሌ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አስደምጧል።
በወታደራዊ ተሽከርካሪው ላይ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎም በኢትዮጵያ ወታደሮችና በአልሻባብ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንም የራዲዮ ጣቢያው አመልክቷል።
ይሁንና በሁለቱም ወገኖች ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ መረጃ አለመገኘቱን ያስታወቀው የራዲዮ ጣቢያው አልሻባብም ሆነ የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ሃይል በጉዳዩ ላይ ምላሽን ከመስጠት መቆጠባቸውን አክሎ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት በተናጠል በአልሻባብ ታጣቂ ሃይል ላይ እየወሰደ ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማጠናከር ሲል በቅርቡ ተጨማሪ አንድ ሺ ወታደሮችን ወደሶማሊያ ማሰማራቱ ይታወሳል።
ይኸው ወታደራዊ ሃይል በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ሶማሊያ በአልሻባብ ቁጥጥር ስር ያሉ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ውጊያን እያካሄደ እንደሚገኝ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ይገልጻሉ።
ኢትዮጵያ ከአራት ሺ በላይ የሆኑ ወታደሮችን በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ስር አሰማርታ ብትገኝም ቁጥሩ ይፋ ያልሆነ የተናጥል ወታደርን በማሰማራት ከአልሻባብ ጋር ውጊያን እያካሄደች ትገኛለች።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአምስት ሃገራት የተውጣጡ ከ20 በላይ ሰላም አስከባሪዎች በሶማሊያ የሚገኙ ሲሆን፣ ታጣቂ ሃይሉ ግን አሁንም ድረስ የሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ሆኖ ይገኛል።

Sunday, February 28, 2016

በአዲስ‬ አበባ ላይ የስራ ማቆም አድማ ተጠራ።



በአዲስ‬ አበባ ላይ የስራ ማቆም አድማ ተጠራ።
በአዲስ አበባ  ላይ የሚገኙ ታክሲዎች ኮድ 1 እና 3 እንዲሁም ሀይገር ባሶችን በዋናነት የተጠራ ቢሆንም ሌሎችንም አሽከርካሪዎች ያካተተ ከሰኞ የሚጀምር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቶዋል።
አዲሱን የትራንስፖርት ህግ በመቃወም የስራ ማቆም አድማው የተጠራ ሲሆን በሁሉም አቅጣጫ ለሚንቀሳቀሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መልዕክቱ በበራሪ ወረቀት ተበትኖ እንዲደርስ ተደርጎዋል። በተጨማሪም በአለም ገበያ ላይ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ቢታይም በኢትዮጵያ ግን ይሄ ነው የሚባል ቅናሽ አልተደረገም የሚል ጥያቄም አብሮ ተነስቶዋል።

ኢንስፔክተር ተስፉ የተሰኘ የፌደራል ፖሊስ ጦር መሪ በርካታ አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዞ ከሁመራ ስርዓቱን ከዳ፡፡



ኢንስፔክተር ተስፉ የተሰኘ የፌደራል ፖሊስ ጦር መሪ በርካታ አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዞ ከሁመራ ስርዓቱን ከዳ፡፡
ኢንስፔክተር ተስፉ ሁመራ እና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው ፌደራል ፖሊስ መሪ፣ ለህወሓት ታማኝ እና ጠንካራ ከሚባሉት ቀዳሚው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የካቲት 19 2008 ዓ.ም የሚመራቸውን በርካታ አባላት ከነሙሉ ትጠቃቸው ይዞ ሁመራ ከሚገኝ ጦር ግንባር ጠፍቷል፡፡
የኢንስፔክተር ተስፉን እና በርካታ ተከታዮቹ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላትን መጥፋት ተከትሎ ህወሓት ጎዳናዎችን በጦር ዘግቶ ወጥሯል፤ ከፍተኛ አሰሳም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ኢንስፔክተር ተስፉና ተከታዮቹ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፡፡ አገዛዙ እነ ኢንስፔክተር ተስፉ ወደ ኤርትራ ተሻግረው ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶችን እንደተቀላቀሉ ያምናል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ተባለ

የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ተባለ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንዳሉት በተለያዩ የውስጥ ችግሮች ተወጥሮ የሚገኘው ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው። በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በአካባቢው በሚገኙ የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችም እነዚህን ነጻ አውጭዎች ለመቀላቀል ድንበር አቋርጠው እየተጓዙ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የኢህአዴግ መንግስት፣ በኤርትራ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመክፈት ወታደራዊ ልምምዶችንና ዘግጅቶችን በማድረግ ላይ ነው። ሰሞኑን በኦሮምያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ሲሉ አቶ ሃይለማርያም መናገራቸው ይታወሳል። ምንም እንኳ የተፈለገውን ያክል የሰው ሃይል ባይገኝም፣ ኢህአዴግ መንግስት ሁለተኛ ዙር ወታደራዊ ምልመላ ለመጀመር ማስታወቂያዎችን በየቦታው ለጥፏል። መከለከያ ሰራዊቱ በከፍተኛ ሁኔታ በዘር ተከፋፍሎ በሚገኝበት በዚህ ወቀት ፣ በኤርትራ ላይ ጥቃት መፈጸም፣ የኢህአዴግን ፍጻሜ ያፋጥነዋል በማለት ምንጮች አስተያየታቸውን አስፍረዋል። በኢትዮጵያ በኩል የሚደረገውን የጦር ዝግጅት በተመለከተ የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።

ነፃነት በነፃ አይገኝም

አድ አዳማ ከኖርወይ (Add Adama from Norway).
በዚህ በአለንበት አለም ብዙ ነገሮች ነፃ ተብለው ሲታድሉ አይተን ይሆናል ነገር ግን ያ ነፃ የተባለው ነገር በፍፁም በነፃ የተገኘ አይድለም ቢያንስ እሱን ለማምረት የተከፈለ ዋጋ አለ። ስለዚህ ሁል ግዜ ነፃ የሚለውን ስንሰማ ከዛ በፊት የተከፈለ ዋጋ እንዳለ ማሰብ አለብን። ነፃነት ማለት ደሞ እስኪገኝ ድረስ የተወሰነ ትውልድን ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ከተገኘ በሗላ ደሞ በደንብ ለሚጠብቀው ማሕበረሰብ በሰላምና በፍቅር እያኖረ የሚያቆ ታላቅና ልዩ ሀይል ነው። ነፃነትን ማግኘት ደሞ የሚቻለው በአንተ ላይ እንዲሆን የማትፈልገውን ነገር በሌላ ላይ ሳታድረግና መብትን ለማስከበር የማይመችህን ነገር በሙሉ ከፊትህ ስታስወገድ ነው።በአሁኑ ሰአት ለኦሮሞ ሕዝብ የማይመቸው ነገር ቢንሮር ኢዲሞክራሲያዊ የሆነው የTPLF አገዛዝ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ይህ ከዚህ በፊት የተጠቀሰውን ነፃነት ለማምጣት ቆርጦ ተነስቶ በመላው ኦሮሚያ ባዶ እጁን በጭካኔያቸው ወድር ከሌላቸው የአጋዚ ወታደሮች ጋር ለአፉት 3 ወራቶች ተፋጧል አሁንም እየተፋጠጠ ነው ።
Oromo
በአሁን ሰአዓት መላው የኦሮሞ ሕዝብ ለነፃነቱ እየታገለ ያለው የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ዋጋዎች እየከፈለ ነው። ዛሬ በየትኛውም የስራ መስክ ያለ ኦሮሞ በልዩ ክትትል ስር ወድቁዋል, ይህ ልዩ ክትትል ግን ተቁዋሞውን አልገታው ይልቁንም አባሰው እንጂ። ዛሬ ለአቅመ አዳም የደረሱ ኦሮሞች እንደወጉ እንደባህላቸው ሆ ብለው ጨፍረው መጋባት የጥይት ውርጅብኝ ያስወርድባቸዋል። ታድያ በሰርጋችን ላይ ሰው ሞቶብናል ብለው ሐዘን አይደለም የተቀመጡት ይልቁንም ወቅቱ የሐዘን ሳይሆን የትግልነው ብለው ሬሳ ይዘው ቀጥታ ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ነው የተመሙት። ከየመስርያ ቤቱ ተመንጥረው ሲባረሩ፣ሲፈናቀለ እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሐገሪቷ ውስጥ ሕግና ስርዓት የለም በማለት ሕዝባዊ ተቁዋሞውን ነው የተቀላቀሉት። ያለምን ጥፋት እስርቤት በሚባለ የስቃይ ቦታ ተሰቃይተው ከወጡ በሗላ ወያኔዎች እንደሚሉት ልክ ገብተው ቁጭ አይደለም የሚሉት እንደውም አንድ በምዕራብ አርሲ የሚኖሩ አቶ በዳሶ የተባሉ ግለሰብ በቪኦኤ ትዝታ የሻሸመኔውን ተቃውሞ ለሚዲያ ስለተናገሩ ችግር ይደርስቦት ይሆን ብላ ስትጠይቃቸው “ችግርማ የልመድኩት ነው። ሰው ገላውን እታጠበ ሌላው ውሀውን ቢጨምርበት ሌል ምን የተለየ ነገር ይመጣበታል። ሕይወቴን በእስር ቤት ያሳለፍኩ ስለሆነ የፈለገው ቢመጣ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ሀቅ ከመናገር ወደሗላ አልልም” ሲሉ በማያወላዳ ሁኔታ መልሰዉላታል(ማዳመጥ ለምትፈልጉ ይህን ሊንክ ክፈቱ http://amharic.voanews.com/content/america-norway-england-issue-travel-warning-to-oromia-region/3195461.html)።ይህ ከላይ የተጠቀሰው ሁሉ ደሞ የሆነው የተለየ ሀፂያት ሰርተው ሳይሆን ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ነው ።ሌላው የሚደንቀው ነገር በአጋዚ ጥይት ተመተው ለመሞት የሚያጣጥሩት ውድ የኦሮሞ ልጆች የመጨረሻ ቃላቸው ታጋይ ይወድቃል ትግሉ ግን ይቀጥላል የሚል የጀግንነት ትምህርት ነው።
በአጋዚ ጥይት ሞት፣ በአጋዚ ጥይት መቁሰል፣ከስራ ገበታ መፈናቀል፣ የውሸት ፕሮፓጋንዳና ክሶችና የመሳሰሉት ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ትግልን ወደፊት ይገፋው ይሆናል እንጂ ፈፅሞ እንደማያቆመው የኦሮሞ ሕዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለወያኔዎች ነግሯቸዋል። ከዚህ በሗል የሐጎስ ጌትነት እና የጫላ ሎሌነት አክትሞዋል በማለት በማያሻማ መልኩ እየነገራቸው ይገኛል። ታዲያ ታላላቅ ውሽቶችን በመናገር የሚታወቀው የመንግስት አፈ ቀላጤው አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ሐቅ መዋጥ እየተናነቀው ሲያሻው በኦሮሚያውስጥ የተነሳውን ተቃውሞ ተቆጣጥረነዋል፣ ሲያሻ ደሞ ተቃዉሞው በሌሎች ብሔር ላይ ያተኮረ ነው፣ ሲያሻው ደሞ ተቃዉሞው እምነት ተኮር ነው፣ ሲያሻው ደሞ ተቃዉሞው የሚመራው በታጠቁ ጋንጎች ነው እያለ ደጋግሞ ሲቀባጥር ይሰማል። ለኔ እንደሚገባኝ ከሆነ ይህ የአቶ ጌታቸው አባባል አንድም ከቀቢፀ ተስፋነት የተነሳ ይሚመልሱት አልያም የፈለኩትን ብልስ ሚዲያው ያለው በጄ ነው የኢትዮዽያ ህዝብ ያለምንም አማራጭ እኔ ነው የሚያዳምጠው በሚል ይመስላል። ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ ለአቶ ጌታቸው ረዳና መሰሎቻቸው የሚለው ነገር ቢንሮ ይህ አላስፈላጊ መዘላበድ ፈፅሞ አያዋጣም። በአሁኑ ሰዓት የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነቱን ለመጎናፀፍ የሚያስፈልገውን መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው። በሆኑም ዛሬ በተንሹ የተጀመሩት እርምጃዎች እንደ እስረኛ ማስፈታት፣ መንገድ መዝጋት፣የኦሮሞ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ የተዝጋጁ ወታደራዊ ተቁዋማትን ማቃጠል፣ በኢንቨስትመንት ሰበብ በግፍ የተወሰዱ የእርሻ መሬት ማቃጠል ከመሳሰሉት አልፎ ወደ ተባብሰው ቀውስ ከመገባቱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የህዝቡ ጥያቄ ቅንጣት ታህል ሳትሸራረፍ መመለስ አለበት።
ዛሬም የኦሮሞ ህዝብ ትግል ብቻውን የትም አይድርስም የሚሉ አካሎች አሉ። ምናልባት የሌላው ሕዝብ አሁን መነሳት ትግሉን ያፋጥነውና ለወያኔ መከራዋን ይጨምርባት ይሆናል ።ይህ ማለት የኦሮሞ ሕዝብ ትግሎን አቁዋርጦ ሌላው እስኪነሳ መጠበቅ አለበት ማለት ደሞ አይደለም። እናም ሌላው ሕዝብ ተነሳም አልተነሳም ልክ ከዚህ በፊት እንደፃፍኩት ትግሉ ይቆማል የሚቆመውም ከድል በሗላ ብቻ ነው። ከመቼውም በላይ ነፃነት በነፃ እንደማይገኝ አውቆ ህፃን አዋቂ ተማሪ ገበሬ ሳይል ሁሉም የኦሮሞ ሕዝብ አስፈላጊውን መስዋእትነት እየከፈለ ይገኛል። ሰላማዊ ትግሉም እያደገ በአሁኑ ወቅት ቀላላል የሚባሉ እርምጃ መውሰድ ደረጃ ላይ ደርስዋል። እርምጃውም እንደ አስፈላጊነቱ ወያኔ እጅዋን እስክትሰጥ ድረስ ያድጋል ይቀጥል።ነፃነት በነፃ ስለማይገኝ መሬት ላይ ቁጭ ብላችሁ የተጀመረ ትግልን ከመተቸት ተቆጠቡ ወይ ደሞ እናንተም ታገሉ እላለሁ ።
የዘወትር ፀሎቴ ፈጣሪ የማይቀረውን ድል ያፍጥንልን!!!

የጭቆናው ምክንያት አንባገነናዊ ሥርዓት ወይንስ የብሄር ልዩነት ይገረም አለሙ

Woyanes shoud face justiceወያኔ በተናጠልም ሆነ በቡድን  በዜጎች ላይ የሚፈጽማቸውን  ድርጊቶች አስመልክቶ  የበደሉ ተጠቂዎችም ሆኑ ለተጠቁት ድምጽ የሚያሰሙ ወገኖች  በደሉ የተፈጸመው  አማራ ስለሆን/ኑ ነው ኦሮሞ ስለሆን/ኑ ነው ወዘተ በማለት በደሉን በብሄራቸው ምክንያት  የተፈጸመ አድርገው  ሲገልጹ ይሰማል፡፡ የሚፈጸሙት የግፍ ድርጊቶች  በተጠቂዎቹ ላይ የሚፈጥሩት ስሜት እንዲህ ሊያናግሩ ይችላሉ፡፡ በምክንያት ወደ ውጤት የሚጓዙ ሳይሆን በስሜት ህዝብ ማነሳሳት ላይ ለሚያተኩሩ ወገኖችም  ይህ አገላለጽ ቀላል መሳሪያ ነው፡፡ ዜጎች በብሄራቸው አስተሳሰብ ታጥረው የእርስ በርስ ልዩነታቸው ሲሰፋ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወገኖችም  ይህን አገላለጽ ይፈልጉታል፤ያራቡታል፡፡ ነገር ግን ሰከን ብለን ካየነው አገላለጹ የነገሩን ትክክለኛ ገጽታ የሚያሳይ  ለመፍትሄም የሚበጅ አይደለም፡፡
ጠለቅ ያለ  መመርመር ሳያስፈልግ በቅርብ ያሉና በግልጽ የሚታዩ ነገሮችን ብቻ በጥሞና መመልከት ብንችል እኔ ወይንም አኛ እንዲህ የሆነው ይሄ ይሄ በደል የተፈጸመብን በብሄራችን ምክንያት ነው ( አማራ ኦሮሞ ጉራጌ ወዘተ በመሆናችን ነው) ሲባል ይህ በደል ያልነካቸው  የብሄሩ አባላትን መዘንጋት ይሆናል፡፡ የጥቃቱ መነሻ ምክንያቱም ሆነ መድረሻ ግቡ ብሄር ተኮር ከሆነ ከተዘመተበት ብር መካከል መስፈርት እያወጣ የሚመርጠው አይኖርም፡፡ በእኛ ዘንድ የሚታየው አጥቂዎቹም ተጠቂዎቹም ከሁሉም ብሄር መሆናቸው ነው፡፡
ከየብሄሩ ከወያኔ በላይ ወያኔ ለመሆን የሚዳዳቸውና በብሄራቸው አባላት ላይ በደል የሚፈጽሙ፤በእኔ ካልደረሰ በማለት ካለው  ተስማምተው የሚኖሩ፤ጎመን በጤና ብለው ህሊናቸው እየቆሰለ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል አይነት የሚኖሩ ወዘተ ብዙ አጅግ ብዙ አሉ፡፡ ታዲያ የተበደልነው  አማራ/ኦሮሞ ወዘተ በመሆናችን  ነው ብለን ጅምላ ካደረግነው  የእነዚህ ወገኖች ጉዳይ  ምን ሊባል ነው፡፡ መቼም የብሄር ማንነነታቸውን መካድም መንሳትም አይቻልም፡፡ በመሆኑም ይህን ብቻ በማየት የበደል ጥቃቱ መሰረተ ምክንያት   የብሄረሰብ ማንነት  ሳይሆን የገዢዎች ጸረ ዴሞክራሲያዊነትና  የተጠቂው ዴሞክራሲ ናፋቂነት ነው ማለት ይቻላል፡፡
ስለዚህ የበደሉ ምክንያት የዚህ ወይንም የዛኛው ብሄረሰብ አባል መሆን ሳይሆን  እኔ ሰው  ነኝ ማለት  ነው፤  እኔ ሰው ነኝ የሚል ሰው  ሎሌነትን  ይጸየፋል ፤ ነጻነቱን ይሻል፤ በጠመንጃ ሳይሆን በህግ መተዳደርን ይፈልጋል፤ በድምጹ የሚመርጠውን መንግሥት ማየት ወዘተ ይመኛል፡፡ እነዚህ ሁሉ  ቢሟሉ ደግሞ  አንባገነኖች በሥልጣን ላይ ውለው ማደር አንደማይችሉ ስለሚያውቁ  ተግባራዊ አየደርጓቸውም፡፡ እንደውም ሰው ነኝ የሚል ሰው የሚያቀርባቸው ጥያቄዎቸም ሆኑ ምኞት ፍላጎቶች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መሆናቸው ይቀርና  የስልጣን ጥያቄ ተደርገው በአንባገነኖች እየተተረጎሙ  ለጥቃት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ሁሉም ዜጋ እኔ ሰው ነኝ ማለቱንና ሰው በመሆኑ ሊኖሩት የሚገቡትን መብቶቹን  ትቶና ረስቶ አቤት ወዴት ብሎ ቢያድር ወያኔን ከነምናምኑ ተቀብሎ ቢኖር  የሚፈጸም ጥቃት ቀርቶ በደል አይኖርም፡፡ ስለሆነም እንግዲህ በዜጎችና በገዢዎች መካከል ያለው  መሰረታዊ ልዩነትም ሆነ  የጥቃት በደሉ ምክንያት የብሄር ማንነት ሳይሆን አንበገነናዊ አገዛዝ  ነው ማለት ይቻላል፡
ከላይ በተገለጸው የዜጎችና የአንባገነኖች መሰረታዊ ልዩነትና የበደል ጥቃት ምክንያት መስማማት ከቻልን የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ሊኖረው የሚገባው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች  በብሄረሰብ ልዩነት ምክንያት የሚለያዩ አይደሉም፡፡ አንዱ ብሄረሰብ ከሌላው ተለይቶ ለእኔ ብቻ የሚገባኝ ብሎ ሊያነሳቸው የሚችሉ ጥያቄዎችም ሆኑ የሚሻቸው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያሉ አይመስለኝም፡፡ሰለሆነም ልዩነቱ አንባገነንነትና አልገዛም ባይነት ነው፡፡መፍትሄው ደግሞ የአንባገነኖችን በደል በብሄረስብ እየሸነሸንን የየራሳችንን መልክና ቅርጽ እየሰጠን ከመከፋፈል ተላቀን  ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት መቻል ነው፡፡
ኢትዮጵያችንን በዴሞክራሲያዊ ጽኑ መሰረት ላይ የቆመ መንግስት ባለቤት ማድረግ ቢቻል  የሁሉም  ልጆቿ የሰው ልጆች ሰው በመሆናቸው ብቻ የሚኖራቸው  ከልካይ አንጂ ሰጪ  የሌለው  መብታቸው፣ የዜግነት ክብራቸው፣የብሄር ማንነታቸው፣ እምነት አመለካከታቸው ወዘተ በእኩልነት የረጋገጣል፡፡ እነዚህ መብቶች ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ አባል በመሆን አለመሆን በመደገፍ በመቃወም ወዘተ ልዩነት ሳይደረግ በህዝብ ንቁ ተሳትፎና ይሁንታ ተግባራዊ የሚሆነውን ህገ መንግሥት አክብረው ለሚኖሩ ዜጎች ሁሉ በእኩል ተፈጻሚ ስለሚሆኑ በዜጎችና በመንግሥት መካከል የሚፈጠር መሰራታዊ ልዩነት አይኖርም፡፡ አበው ሰው በሀገሩ ቢበላ ሳር ቢበላ መቅመቆ ይከበር የለም ውይ ሰውነቱ ታውቆ ይሉት የነበረውም ያኔ እውን ይሆናል፡፡
አንድ ሁለት ተጨባጭ ጉዳዮቸን በመጠኑ አንመልከት
አማራው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሀገሬ ብሎ ሲኖር ለጥቃት ተጋልጧል በክልሉም በወያኔ ጥቃት እየደረሰበት ነው ስለዚህ መደራጀት አለበት ሲባል አንሰማለን፡ የተደራጁም አሉ፡፡በተለያዩ ክልሎች ይኖሩ በነበሩ ወገኖቻችን ላይ ጥቃት የተፈጸመው አማራ በመሆናቸው ነው ብሎ ለመቀበል የሚቸግረው እነዚህ ወገኖቻችን በዛ አካባቢ መኖር የጀመሩት ከብዙ አመታት በፊት በመሆኑ ጉዳዩ አማራነታቸው ከሆነ እስከ ዛሬ አንዴት በሰላም ኖሩ የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ነው፡፡ መኖር ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ከሚኖሩ ሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ተጋብተዋል ተዋልደዋል በተለያዩ ማህበራዊ ግንኑነቶች ተሳስረዋል፡፡
ስለሆነም ነገሩን በወገኖቻችን ለይ የደረሰው በደል ከፈጠረብን ስሜት ሰከን ብለን ካየነው ችግሩ አማራነታቸው ሳይሆን የአንባገነኖች እርስ በእርስ እያጋጩ የሥልጣን ዘመንን የማራዘም እኩይ ሴራ ውጤት ነው፡፡  እነዚህ ወገኖች እኔ ሰው ነኝ ሳይሉ ተገዢነትን አሜን ብለው በወያኔ አገልጋዮች በኩል ለወያኔ እየገበሩ መስለው ተመሳስለው ቢኖሩ እንደማይነኩ ይገመታል፡፡ ስለሆነም ችግሩ የተፈጠረው በአማራነታችን/ቸው ነው ሲባል ይህን የወያኔ እኩይ ተግባር ማለምለም ይሆናል፡፡
አማራው በሚኖርበት ክልልም እየተበደለ መሆኑ አነጋጋሪ አይደለም፡፡ ይህም  አንደኛ ከላይ ለማየት አንደተሞከረው እኔ ሰው ነኝ በሚሉት ላይ አንጂ በሁሉም አማራ ላይ ባለመሆኑ፤ በወያኔ አገዛዝ ስር ባሉ ሁሉም ክልሎች የሚፈጸም በመሆኑ  እንዲሁም የበደሉ ፈጻሚዎች የወያኔ አገልጋይ አማሮች በመሆናቸው የበደሉ ምክንያት አማራነት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡
በኦሮሞዎችም ላይ የሚፈጸመው በደል የዚሁ ተመሳሳይ ነው፡፡ ለሰሞነኛው ያላባራው ተቃውሞ ምክንያት የሆነውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ብንመለከት ኦሮሞን ለማፈናቀል ባህሉን ቋንቋውን ላማጥፋት በኦሮሞ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው የሚለው ትክክል አይመስለኝም፡ ምክንያቱም አንደኛ  አጋጣሚ ሆኖ አዲስ አበባ በኦሮምያ ክልል መገኘቷ አንጂ በአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆነ አቅጣጫ ሌላ ተጎራባች ክልል ቢኖር ማስተር ፕላኑ ሁሉንም ነበር የሚነካው፤ ስለሆነም ጉዳዩ  የወያኔ የመስፋፋትና መሬት የመቀራመት  እንጂ በተለየ ኦሮሞን የማጥቃት አይደለም፡፡ ሁለተኛም  እስካሁን በአዲስ አበባም ሆነ በአካባቢው  የተፈጸመው ማፈናቀል የቦታውን መፈለግ አንጂ በቦታው ላይ  የሚገኙ ዜጎችን ብሄረሰብ ማንነት መሰረት ያደረገ አይደለም፡፡ በሶስተኛ ደረጃም የድርጊቱ ዋና አስፈጻሚዎች ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ ኦሮሞ በኦሮሞ ላይ የሚፈጽመው ጥቃት ብሄርን ምክንያት ያደረገ ሊባል አይችልም፡፡
ስለሆነም የችግሩ  ምንነትም  ሆነ የጥቃቱ ምክንያት አንበገነናዊ ሥርአት አንጂ የተጠቂዎች ብሄር ማንነት አይደለም፡፡ መፍትሄውም ጥቃቱን በየብሄር እየለያዩ መለያየት ሳይሆን በጋራ ትግል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መብቃት ነው፡፡

Saturday, February 27, 2016

ኃይለማርያም ደሳለኝ በቴሌቭዥን ቀርቦ በሕዝቡ ላይ ዛተ

harar
ከግርማ ካሳ
ሕዝቡ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ነው ያቀረበው። ሕገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት፣ ህዝቡ በሰላም ድምጹን አሰማ። ዜጎች ባነሱት ጥያቄ ልንስማማ፣ ላንስማማ እንችላለን ። ሆኖም ማንም ዜጋ የመሰለውን መናገርና መቃወም ይችላል። ህዝቡ ያደረገውም ይሄንኑ ነው።
ሆኖም የአጋዚ ጦር ሕዝቡን ጨፈጨፈ። ሕጻናት፣ አረጋዉያን ሴቶች፣ ወንዶች፣ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች ሁሉም እንደ ቅጠል በጥይት ረገፉ።
አጋዚ የፈጸመው ወንጀል የተደበቀ አይደለም። ፎቶዎችንና ቪዲዮዎች እያየን ነው። የሟች ቤተሰቦችን ድምጽ እየሰማን ነው። መረጃው፣ ሁሉም ነገር አለ።
ሆኖም ሃይለማርያም ደሳለኝ የሕዝቡን ጥያቄ አራክሶ፣ “የማይደገም ትምህርት እንሰጣለን” እያለ በመዛት ለሕዝብ ያለውን እጅግ በጣም ትልቅ ንቀት ማሳየቱን መርጧል። ከሕዝቡ ጎን ከመቆም፣ለህዝብ ከመቆርቆር፣ እነ ሳሞራን አሁን በቃቹህ ከማለት፣ እነ ሳሞራ ለፈጸሙት ወንጀል የክብር ሜዳሊያ እያጠለቀላቸው ነው። “ጎሽ ጥሩ አደረጋችሁ” እያላቸው ነው።
ኃይለማሪያም አይኖቹ የሚያዩ፣ አይምሮ የሚያስብ ከሆነ ፣ ትንሽ በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ ይመረመር ዘንድ፣ ተቃዉሞ የተነሳባቸውን ቦታዎች እንደሚከተለው ላቀርብለት ወደድኩ። እንቅስቃሴ የተደረገባቸው ቦታዎችን በቀይ ተከበዋል። (ካገኘሁት መጠነኛ መረጃ በመነሳር)
በኦሮሚያ ወደ 20 ዞኖች አሉ። የጂማ ልዩ ዞን፣ የጂማ ዞን፣ የኢሊባቡር ዞን፣ የቀለም ወለጋ ዞን፣ የምእራብ ወለጋ ዞን፣ የምስራቅ ወለጋ ዞን፣ የሁሩ ጉዱሩ ዞን፣ የአዳማ ልዩ ዞን፣ የቡራዪ ልዩ ዞን፣ የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የሰሜን ሸዋ ዞን፣ የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የምእራብ ሸዋ ዞን፣ የአርሲ ዞን፣ የምእራብ አርሲ ዞን፣ የምስራቅ ሃረርጌ ዞን፣ የምእራብ ሃረርጌ ዞን፣ የባሌ ዞን፣ የጉጂ ዞንን የቦረና ዞን ናቸው።
• በጉጂ ፣ በምእራብ ሃረርጌ ፣ በምእራብ አርሲ፣ በምእራብ ወለጋ፣ በምስራቅ ወለጋ ፣ በቀለም ወለጋ ፣ በአጠቃላይ በስድስት ዞኖች ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ተቃዉሞ ተነስቷል።
• በምስራቅ ሃረርጌ፣ ከሃረር በስተምእራብ ባለው ቦታ፣ በአርሲ ወደ ታች ወረድ ብሎ፣ በጂማ ዞን በስተምእራብ ደቡብ በሸቤ ሳምቦ፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን ወደ ታች ወርዶ ምእራብ አርሲ ዞን አዋሳኝ ላይ በሚገኙት በቡልቡላና አዳሚ ቱሉ አካባቢ፣ ምእራብ ሸዋ ዞንን በሚያዋስኑ የሰሜን ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች፣ ወሊሶን ጨምሮ ግማሽ በሚሆነው የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ ባጠቃላይ በጥቂት ይሁን በከፊል በሌሎች አራት ዞኖች ተቃውሞ ተነስቷል።
• እርግጥ ነው ከቡልቡላ፣ አዳሜ ቱሉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ አሉ ከሚባሉት ትላልቅ ከተሞች ከአንድ እስከ አምስት ከሚጠቀሱት ዉስጥ ( አዳማና ቢሾፍቱ) በሚገኙባቸው የአዳማ ልዩ ዛን እና በምስራቅ ሸዋ ዞን ብዙ እንቅስቃሴ አልታየም። እንደ ጂማ፣ አሰላ ባሉ ከተሞችም እንደዚሁ። በኢሊባቡር ዞን እንደ ሌሎች ዞኖች ብዙ የሚታይ እንቅስቃሴ የለም። ሆኖም እንቅስቃሴው የመዛመት ባህሪ ስላለው ተቃዉሞ በሌለባቸው ቦታዎች ያለው ህዝብም መብቱን ነጻነቱ የተነፈገ በመሆኑ፣ በማንኛውም ጊዜ ሊንቀሳቀስም ይችላል። ይንቀሳቀሳልም።
እንግዲህ ኃይለማሪያም ይሄንን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅን የሕዝብን እምቢተኝነት ነው፣ በሚቆጣጠረው ሜዲያ እያሳነሰ ያቀረበው።
የሚያዙት ሕወሃቶች ነገ ያስጡልኛል፣ ወይንም ሸሽተው ወደ ትግራይ ሲሄዱ እዚያ ያስጠልሉኛል ብሎ አስቦ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። ተጠቅመዉበት እንደ ታኘከ ማስቲካ ነው የሚተፉት። በአደባባይ ለተናገራቸውም ነዋራ ንግግሮች ምላሽ በሕዝብ ፊት ይሰጣል።
ያመረረና በቃኝ ያለ ህዝብ የሚፈለገውን ካለገኘ ወደኋላ አይልም። እነ ኃይለማርያም የሚበጃቸው ሰላምን መፈለግ ነበር። የሚበጃቸው የሕዝብን ጥያቄ አክብሮ ብሄራው እርቅ እንዲመጣ ነገሮች ማመቻቸት ነበር። እንግዲህ እንደ እንስሳ ማሰብ ከፈለጉና ከሕዝብ ጋር መላተም ከመረጡ መንገዱን ጭርቅ ያድርግላችው ከማለት ውጭ የምንለው የለንም። እኛ መክረናል። አስጠንቅቀናል። እንደ ጲላጦስ እጆቻችንንም ታጥበናል።

የኢህአዴግ የተበሉበት 7 ሙዶች


ከአቡ ባይሳeprdf
1. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ ጥቅሙን የሚጎዳ ነገር አልቀበልም በማለት ተቃውሞ ካነሳ ትምክተኛ ሲባል፤ ኢህአዴግ የህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነገር በግድ ካልተቀበላችሁ ብሎ ሙጭጭ ካለ ግን የዓላማ ፅናት ነው::
2. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ በኢህአዴግ ላይ ቁጣ ሲያስነሳ ሽፍታ ሲባል፤ ኢህአዴግ ቁጣውን ለማብረድ ንፁሃንን ሲገድል ግን የማያዳግም እርምጃ ነው።
3. በኢትዮጵያ፣ ጋዜጠኛ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቸ ወይም ከተቃወመ አሸባሪ ሲባል፤ ጋዜጠኛ ሆኖ ኢህአዴግን ከደገፈ ግን ልማታዊ ጋዜጠኛ ነው::
4. በኢትዮጵያ፣ ኦሮሞ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቃወመ ኦነግ፣ አማራ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቃወመ ደግሞ ግንቦት ሰባት ሲባል፤ ኢህአዴግ ህዝቡን ሲቃወም ግን መንግስት ነው::
5. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ የኢህአዴግን ወታደር ሲገድል ሽፍታ ጋኔን ሲባል፤ የኢህአዴግ ወታደሮች ህዝቡን ሲገድሉ ግን ፀጥታ ለማስፈን ነው::
6. በኢትዮጵያ፣ ጥፋተኞች ተብለው ነገርግን ያለምንም ጥፋት ከኢህአዴግ ጋር ፍርድ ቤት የቆሙ በሙሉ ሲፈረድባቸው፤ ኢህአዴግ ግን ጥፋተኛም ሆኖ ይፈረድለታል
በኢትዮጵያ፣ ህዝብ “ዴሞክራሲ መሰረታዊ ነገር ነው” ሲል፤ ኢህአዴግ ግን ” ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው::
7. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ ሲሳሳት ኢህዴግ ለምን ተሳሳተ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል ፤ ኢህአዴግ ሲሳሳት ግን ” ከኢህአዴግ ስተት ከብረት ዝገት አይጠፋም……… ” በማለት የተበላበት ሙድ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመያዝ ይሞክራል………………።

በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ – ጣስው አሰፋ




የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016  3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤  2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር  3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት  አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ አበበ የተዋንያኑ አመራረጥ የተዋጣለት ስለ  መሆኑ ያለኝን አድናቆት ልገልጽለት እወዳለሁ፤ እነሱም ለዚህ መልካም ተግባር ዝግጁ ሆነው መገኘታ
“…የዲያሰፖራው ሃይል፤ ውጭ ያለው ሃይል ውጭ ነው ያለው  እንግዲህ ምከንያቱን የመለየቱ ጉዳይ የሚጠበቅብን ነው። እንዴት ነው? አሁን ደጋፊ ነን? መሪ ነን? የሚለው ጉዳይ እንግዲህ አገር ውስጥ ያለውን ትግል የሚመራው እዚያ ያለ ሃይል ነው፤ እዚያ ያለ ሕዝብ መሆን አለበት። እኛ ወይ ገብተን እዚያ መታገል አለብን ወይ ደግሞ ከፍተኛ የድጋፍ አስተወ ጽኦዋችንን መቀጠል አለብን። በሪ ሞት ኮንትሮል ትግል መምራት እንደማይቻልም ታይቷል እሱን ባን ቃጣም…” ስርዝ የኔ
                   ዶ/ር በያን አሶቦ
ቸው የሚያስመሰግን ነው።
እኔ ታዲያ ያንን ሰፊ ውይይት ለመተቸት የተነሳሁ አይደለሁም፤ ሀሳብ ልሰጥበት በርዕሰ ስላስቀመጥኩት ጉዳይ መዳረሻ የሚሆነኝን ያህል ብቻ ቀንጨብ አድርጌ  ለመያዝ ነው።
አስተናጋጁ  ለሁሉም ያቀረበው የጋራ ጥያቄ ፤ “ባሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችንን እያበሳጨ ያለው በጣም በየጊዜው የተደረገ ነገር ነው፤ አዲስ ነገር አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ለሁለትና ለሶስት ወር የቆየ ሊቆም  ያልቻለ ማባሪያ የሌለው ግድያ ባገዛዙ በተለይ በኦሮሞ ክፍለሃገር የተለያየ አካባቢ ወገኖቻችን እየተገደሉ፤ እየታሰሩ፤ እየተፈናቀሉ ነው የሚገኙትና እንዴት ነው የተከታተላችሁትና የህብረተሰቡስ ጥያቄ፤ ያለውን ሁኔታ በእናንተ ዕይታ እንዴት ነው ያያችሁት?”  የሚል ሲሆን፤ ተጠያቂዎቹን ተራ በማስያዝ መልስ እንዲሰጡ አደረገ። ዶ/ር በያን ጀመሩ፤ ዶ/ር አረጋዊ ቀጠሉ አቶ ተክሌ የሻው አሳረጉ።
ተጠያቂዎች የቀረበላቸውን ጥያቄ ሲያስተናግዱ የኔ ከሚሏቸው የየግል የልብ ቁስሎች እየቆነጣጠሩ የጨመሯቸው ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም፤ በጊዜው የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተማሪ ወጣቶች ላነሱት ጥያቄ  የማስተር ፐላኑ እንደምክንያት ሆነ እንጂ፤ የወያኔ አገዛዝ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲፈጽም የኖረው የተከማቸ በደል ብሶት ጋኑ ሞልቶ መፍሰሱን የሚያሳይ ምልክት ነው ነው በማለት ነበር ሶስቱም ባንድ ቃል ያሰመሩበት። ከዚህ በሁዋላም በኦሮሚያ ክፍለ-ሃገር – ክፍለ ሃገር የምለው እኔ ነኝ፤ ምከንያቱም በልጅነቴ በከብት ጥበቃ (እረኝነት) ስራ ተሰማርቼ ስሰራ  ክልል የሚለውን ቃል ሲጠቀሙበት የማውቀው ለከብት ግጦሽ የሚውል የሳር መሬት ሲከለልበት ስለነበር፤ ዛሬ ወያኔ በከብት ምትክ ሰውን መከለያ ማድረጉ ስላልተመቸኝ ነው። – በሰፈነው እንቅስቃሴ ላይ ብዙ አልቆዩበትም። ከዚያ ይልቅ በመልስ አሰጣጡ ሂደት ጊዜ  በአቶ ተክሌ የሻው ለመድረኩ እንግዳ የሚመስል “እንቅስቃሴውን ኢትዮጵያዊ መልክ እንስጠው” የሚል  ሃሳብ ተነስቶ ስለነበር፤ እሱን የመልሱ አካል ሆኖ እንዲዋሃድ ለማለማመድ  የተደረገው ውይይት ሰፋ አለና ተሳታፊዎቹን ባላሰቡት ጊዜና ፍጥነት ወደሌላ የውይይት ነጥብ ማለትም የሃገሪቱ መከራና ስቃይ ምንጭ የሆነው አጥፊ የወያኔ ሥርዓትን  አደብ ማስያዝ ስለሚቻልበት የትግል ጥያቄ ጉዳይ አሸጋገራቸውና በዚያ ላይ ላደረጉት ውይይት ሰፊውን ጊዜ ሰጡት።

ብሎም ይህ ጸረ-ወያኔውን ትግል ማዕከል ያደረገው ውይይት በመጠናቀቂያው አካባቢ፤ ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ፤ ሃቻምና፤ አምና፤ ዘንደሮ፤ ተናትም ዛሬም፤ እየተነሳ የሚጣለው የህብረት ትግል አስፈላጊነት  በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው! ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ጉዳዩን ለማፋጠን ድርጅት ከድርጅት ጋር ለምሳሌ ኦዴኤፍ ከሸንጎ ጋር፤ ሞረሽ ወገኔ እንዲሁ ከሸንጎ ጋር ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተበስሯል። በዚህ መሃል ግን  ዶ/ር በያን – መድረኩ ሳይበርም ቢሆን፤ ልብ ብላችሁ ቨዲዎውን አዳምጡት ልክ ዲያስፖራውን ዞር ዞር ብለው የሚቃኙ ይመስላል – ለመሆኑ እኛ ማንነን? የትና ምንስ ለማድረግ ነው ሕብረት የምንፈጥረው በሚል መንፈስ የቃኙትንና የኔንም ቀልብ የሳበውን  ከዚህ ጽሁፍ አናት አካባቢ በአራት ማዕዘን ማዕቀፍ ውሰጥ ያስቀመጥኳትን ሃሳብ የወረወሩት፤ ሌሎቹ ተሳታፊዎች ልብ ብለዋት ይሁን አይሁን ለጊዜው መረጃ ባይኖረኝም፤ ሃሳቧ ወደፊት በሚፈጠረው ሕብረት ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ትጫወታለች ብዬ አስባለሁ፤ መጫወትም አለባት፤  የዚያን ጊዜ እንጠብቃት፤

ሶስቱም የውይይት ተሳታፊዎች አበክረው የዘከሩለት የትግል ዓይነት የሰላማዊ ትግል/ሕዝባዊ እምቢተኛነት መሆኑ ግልጽ የሆነውን ያህል፤ ይህ ህዝባዊ እምቢትኝት እንዴት ነው የሚገለጠው? የትስ ነው የሚካሄደው? ሲሉ በያን ያነሱትን ጥያቄ ለማጠናከር ዕውነትም ብለን፤ ለናሙና ያህል ጥቂቶቹን ብናነሳ፤- ስትራይክ፤ ቦይኮት፤ ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፤ አግባብ የልሆኑ ህጎችን አለመቀበል የመሳሰሉትንና ባሁኑ ጊዜም ዛሬ በኦረሚያ ክፍለሃር፤ በጎንደር አካባቢ  የሚጫጫሰውን ዓይነት  መሪ የሌለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ መስመር አሲዞ፤ በእቅድና በጥበብ እንዲራመድ ለማድረግ፤ እንደገና በያን እንዳሉት በሪሞት ኮንተሮል  እንደማይቻል ማን ነው አሌ የሚል?

ትብብር  ትብብር! ትብብር! ትብብር! ይህ ቃል የወሬ ወፈጮዋችን እሰኪሟልጥ ከርትፈነዋል፤ ሰልቀነዋል፤ አልመነዋል ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ባህል ሆኖናል ብል የተሳሳተ ግምት አይሆንብኝም። ከፍ ብሎ በተደረገው ውይይት ላይም ተነስቶ ሲወራ ቀደም ሲል ተደርገው ስለነበሩ ህብረቶችም በዶ/ር አረጋዊ በርሄ “የተሞከሩ ህብረቶች ነበሩ” በሚል መነሳታቸውን  አዳምጫለሁ። ይህንን እኔም አረጋግጣለሁ፤ ነበሩ። ነገር ግን ታዲያ እንዲሁ ነበሩ ብሎ ማለፉ ስላልተመቸኝ የሚከተለውን ላክልበት ሞክሬአለሁ፤

ካልተሳሳትኩ ወያኔ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ብቻ በተቃዋሚነት የተፈጠሩትንና ነበሩ የተባሉትን ትብብሮች በዝርዝር ላስቀምጣቸው፤ የመጀመሪያው የአማራጭ ሃይሎች ምክር ቤት፤ ሁለተኛው/ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድህ)፤ ሶስተኛው/ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ሕብረት (ኢድሃህ)፤ አራተኛው/ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ (ቅንጅት)፤ የሚባሉት ናቸው። ስለያንዳንዳቸው የሚክተልውን ላስታወስ፤

አማራጭ ሃይሎች ምክር ቤት፤- ይህ ምከር ቤት የተቋቋመው ከጅምሩ ለማቋቋም ታስቦ ሳይሆን፤ በሀገርቤትና እውጭ ባሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር ኢህአዴግን ጨምሮ በሃገር ቤት እንዲደረግ  የተዘጋጀ የሰላምና እርቅ ጉባኤ  ወያኔ አሻፈረኝ ቢልም ጉባዔው ተደርጎ ሲጠናቀቅ በአጋጣሚ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ወያኔው የሱ በጉባዔው አለመሰታፍ ብቻ ሳይሆን፤ በጉባዔው ለመካፈል  ከውጭ ሰዎች እንዲገቡ ከፈቀደ በኋላ ሀገር ሲደርሱ ማሰር ጀመረ፤ በመንገድ ላይ የነበርው ጉዞወን አቋርጦ ተመለሰ፤ ይህ የወያኔ ድርጊት በሃገር ቤቱና በውጭው ባለው ሃይል በኩል ጉባኤው እኛ ካልተካፈልንበት መደረግ የለበትም የሚል ሃሳብ ተነሳና ካከራከረ በዃላ በወግ የተጣሉና እርቅ የሚሹ ሰዎች ባለመገኘታቸው ጉባኤው የእርቅና የሰላም መሆኑ ቀርቶ ድርጅት ማቋቋሚያ ሆነና አማራጭ ሃይሎች ምክር ቤትን አምጦ ወለደ። ከዚያ በኋላ በውጭውና በሃገር ቤት የነበረው ግንኙነት ሻከረና ቀልብ ያለው ግንኙነት ሳይሰፍን ሰነባበተና፤ በመሃሉ ሌላ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድህ) የሚለው ድርጅት የማቋቋም ሂደት ተጀመረ።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድህ)፦ ይህ ስብስብ ልዩ የሚያደርጉት ሁለት ጥሩ ነገሮች ነበሩት፤ አንደኛ/ እስከዚህ ጊዜ ድርስ አንዱ ወያኔ እንደምክንያት እያደርገ ነገር ያቆረፍድበት የነበረ ጉዳይ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በመካክላቸው ጦረኞች አሉባችው፤ ሰላማዊ አይድሉም እያለ የሚወነጅለብት ምክንያት ጦረኞቹ ለሰላም ባላቸው ፍቅር ከወያኔ ጋር ያግባባን ነበር የሚሉትን የመሳሪያ ቋንቋ እርግፍ አድርገው የተውበትና ለወያኔ የሰላም እጃቸውን የዘረጉበት ጊዜ ሲሆን፤ በሌላው በኩል ደግሞ ይህ ስብስብ አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረውና የት ይደርሳል የተባለም ነበር። ታዲያ ምን ይሆናል ይህም ስብስብ “የማያድግ ልጅ … እንትን ይበዛዋል” እንዲሉ፤ ችግር የገጠመው ምስረታው በተጠናቀቀ በማግስቱ ነበር። የተፈጸሙት ነገሮች አስገራሚም፤ አሳፋሪም ነበሩ፤ መጥፎ ሽታ ስላላቸው እዚህ አይነሱም እንጂ፤ ሆኖም ይህ ስብስብ ከተቋቋመ በኋላ ያንን ጉባኤ አዝጋጅቶ በነበረው “ሰላም ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ የምርምርና የተግባር ቡድን” (Research and Action Group for Peace in Ethiopia and Horn of Africa)” በተባለው ደርጅት ድጋፍ አማካይነት ወደሃገር ቤት የሚተላለፍ ቀስተዳመና የሚል ራዲዎ ፕሮግራም ነበር። ይህም ሊሆን የቻለው ቀደም ብዬ እንደጠቆምኩት ስብስቡ ክነበረው ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ የተነሳ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ሕብረት (ኢድሃህ)፤  ይህ ስብስብ 15 የፖለቲካ ድርጅቶችን አቅፎ የተቋቋመ ሲሆን፤ ከነዚህ 15 ድርጅቶች ውስጥ 10ሩ ከውጭ፤ 5ቱ ከሃገር ቤት የነበሩ፤ የዚያን ያህል ብዛት ያለው የፖለቲካ ድርጅት አሰባስቦ የያዘ ስብስብ እስከዛሬ ታይቶ አይታወቅም። እዚህ ስብስብ ላይ ጥኢት ልቆይበት፤ የስብስቡ አመራር ሃገር ቤት የተደረገ ሲሆን፤ ይኸው አመራር በውጭ የሚገኙት አባል ድርጅቶቹ  በሃገር ውስጥ ተቋቁመው እንደማንኛቸውም በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በህጋዊነት ተመዝግበው እንዲንቀሳቀሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመነጋገር እንዲያመቻች ይደረጋል፤ በዚህም መሰረት ሁኔታው በመንግሥት በኩል አዎንታዊ መልስ ያገኘ መሆኑን ገልጾ፤ በውጭ ያሉት አባል ድርጅቶቹ ወደሃገርቤት ገብተው ህጋዊ ሰውነት አግኝተው አብረው በህብረት እንዲነቀሳቀሱ መልክት ያደርሳል፤ የውጭየዎች „ፍንከች ያባ ቢላዎ ልጅ“  አሉ። ምናልባት እውጭ ካሉት በአመራር ላይ የሚገኙና በመነግስት በኩል በቂ መተማመኛ የሌላቸው ቢሆኑ እንኳን፤ የግድ የነሱን ወደሃገር መግበት ሳያስፈልግ፤ ሃገር ውስጥ ባሉ አባሎቻቸው አማካይነት ሊመዘገቡ እንደሚችሉ ሁሉ ከሃገር ቤቱ በኩል ሃሳብ ይቀርብ ነበር። ቆየና ከሃገር ቤቱ ሃይል ውስጥ ካ5ቱ ሁለቱ ህብረቱን ትተው ወጥተው ቅንጅትን ይፈጥራሉ፤ እንዲያ እንዲያ እያለ የግንቦት 1997 ዓ.ምህረቱ የአቶ መለስ „ዕንከን የለሽ“ – በዃላ ላይ „ዕውር ሲቀናጣ በትሩን ጥሎ ፍለጋ ይሄዳል“ እንደሚባለው የሆነበት –  ምርጫ ይደርስና፤ ምርጫው ይደረግና፤ ወያኔ በምርጫ ይሸነፍና፤ አሸናፊዎቹ በአሸናፊነት ወንጀል ተከሰው በተሸናፊ ወያኔ ፊት ለፍርድ ይቀርቡና፤ የተሰጣቸው ፍርድ ከአንገት መድፋት ወይም አንገት ቀና አድርጎ ቃሊቲ ከመግባት መምረጥ ነበር፤ – እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባ ነገር የተሰጠው አማራጭ ነጻና ፍትሃዊ አይሁን እንጂ ዴሞክራቲክ ነበር – ከፍርድ በሁዋላ ስለሆነው መቀጠል  አሰልቺ ስለሚሆን፤ እሱን አልፌ ከዘረዘርኳቸው ስብስቦች ሂደቶች ምን እንማራለን ወደሚለው ተሻግሬ ጠቅለል ያለ ሃሳቤን ላስፍር፤

ምን እንማራለ? የማወራው ለውጭው ሃይል እንደሆነ አይዘንጋ፤ ምንም እንኳን አንዱ ከሌላው ለየት የሚልበት የራሱ ገጽታ ቢኖርም፤ ሁሉም ከሃገር ቤቱ ሃይል ጋር ከሞላ ጎደል ግለጽ በሆነ መነገድ በመገናኘት  በጋራ ይሰሩ ነበር። ሁሉም የዲያሰፖራው ድጋፍ ነበራቸው፤ በወጤትም በኩል ቢሆን፤ የሚመዘነው ወያኔን ከቤተ-መንግስት አውጥቶ በመጣል ብቻ ነው ካልተባለ በስተቀር፤ በ1997 ምርጫ ከቅንጅት ቀጥሎ ብዙ መቀመጫዎችን ያገኘው ህብረቱ እንደነበረ አይዘነጋም። ያም ሆኖ ደግሞ የውጭው ሃይል ህብረቱ በተቋቋመ ጊዜ አመችውን ሁኔታ ተጠቅሞ ወደሀገር ገብቶ/በሀገር ውስጥ ተተክሎ ትግሉን አለመቀላቀሉ ትልቅ ጥቁር ነጥብ መሆኑን መዘንጋት አይገባም፤ ለምን ለሚለውም ጥያቄ አንድም መልስ የሰጠ የለም። ሕዝብም „እንግዳ ሳይመጣ ሁሉ ሴት“ እንዲሉ በውጭ ያሉት የራሳችን የሚሉት በሀገር ውስጥ መሰረት የሌላቸው፤ ወይም ቢኖራቸውም ውጭ ባለውና አገር ውስጥ ባለው ሃይላቸው መካከል መተማመን ባለመኖር ይሆናል የሚል መላ ምቱን አዚሞ ነው የቀረው። እድሉ ግን አምልጧል። አንባቢ የራሱን ሃሳብ ይስጥበት፤ እንደኔ ግን  ወደፊት  በውጭ  ያሉ ድርጅቶች ከሁኔታዎቹ ብዙ ሊማሩባቸው የሚችሉ ነገሮች ስላሉ ነገ እኔን አንዱ ወይም ሌላው ሁኔታ ቢገጥመኝ እንዴት ነው የማስተናግደው ብሎ ለማሰብ ይረዳዋል ብዬ አምናለሁ። በመጨረሻም ታዲያ ከዚህ በላይ ያመላከትኳቸው በውጭና በግቢ መካከል የነበሩ ግንኙነቶች ከ1997 በዃላ ተቋርጠው ቀርተዋል፤ ለምን? ለዚህ ጥያቄ የዚያን ጊዜ በኢትዮጵያ  የነበረውን ሁኔታ ከዚያ ወዲህ ካለው ጋር ማገናዘብ ለሚችል ሁሉ በቀላሉ መልሱን ማግኘት የችላል። ከሁሉም እጅ ይጠበቃል፤ ይህንን እዚህ ላይ ሸብ ላድርግና በአዲስ ድምጽ ራዲዎ በሶስቱ የድርጅት ተወካዮች ቀን የማይሰጠው ተግባር በመባል ውይይት ወተደረገበት፤ ከአድማጭ ጋር በተደረገ ጥያቄና መልስ ዳብሮ፤ የተግባራዊነቱን ከፍተኛ ሃላፊነትም አዋያዩንና ተዋያዮቹን ተሸካሚ አድርጎ፤ ወደተጠናቀቀውና የብዙዎችን የልብ ትርታ ወዳናረው፤ የአጣዳፊው ትብብር ጥያቄ ልለፍ፤

በውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሳው አጣዳፊው ትብብር፤- ይህ ትብብር ተቃዋሚዎች የሚቃወሙትን ሃይል በሚገባ አውቀው የሚያቅዱት፤ የሚተልሙት፤ የሚቋጠሩት የሚፈቱት እርምጃ ሁሉ በዚያ ሃይል ላይ እንጥፍጣፊም እንኳን ቢሆን ተጽእኖ ለማሳደር የሚችል መሆን አለመሆኑኑን በማመዛዘን የተቀናጀ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል። ሌላው  ከዚህ ተለይቶ የማይታየው ጉዳይ ደግሞ፤ የሚፈጠረው ትብብር ምንም ያህል ቅንጅቱ ቢያምር፤ መተማመን ከሌለ፤ ጊዜው የሚባክነው በውስጥ ፍትጊያ ስለሚሆን፤ አመርቂ ስራ ለመፈጸም አይቻልም። ለመተማመን ደግሞ ልዩነት ይታይባቸዋል የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ አፍረጥርጦ በማውጣት፤ በማይፈልጉትና በሚፈልጉት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይገባል፤ ለዚህ አሰራር ጠቃሚ ይሆናሉ በማለት ካለኝ ልምድ ተነስቼ  በቅድሚያ ሊጤኑ ይገባል የምላቸውን አካሄዶች እንደሚቀጥለው ለማቅረብ ሞክሬአለሁ፤ የትግሉ መነሻ በደልን መቃ
ወም ነው። በደል ደግሞ አድራጊና ፈጣሪ አለው። ዛሬ በሃገራችን በደል ፈጻሚ ነው የተባለውና ሕዝብ የሚማረርበት አንድ መጥፎ ስርዓት አለ። ታዲያም ይህ ሥርአት የሚጠራበት ስም ብቻ ሳይሆን፤ የሥርዓቱ አራማጅም ስም ሳይቀር አደናቃፊ ሚና ይኖራቸዋል የምላቸውን እንደሚከተለው አቅርቤያቸዋለሁ፤

1ኛ/ የሥርዓቱ መጠሪያ፤- አንዱ አፋኝ አምባ ገነን ሥርዓት ነው  ሲለው፤ ሌላኛው  ዘረኛ ሥርዓት ነው  ይለዋል። በጉዳዩ ብዙ የማይጨነቅ ሰው ታዲያ፤ ኤዲያ! ያንንም አልከው ያንን ሁሉም ጸረ-ዴሞክራሲ ነው ተወኝ በማለት ሊሸኘው ይሞክራል። ነገሩ ግን እንደሱ አይደለም። በሁለቱ መካከል ትልቅ ልዩነት አለና።

ካጭሩ እንጀምር፤- – ዘረኛ ሥርዓት በተፈጥሮው  ጸረ-ዴሞክራቲክ ነው።
– ጸረ-ዴሞክራቲክ ሥርዓት ሁሉ ግን ዘረኛ አይደለም። ይህ ዋናና የመጀመሪያው ልዩነት ሆኖ፤ ከሁለቱ ስርዓቶች ጋር የሚደረገውም የትግል ግብ-ግብ የተለያየ ነው። አጠር አጠር እያደረግሁ ሌሎች ልዩነቶችንም ላመላክት፤

ድርድረ፤- በአምባገንን ስርዓቶቸና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል የሚደረገው ትንቅንቅ ከሁለቱ አንዳቸውንም            በአሸናፊነት የሚያወጣቸው ሆኖ ሲያገኙትና መውጫ ሲያጡ፤ ወይም በሌላ ምክንያት ወደርድር መጥተው ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ይሆናል። ድርድር አድራጊዎቹ ማንኛቸውም ቢሆኑ የሚያገኙት ድርድሩ ያስገኘላቸውን እንጂ፤ የሚፈልጉትን እንደማያገኙ አውቀውም ነው ወደድርድር የሚመጡት፤ በተለመደው አነጋገርም ሰጥቶ መቀበል በሚለው መርህ መመራትም ማለት ነው።

ከዘረኛ ስርዓት ጋር ግን ለመደራደር እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም ከላይ እንዳልኩት ድርድር ሰጥቶ መቀበልን ስለሚጠይቅ፤ ዘረኝነት ይሕንን መርህ በስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል አይደለም። ከዘረኝነቱ ይህን ያህሉን ልተውልህ ይህን ያህሉን ተውልኝ አይባልም። ምክንያቱም ዘረኝነት ወደር የማይገኘለት አገርና ሕዝብ የሚያጠፋ በሽታ በመሆኑ ከምድረ ገጽ መጥፋት ያለበት ስለሆነ ነው – መናለባት ተግደዶ ይደራደር ይሆናል ቢባል እንኩዋን፤ የሚሰጠው እንጂ ምንም የሚቀበለው ነገር ስለማይኖር፤ ትልቅ የባልሞት ባይ ተጋዳይነት ጥፋት ከማድረስ ስለማይቆጠብ አስቸጋሪነቱን ልመገመት የሚቻል አይደለም። – ለድርድር አይመችም የምለው፤ አንድ ዘረኛ ድረጅት መቆሚያውና የጀርባ አጥንቱ ዘረኝነቱ ነው። ያ ከተነካበት ፈረሰ ማለት ነው። ስለዚህም ነው መለስ ዜናዊ  በ2002ቱ ምርጫ ጊዜ የራሱን ጋዜጠኞች ሰብስቦ ጠይቁኝ በማለት ባደረገው ድራማ ላይ እንዴት ነው ስልጣን መካፈል ስለሚባለው ምን አስተያየት አለህ ተብሎ ሲጠየቅ “ይህ ማለት እኮ የኔ ፐሮግራም ስራ ላይ እንዳይውል መደናቀፍ ማለት ነው። እኔ እንደዚሕ ያለውን አላደርግም። ከተሸነፍኩ ጥየ መሄድ ብቻ ነው።” ሲል መልስ የሰጠው። ከሰወየው ሳልርቅ የኢትዮጵያ ገዢ ሆኖ እያለ እሱ አላኮራውም። “ትግሬ ወርቅ ነው ከዚህ ዘር በመወለዴ እኮራለሁ” ነበር ያለው። ይህን  ማነው የጤና ነው ብሎ የሚወስደው? ይህ ሰው እኮ ለምሳሌ እናቱ ወይም አባቱ አንደኛቸው ከወላይታው፤ ከኦሮሞው፤ ወይም ከጉራጌው ወዘተ… – ከአማራው መቸም አይሞከርም – ቢሆኑ ኖሮ አጋም ስር እንደበቀለ ቁልቋል ሲያለቅስ የኖረ ይሆን ነበር ማለት ነው።  እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን “ወርቅ” የሚሏት ቃል በጌጥነቷ ብቻ ሳይሆን እንደተጠቃሚው ሌላም  የምትታወቅበት ሙያ ስላላት ግጭት እነዳትፈጥረ ነው። በመጨረሻም እንግዲህ ከሁለቱ ስሞች በየትኛው ስም የሚጠራውን ነው የምንታገለው የሚለውን ማሰብ ግድ ይላል፤ ስለ ሥርዓቱ መጠሪያ ጉዳይ በዚህ ላብቃና ወደስርዐቱ አራማጅ መጠሪያዎች ልሻገር፤

ስለገዥው ፓርቲ መጠሪያ

ሀ. ወያኔ                   በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጥቅም ላይ የሚውል። ተቃዋሚ የትግራይ ተወላጆች የማይጠቀሙበት፤ ሌሎችም
ሲጠቀሙበት ባይሰሙ ፈቃዳቸው የሚሆን፤ አንዳንዶቹ በአጼ ሃይለስላሴ መንግሰት ጊዜ  አምጾ የነበረውን ገራገሩን ወያኔ ካሁኑ ከፉው ወያኔ ጋር መቀላቀል ይሆናል የሚል ስጋት እነዳላቸውም የሚጠቁሙ አሉ፤ አብዛኛው የሚጠቀምበት ግን ይህን ያህል የይዘት ልዩነት ያመጣል አያመጣም ብሎ ሳይሆን፤ በጣም የተለመደና ቀላልም በመሆኑ ብቻ ነው፤     

ለ. ኢሕአዴግ   በሃገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀቶች፤ በገዢው ፓርቲና አገልጋዮቹ ጥቅም ላይ የሚውል፤ ከላይ የጠቀስኳቸው ተቃዋሚ የትግራይ ተወላጆችም የሚፈቅዱት፤
                  
ሐ. ወያኔ/ኢሕአዴግ፤  የወያኔ የበላይነት የጎላበት  ሆኖ ሌሎቹም ተለጣፊዎቹ  ሚና እንዳላቸው ለማሳየት በሚፈልጉ፤ ወይም
                    ደግሞ ከሁለቱ ባንዱ ቢጠራ ለውጥ የለውም ለማለት በሚፈልጉ፤                                      
        መ. የትግሬ ሕዝበ ነጻነት ግንባር/ ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃርነት ትግራይ፤ በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ                                    ድርጅቶች/ግለሰቦች በማለዋወጥ ስራ ላይ የሚውል፤ ህዝባዊ ወያኔ የሚለው አልፎ አልፎ ካልሆነ፤ ብዙ                            አይሰማም። የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ከማለት ይልቅ በእንግሊዝኛው ቲፒ ኤል ኤፍ ቢባል ደስ የሚላቸው                           የትግራይ ተወላጆችመ አሉ።

ማሳሰቢያ.- ከዚህ በላይ ስለ አጠራሩ ያቀረብኩት እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ ሳይሆን፤ አንዳንድ ካጋጠሙኝ ሁኔታዎች ተነስቼ ነው። በዚህ በስም አጠራር ምክንያት ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ሲስተናገድ አይቻለሁ፤ እራሴም ብሆን ወያኔ ከሚለው አልፎ አልፎም የትግሬ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከሚለው በስተቀር ሌላ ባፌ ስለማይዞር ካንዳንድ ወዳጆቼ የትግራይ ተወላጆች በንግግራችን መሃል  እንዲያው እንዲህ ከምትል እንዲህ ብትለው ይሻላል የሚል ጥቆማ ያጋጥመኛል። የትግራይ ወንደሞቼን ችግራቸውን አልረዳም ማለቴ እንዳልሆነ ግን  ተረዱልኝ፤ ትግሬ የሚለው ቃል ከክፉ አድራጊዎች ጋር ተቀላቅሎ መነገሩ ስለሚያሰቆጫቸው እንደሆነ እረዳለሁ፤ አኔም በነሱ ቦታ ብሆን ከዚያ የተለየ አቋም ላይኖረኝ እንደማይችል ዋስትና አልሰጥም። እዚህ ያነሳሁበት ምክንያት ግን በህበረት ትግል ሂደቶች ውስጥ ላለመተማመን በመጠኑም ቢሆን ምክንያቶች እንደሚሆኑ ስለምገነዘብ ነው። ስለሆነም ተነጋግሮ ለስርዓቱም ሆነ ለስርዓቱ አራማጆች በጋራ  ስምምነት የተደረሰበትን ስም  የህብረቱ የጋራ ቋንቋ ይዞ መሄድ የመለያያ ምክንያቶችን ማጥበቢያ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። እነዚህን ሁለት ከስም አጠራር ጋር የተያያዙ ሃሳቦችን ከዳሰስኩ   በዃላ ወደዋነው ጉዳይ ስመለስ በተለይ ሥርዓቱን በተመለከተ የትኛውን ዓይነት ሥርዓት ነው የምንታገለው የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በሱ ላይ ስምምነት ኖሮ ግልጽ አቋም ሳይደወሰድ በተሸፋፈነ መልክ አንዱ ዘረኛ ሌላው አምባገነን እያለ አብሮ በህብረት መስራት እንደማይቻል፤ ግልጽ ነው። ነገር ግን ሁለቱም በየግላቸው ሊታገሉ ይችላሉ ወደዲያሰፖራው ተመልሰን የሚፈጠረውን አጣዳፊ ሕብረት እንየው፤

ትግሉ ሰላማዊ ነው እስከተባለ ድረስ፤ ዶ/ር በያን ያነሱት በሀገር ቤት ተተክሎ እዚያ ስለሚፈጠር ሕብረት ወይም እዚሁ በዲያስፖራው ስለሚመሰረት የድጋፍ ድርጀት ሕብረት የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ መልስ እንዲያገኝ ማድረጉ አላስፈላጊ የሆኑ ውጣ ውረዶችን ያስወግዳል። ሌላው ከዚሁ ጋር እየተነሳ ያለው  „ሁሉን ያቀፈ“ የሚባለው ሃሳብ ነው። ይህ ነገር ለመረዳት ከሚያስቸግሩኝ ሚሊዎን ነገሮች አንዱ ነው። ሁሉን ያቀፈን ጽንሰ ሃሳብ የሚያራምዱት ወገኖች  አንዴም አብራርተው ሲያስቀምጡት አላየሁምና ነው። ያ ማለት ግን፤ እራሴን በራሴ ለመርዳት ሙከራ አላደረግሁም ማለት አይደለም።

ስለሆነም፤ የመጀመሪያው ግንዛቤዬ እንዲታቀፉ/እንዲተቃቀፉ የሚፈለጉት በየሜዳው፤ በየተራራው፤ በየሸንተረሩ፤ በጓዳ በጎድጓዳው ተበታትነው የሚገኙትን የተደራጁ ሃይሎች በወረንጦ ለቅሞ ይዞ አስተባብሮ/ተባብሮ ሕብረት መፍጠር ማለት ይመስለኛል። እዚህ ላይ ግን፤ አንተኛው ማተብህን በጥሰህ፤ አንተኛው ደግሞ ክርስትና ተነስትህ ነው ለዕቅፍ የምትበቃው  የሚሉ ገደቦች እነዳሉም አለመዘንጋቴን ዕወቁልኝ፤ ወደዃለም እመለስበታለሁ። በወረንጦ መልቀሙ ከተቻለ መጥፎ አይደለም። መቻሉን ግን እጠራጠራለሁ። ሌላው የሚታየኝ አማራጭ ደግሞ፤ ሁሉንም ለቅሞ መያዝ ሳያስፈልግ አንድም፤ ሁለትም፤ ሶስትም ጠንከረከር ያሉ ሃይሎች ተሰባስበው፤ እነሱ ለህዝብ የሚመኙለትን ሳይሆን፤ ሕዝቡ ምን ይፈልጋል? ምን እያለ ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ፤ የህብረተሰቡን ስሜት ተከታትሎ በመረዳት፤ ዛሬ ምን ይዘን ብንቀርብ ነው ህዝብ ለማዳመጥ ጆሮውን የሚሰጠን? የሚለውን ጥያቄ  መልሶ፤ ለዚህ የህዝብ ስሜት ቀራቢ የሆነና ሁሉንም ያሰባስባል የሚል ፐሮግራም ዘርግቶ፤ ማስተዋወቅ፤ ሁሉም እስኪሰባሰብ ሳይጠብቁ እጅ ላይ ባለው ሃይል ሥራ መጀመር፤ ዱሮ ለቡሄ ስንጨፍር „እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል አጋፋሪ ይደግሳል“ እንደምንለው የስራ ጭስ ሲጨስ ያየ፤ ቀድሞ ጥሪውን ያልሰማው ጭምር፤ እዚያ ማዶ ምን አለ ሲል  ጆሮውን ይቀስራል፤  ይህ የኔ እምነት ብቻ ሳይሆን፤ በልምድ ያገኘሁትና፤ አሁንም የሚታይ ነው።

ሰለማተብ መበጠስና ስለክርስትና መነሳት ባነሳሁት ላይ እመለስበታለሁ እንዳልኩት ተመልሻለሁ፤ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት የሚሏቸው አነጋገሮች በተወሰኑ የየዘውጋቸውን መብት እናስጠብቃለን በሚል ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ አካባቢ ጉሮሮ የመከርከር ጠባይ ያላቸው መሆናቸውን  አሌ ማለት ይከብደኛል።     – አንድ ትዝ የሚለኝ ነገር፤ ዶ/ር መርራ ጉዲና ጀርመን ሃገር አንድ ማህበራዊ ስብሰባ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዣቸው ንግግሩን ካደረጉ በሁዋላ፤ ስላደረጉት ንግግርና ሌላም ሌላም ለብቻችን ቁጭ ብለን ስንጨዋወት፤  የኢትዮጵያዊነቱና የተያያዙ ጉዳዮች ተነስተው ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ፤ ወዘተ … እያልኩ ስንጫጫባቸው ይመስለኛል፤ እንደመሰልቸት ብለው፤ „እናንተ ( እናንተ የሚለው የተቀየረ ስም ነው) እኮ የኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት ችግር የለባችሁም፤ እኛ ሰፈር ግን ችግር አለ።“ ያሉኝን አስታውሳለሁ። – ከእነዚህ ንቅናቄዎች ውስጥ ደግሞ  „እንገነጠላለን“ ይላሉ የሚልም አለ። ሕብረት እንፍጠር ብለው ለሚነሱ ሌሎች ወገኖች እንዲህ ያለ ጥያቄ የሚያነሳን ዓይኑን አያሳየኝ  ይሉና ለመተባበር መጀመሪያ ይህንን አላማሕን ሰርዘህ፤ ያንን አቋምህን ትተህ ነው ካንተ ጋር የምነጋገረው ይላሉ፤ በበኩሌ የዚህ ዓይነቱን ጥያቄ ማቅረብ ማለት በተዘዋዋሪ እራስህን አጥፋ እንደማለት አድርጌ ነው የምወስደው፤ ምክንያቱም ድርጀቱ ያለአላማ፤  አላማው ደግሞ ያለድርጅቱ ህልውና ሊኖራቸው  ስለማይችሉ ጥያቄው ፉርሽ ነው ማለት ነው።

እንደኔ ከነጻ አውጭዎቹ የሚጠበቀው እንዲሁ አየር ላይ የተነሳፈፉ ሳይሆኑ፤ የሚኖሩት እዚቺው  ኢትዮጵያ በምትባለው ጥላ ስር መሆናቸውን፤ በዚህ ጥላ ስር የተጠለሉት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሚሊዎኖችም እነደሆኑ፤ በዚያውም ልክ ሕይወታቸው ከሌላው ጋር በብዙ ድር የተሳሰረ መሆኑን፤ ባሁኑ ሰዓት ሀገሪቱና ሕዝቧ  ላይ ተንሰራፍቶ በሚገኘው ዘረኛ ስርዓት ስር የሚማቅቁ መሆናቸውን፤ እነሱም የዚህ የአጥፍቶ አጥፊ ሥርዓት ሰለባ መሆናቸውን                   – ይሄኛውን እያረጋገጡጥ እንዳሉ ግልጽ ነው – መቀበል፤ በወዲህ በኩል ደግሞ ልገንጠል ብሎ ጥያቄ ማንሳት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብትም ጥያቄ መሆኑ ታውቆ፤ የዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ደግሞ በዴሞክራሲ መፈታት ስለሚገባውና ስለሚቻልም „ተገንጣዮች“ ችግራቸው በዴሞክራሲ የሚፈታ መሆኑን በማስረዳት ለጋራ ትግሉ ተባባሪ እንዲሆኑ መጋበዝ፤ በዘውግ ንቅናቄ ውስጥ ያሉ ዴሞክራቶች ይህንን አይቀበሉትም የሚል እምነት የለኝም። ይቻላል ብዬም  አምናለሁ። ጥያቄው እንዴት የሚለው እንደሆነም ግልጽ ነው። በኔ እምነት ብዙ የሚከብድ አይደለም። የሚጠይቀው ዋና ጉዳይ ቢኖር በሁለቱም ወገን  የዴሞክራሲ አርበኛ ሆኖ መገኘትን ብቻ ነው። በስርዟ ላይ እመለስባታለሁ፤  ወደሚከተለው ላግድም፤

ዴሞክራሲ በተግባር – ይህቺ ቋንቋ  ከቪኦኤ በትውስት የተገኘች ነች – ዴሞክረሲያዊ ጥያቄን በዴሞክራሲ ለመፍታት በመጀመሪያ ዴሞክራሲ እራሱ ረጋ ብሎ የሚኖርበት  መቀመጫ ቦታ ያስፈልገዋል። ዛሬ ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ሁሉ ታጥሮበት፤ መተናፈሻ አጥቶ እንደሚገኝ እናውቃለን፤ እንዲህ ከሆነ ታዲያ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄያችንን በዴሞክራሲ  ለመፍታት ከተስማማን፤ ዛሬ ነገ ሳንል ያሉንን ጥያቄዎች(ፐሮግራሞች) ጉዳት እንዳይደርሰባቸው በጠንካራ ካርቶን አሽገን አስቀምጠን፤ ዛሬ ወያኔን ዙሪያውን ከብበን ወደየራሳችን መጎተቱን አቁመን፤ ወደ አንድ አቅጣጫ ጎትተን ጥለን ቦታውን ከወያኔ ጉጀሌ መፈንጫነት የዴሞክራሲ መናኸሪያ ማድረግና ተደራጅተው ወያኔውን በማስወገድ የተሳተፉት ብቻ ሳይሆኑ፤ ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው የህብረተሰብ ተወካዮችን  አካትቶ በሚቋቋም የሽግግር መንግሰት አማካይነት  ወያኔ በሱ ሽንጥ ልክ የሰፋውን ሕገ-መንግሥት በሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሽንጥ ልክ በተሰፋ ሕገመንግስት ተክቶ፤ በሱ መተዳደር መጀመር፤ እዚህ ከተደረሰ ስለሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ገብቼ ላሰለቻችሁ አልፈልግም። ምክንያቱም ያሰመርኩበት ደረጃ እስከሚደረስ ድረስ በሚደረገው ጉዞ በዙ ዳገትና ቁልቁለት ተወጥቶ ተወርዷልና፤ በዚያወም ልክ ብዙ ጉዳዮች ቀደም ብለው ፍጻሜ ስለማግኘታቸው ጥርጥር አይኖርም።

የዴሞክራሲ አርበኛ ሆኖ መገኘትን አመለስባታለሁ እንዳልኩት፤ የምለውን ልበልና ከዚህ ሰፈር ልውጣ፤  ግንዛቤዬ፤- „ተገንጣይ ሃይል“ በሚለው ትይዩ የቆመው „የአንድነት ሃይል“ ነው። በነዚህ ሁለት ሃይሎች ዘንድ ዴሞክራሲ የሚፈራበት („ፈ“ ን አጥብቃችሁ አንብቡ) ጉዳይ አለ። የአንድነት ሃይሉ „አንድነት“ ወደመንግስተሰማያት የሚያስገባው መንገድ እሱ ብቻ ነው የሚል የማይነቃነቅ ዕምነት ስለያዘ፤ በዴሞክራሲ አማካይነትስ ቢሆን፤ እገዜሩ/አላሁ የሚሰሩት ስለማይተወቅ፤ መገንጠል ቢመጣ ምን ይውጠኛል የሚል ስጋት አለው። „ተገንጣይ ሃይል“ ደግሞ  የዚያች እጁ የሚያደረጋት  ቀበሌ  ገዥ ሆኖ በዓለም አቀፍ መድረክ ብቅ ማለት ቅሪት በውስጡ ሰለሚኖር፤ ይህ ምኞት ደግሞ በዴሞክራሲ መንገድ ስለመሟላቱ እርግጠኛ ያለመሆን ስጋት አለው። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ „የዴሞክራሲ አርበኝነት“ ያስፈልጋል የምለው፤ ባጭር ቋንቋ፤ በዴሞክራሲ የተገኙ ውጤቶችን ለመቀበል በቁርጠኝነት መቆም ማለት ነው። ምክር፤- ለ“ተገንጣይ“ ታጋይ! ዛሬ ለመገንጠል ብለህ ብረት አንግበህ በረሃ ለበረሃ መንከራተትህ፤ እንደ አውሬ መታደንህ፤ ይቀርና፤ ዴሞክረሲ በሰፈነባት ኢትዮጵያ ውስጥ ከመገንጠሉ ፖለቲካ ትግልህ ጎን ለጎን  በህዝብህ መሃል ሆነህ፤ አገርህን፤ ሰፈርህን፤ መንደርህን እያለማህ አንተም እየለማህ፤ እየወለድክ እየከበድከ የምታደርገው ትግል ስለሆነና፤ ይህ የሰለጠነ አካሄድም እንደሆነ መገንዘብ አስቸጋሪ ሳይሆንብህ፤ ቀደም ብዬ እንደጠቆምኩት፤ ዛሬ ያነገብካትን ፕሮግራም አመቺ በሆነ ቦታ አሽገህ አስቀምጠህ፤  ነገ ዛሬ ሳትል ዛሬውኑ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን በማስፈኑ ስራ ተሳተፍ!  „የአንድነት“ ሃይልም የዜጎች ሃይል እንደመሆንህ  ከአንድ የዘውግ ስብስብ የከበደ ሃላፊነት እንዳለብህ ተገንዝበህ ያህንን ሃላፊነት የመወጣት ብቃት እንዳለህ ማሳየት ሊቸግርህ አይገባም።

እስከዚህ ድረስ ሕብረትን በተመለከተ ካለፉ ትብብሮች በክፉም ሆን በደጉ ምን መማር እንደሚቻል፤ ተቃዋሚዎች ለትብብር ሲዘጋጁ ቢያጤኗቸው ይጠቅማል የሚሉ ጉዳዮችን በመጠቆም፤ ትብብሩ ሁሉንም ያቀፈ ይሆናል ለሚለውም አማራጭ አካሄዶችን ለማመላከት ሙከራ በማድረግ፤ ከኢትዮጵያ ሁኔታ በመነሳት ለህብረት የሚሰባሰቡ ሃይሎች ሰለዴሞክራሲ ሚና ሰለሚኖራቸው ዕይታና ተመሳሳይ ነጥቦች ላይ ያለኝን ግንዛቤን ነማንሸራሸር ሞክሬአለሁ። እነዚህ በህብረት ለመሰባሰብ ጠቃሚ ናቸው ያልኳቸውን ሃሳቦች ግንዛቤ በማስገባት በዲያስፖራ የሚቀናጀው አጣዳፊው የትብብረ ሃይል በሚከተለው መልክ ቢቀናጅ ፍሬአማ ስራ ሊሰራ ይችላል የሚል እምነት አለኝ።

የወያኔን የባርነት አገዛዝ ለማስወገድ የሚደራጅ ሃይል በርግጥም ታግሎ ለማታገል የወሰነ ከሆነ፤ በሃገር ውስጥ ሕልውናውን አሳውቆ ከሕዝብ መሃል በመገኘት ትግሉን መምራት፤  „በሪሞት ኮነትሮል እመራለሁ ብሎ አለመቃጣት፤  ይህ የማይሳከ ከሆነ ደግሞ፤ ተሳክቶለት በሃገር ውስጥ ታግሎ በማታገል  የባርነቱ አገዛዝ እንዲያበቃ ለማድረግ ደፋ ቀና የሚለውን ሃቀኛ ታጋይ ሃይል አጢኖ በስንቅ፤ በትጥቅና በሌላ ሌላም አቅጣጨ በሚደረጉ ድጋፎች ትግሉን ለማጠናከር ተደራጅቶ መንቀሳቀስ። እዚህ ላይም አንድ ምልከታ አለኝ። በተለይ ሁለተኛውን አቅጣጫ በተመለከተ፤ ቅኝቱ ከወያኔው ባህርይ አቅጣቻ መሆን ስላለበት፤ ከሁሉ አስቀድሞ  ከሀገር ቤቱ ሃይል ጋር በሚያስማማ ቋንቋ መግባባትን መፍጠር፤ (ወያኔን የሚያሸብሩ ቋንቋዎች አለመጠቀም)፤ ከማንኛውም መሳሪያ አንጋች ጋር ብቻ ሳይሆን፤ ተመሳሳይ ሃሳብ የሚያወጣ የሚያወርድ ነው ተብሎ ከሚጠረጠር ጋር ጭምር ንክኪ እንደይኖር ጥንቃቄ እንደይኖር ማድረግ፤  ይህንን የምለው ያለምክንያት አይደለም። ወያኔን እንደምንታዘበው፤ የራሱም ጥላ ጭምር ስለሚያስሸብረው፤ ተሸብሮ እንዳያሸብርና በሃገር ቤቱና በዲያስፖራው መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳያደናቅፍ ለማለት ነው። ጸረ-ሽብር ሕጉ „የንጉሡን ጠላት የራቀውን በመድፍ የቀረበውን በሰይፍ“ እንደሚሉት በቅርብም በሩቅም አገልግሎት ላይ ስለሚውል፤ ስህተት እንዳይፈጸም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። በመጨረሻም ጥያቄ አለኝ።

ትግል የሚደረገው ምን ለመድረስ ነው?  እስከዛሬ በነበረው አካሄድ ሰላማዊና ሕጋዊ ታጋዮች – የምርጫ ፓረቲዎች – ጥርሳቸውን ነከሰው በያአምስት አመቱ በሚደረገው የምርጫ ግርግር ተሳትፈው የወያኔ የዘውድ በዓል ከተከበረ በዃላ በዚህም በዚያም በምርጫው ላይ የተፈጸመ ደባዎችን መዝግበን፤ ለምርጫ ቦረድ አቅርበን፤ ተወዳዳሪዎቻችን ተደብድበውብን፤ ታስረውብን፤ ታዘቢዎቻችን ተበርረውብን ወዘተ … የበደሉ ዓይነት ተዘርዝሮ አያለቅም፤ እያሉ ይተርኩልናል፤ ዱሮውንም ቢሆን፤ ምረጫው ውስጥ የገባነው ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ይሆናል ብለን ሳይሆን፤ አንዱ የውጭ መንግስታት ጽንፈኞች የሉናል ብለን ነው፤ ሲል ሌላው ደግሞ ምርጫ ሰው እንደሚለው መወዳደሪያ ሳይሆን፤ መታገያ ስለሆነ ነው የገባነው፤ አንድ ጊዜ ደግሞ የሰማነው፤ ከዚሁ ከምረጫ ጋር የተያያዘ ፊረማ ተፈርሞ የፈረምነው የውጭ መንግስቶች ኮረኩመውን ነው የሚል ሮሮ ሁሉ ሰምተናል። ከምርጫው በሁዋላ ደግሞ – ምርጫውን አያሸንፉ እንጂ የመረጣቸው ምንም ሰው የለም ማለት ግን አይደለምና – እኛን የመረጡ ደጋፊዎቻችንን ገዠው ፓረቲ እኔን ለምን አልመረጣችሁም እያለ ያሰቃያቸዋል፤ ከመሬታቸው ያፈናቅላቸዋል፤ – ምርጫ አለማሸነፋቸው አንሶ ለመራጮቻቸው ጦስ የመሆን ጣጣ ሁሉ አለባቸው። – መቼም ላይችል አይሰጠው ማለት ነው እንጂ መከራው ብዙ ነው። በመጨረሻው ምርጫ ይልቅ በጣም ስለመረራቸው መሰለኝ ቁርጥ አድረገው ምርጫውን አንቀበለውም አሉና “አፈር አስበሉት።” አልፎ አልፎም ምርጫው ነጻና ፍታዊ ቢሆን ያለጥርጥረ እናሸንፍ ነበር የሚሉትም ነገር አለ። እዚህ ላይ ጥሩ ነገር መጣ። „ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ቢሆን“ የሚለው ነገር፤ ይህን በተመለከተ አጠቃላይ ሕዝብን አንድ ያደረገ  ድምዳሜ አለ። ይኸውም በኢትዮጵያ ውስጥ የብዙሃን ፓረቲ ስርዓት የሚስተናገድበትን  አካሄድ ተከትሎ ዛሬ ባለው የገዥ ፓርቲ አዘጋጅነት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ መካሄድ ይችላል ብሎ ማሰብ „የህልም እንጀራ“ ነው የሚለው ነው።  ይሄ ወዴት ነው የሚወስደን? ካልን፤ በወያኔ አገዛዝ ስር በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚደረገው ፋይዳቢስ የመረጫ  ውጣ ውረድ ቀርቶ፤ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ለሚያስችል ነጻነት መታገልን አስፈላጊ ነው ወደሚለው ይሆናል። ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ለሚያስችል ነጻነት ስንል ምን ማለታችን ነው?  መልስ፤-  መራጩ ነጻ መሆን አለበት ማለት ነው። እንደዚያ ካልን ታዲያ ደግሞ የመራጮች ሁሉ ትግል የሚሆነው የነጻነት ትግል ነው ማለት ነው። ለዛሬ እዚች ላይ ላብቃ፤ ነገ በዚሁ የነጻነት ትግል ላይ አቅሜ በፈቀደው ያለኝን ሁሉ  አሟጥጬ ይዤ እቀርባለሁ፤ የዚያው ሰው ይበለን።

ጣስው አሰፋ
tassat@t-online.de

Friday, February 26, 2016

Oromos Should Boycott MIDROC Ethiopia Products; Force Shut Down Gold Mining in Oromia!


alamudi

Mohammed International Development Research and Organization Companies (MIDROC)

MIDROC Companies are owned by the Saudi billionaire, Sheikh Mohammed Hussein Ali Al-Amoudi. Al-Amoudi Companies are operating in Africa, Europe, the Middle East, and the United States of America[i].

Who is Mohammed Hussein Al-Amoudi?

Mohammed Hussein Ali Al-Amoudi is a Saudi Arabian billionaire businessman. Al-Amoudi was born July 21, 1946 from his mother Rakiya Mohammed Yassin (Wollo) and his father Haji Hussein Al-Amoudi (Saudi Arabia). The 69-year-old is close to the Saudi royal family.

He was ranked by Forbes magazine as the world’s 63rd-richest person and was worth $12.3 billion in 2012. In early March 2015, had his net worth estimated at Forbes at $10.8 billion. Mohammed Al-Amoudi’s estimated net worth declined to $8.4 billion as of February 2016, according to Bloomberg, a relative fall in net value was linked to the global fall in oil prices at the time of estimation. This son of Saudi father and Ethiopian mother, Al-Amoudi started investing in Sweden in the 1970s. His construction company MIDROC scored contract to build Saudi Arabia’s nationwide underground oil storage complex in 1988 estimated at $30 billion project. This solidified his fortune. Today the Ethiopian economy is controlled by two large major conglomerates: his MIDROC (Mohamed International Development Research Organization Companies) and EFFORT (The Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigrai).

In addition to his economic empire, Al-Amoudi seems to have built a sophisticated security apparatus akin to shadow government inside Ethiopia–Trust Protection and Personnel Services Pvt. Ltd. Co. (TRUST). According to Al-Amoudi, TRUST is “engaged in providing protection and other professional as well as personnel services on contract basis. It also renders services related to customs clearing and forwarding services, as well as safety and modern alarm services for interested organizations. The company started its service activities with the aim of modernizing protection and personnel services within companies in Ethiopia.” Only a country ruled by lawless rebels whose primary aim is robbery of that country will allow a foreign national (Saudi Arabian billionaire) to form such a sophisticated security apparatus inside their country.

 Albasa Dagaga
- See more at: http://www.zehabesha.com/oromos-should-boycott-midroc-ethiopia-products-force-shut-down-gold-mining-in-oromia/#sthash.oVVzeIFf.dpuf

የጅማ ህዝብ ተነሳ – በቀለም ወለጋ ሕዝብ በጩኸት አጋዚ በጥይት እየታገሉ ነው * 4 ሰልፈኞች ተሰውተዋል




(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ የመንግስት ጋዜጠኞችን ሰብሰበው በኦሮሚያ ክልል ሰልፍ የወጡ ነጹሃንን ካላረፉ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ቢያስፈራሩም በኦሮሚያ ክልል ግን ይህን የርሳቸውን ቃል የሚሰማ እንደሌለ በየከተማው እየተደረጉ ያሉ ተቃውሞዎች አሳይተዋል::
Jima
በቀለም ወለጋ በጊዳሚ ወረዳ በቡሪ መንደር ዛሬ በተደረገ ከፍተኛ ተቃውሞ የአጋዚ ጦር በሕዝቡ ላይ ጥይት አንዝንቦ ከ40 በላይ ሰዎችን ሲያቆስል 4 ሰዎችን እንደገደለ ለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች አሳይተዋል:: ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄው እንዲመለስ መንግስትም እንዲለቅ እየጠየቀ ባለበት ወቅት በተለይም ከቤንሻንጉል እና ከጋምቤላ አካባቢ የመጡ የአጋዚ ጦር አባላትይ ሕዝቡ ላይ ተኩሰዋል:: እነዚህ የቤንሻንጉል እና የጋምቤላ የአጋዚ ጦር አባላት አማርኛም ሆነ ኦሮሚኛ የማይነገሩ በመሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ ምን እያለ እንደሚጮህ እንኳ የሚረዱ አይደሉም የሚሉ በስፍራው ያሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ሕወሓት መንግስት በምርጫ 97 ማግስት በሕዝብ ላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ወታደሮችን ከሌላ ክልል በማስመጣት የፈጸመውን ተመሳሳይ ፍጅት በኦሮሚያም እየደገመው ነው ብለዋል::
የኦሮሞ ሕዝብ ተቃሞ በጉጂም በረካ ሕዝብ በአደባባይ ወጥትቶ ዛሬም ተቃውሞውን ሲያሰማ ነው የዋለውም:: በተለም በቀንቻ ከተማ ከህፅአነት እስከ አዋቂ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰማ የኦሮሚያ ፖሊስ ከሕዝብ ጋር በመሆን ያለውን አጋርነት አሳይቷል:: በተለይ በዛሬው ተቃውሞ የኦሮሚያ ፖሊስ የጉጂን ሕዝብ አጅቦ እንደነበርና ከጥቃትም ሲከላከል እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
tekawemo
በጅማ እስካሁን የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በኋላ አሳይቶት የነበረውን ዝምታ በመስበር ዛሬ በ ሻቤ ሶዶ ከተማ በዓይነቱ ልዩ የነበረ ት ዕይንተ ህዝብ ታይቷል:: በጅማ ከሕፃናት እስከ አዋቂ አደባባይ በመውጣት በስር ዓቱ ላይ ያለውን ጥላቻ ገልጾ የሕወሃት መንግስት አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ሲጠይቅ እንደነበር ምንጮቻችን አስታውቀዋል::
west welega
በሌላ በኩል በምስራቅ ወጋ ቆዶላ ከተማም እንዲሁ ሕዝቡ አደባባይ ነበር የዋለው:: እንደ ሪፖርቶች ገለጻ በምስራቅ ወለጋ በቆዳላ ከተማ በነበረው ተቃውሞ አጋዚ ሠራዊት ሕዝቡ ላይ እንዲሁ ሲተኩስ ነበር:: እነዚሁ ዱላ የያዙትና በዝማ

wanted officials