Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, February 11, 2016

የህወሃት ደህንነትና የሚጠፉት ሰዎች ሚስጥር








በአሁኑ ጊዜ ‹አፋልጉኝ› የሚሉ ፎቶግራፍ የያዙ ማስታወቂያዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ግን ሰዎች የሚጠፉት የት እየሄዱ ነው??በሌላ በኩል ‹‹ለሁሉም ኢትዮጵያዊያንና የውጭ ዜጎች ስልክዎን (What’s up) ብቻ በመጠቀም ትርፋማ የሚሆኑበት ስራ!አሁኑኑ ይደውሉ!››የሚሉ ማስታወቂያዎችን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተለጥፈዉ ተመልክታችሁ ይሆናል፡፡ይህን ይዤ ደህንነት ቢሮ ወደሚሰሩት ጓዶቼ አቀናሁ፡፡እናም በስልክዎ ብቻ የሚሰሩት ስራ ስለላ መሆኑን ተረዳሁ፡፡አንድ ድርጊት ሪፖረት ካደረጉ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያገኛሉ፡፡ይህ የደም እንጀራ መሆኑ ነው፡፡እህትን ወንድምን እያሳሰሩ፣እያስገደሉ ከርስን መሙላት!እትፍ ይቅር አይበላ!ሺ አመት አይኖር!
ደግነቱ ይህ የደህንነት የስለላ ስራ ለሰሪውም አይመች!ውድ ህይወትን ያስከፍላል፡፡የደህንነት ሚስጥር ያልገባው ነፈዝ ዘሎ ጥንቅር ይላል፡፡‹‹አያ በሬ ሆይ፣ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ›› እንዲሉ፡፡ስልጣኑን በጉልበት ለማራዘም የወሰነው ህወሃት ለስለላ ተግባር የሚያሰማራቸው ሰዎች ባብዛኛው ገንዘብ የሌላቸው ደሃ ወጣቶችን(ሊስትሮዎችን ሳይቀር) ቢሆንም አንዳንዴ በታማኝነታቸውና ወሬ በመሰብሰብ ቅልጥፍናቸው መሰረት አሮጊቶችን፣ሽማግሌዎችንና ህጻናቶችንም ይጨምራል፡፡ግን ህወሃቶች የሚከተሉት አንድ የኮሚኒስቶች አባባል አለ ‹‹ሚስጥር የማያወጣ ሰው አንድ ብቻ ነው፤እሱም የሞተ ሰው ነው›› ከደህንነት ሰዎች ጋር መስራት እንኩዋን ስርዓቱ እየፈራረሰ ባለበትና አንዱ አንዱን በማያምንበት ባሁኑ ወቅት ይቅርና በሰላም ጊዜም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ከላይ ያሉት የደህንነት ሰዎች ሰውን እንደቃ ነው የሚጠቀሙበት፤አንድ ሰው ትንሽ ካገለገለ በኋላ በአስወጋጅ ኮሚቴው አማካኝነት ስለሚወገድ(ስለሚገደል) የደረሰበት አይታወቅም፤ ቤተሰቡም ‹አፋልጉኝ ለጠቆመኝ ወሮታውን የምከፍል መሆኑን እገልጻለሁ› ከማለት ውጭ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ምክንያቱም ለደህንነት ቢሮ የስለላ ስራ ለመስራት ሲስማሙ ልጆችም ሚስትም ሌሎችም የቤተሰብ አባላት እንዳይሰሙ በብዙ መሃላና ማስጠንቀቂያ ስለሆ ነው፡፡በቃኝ ያለ ቀን አስወጋጁ ቆሻሻውን ያስወግዳል፡፡ ከደህንነት እንዳገኘሁት መረጃ ብዙ ሰዎች በዚህ መልክ ጠፍተዋል(ተገለዋል)፡፡ይህ ማለት ግን የጠፋዉ ሰዉ ሁሉ ተገድሏል ማለት አይደለም፡፡
እባካችሁ ወገኖቼ ገና ለገና ጥቂት ዘረኞችን ስልጣን ላይ ለማቆየትና የእለት ከርሳችን ለመሙላት ብለን ከእንደዚህ አይነት አጥፍቶ ጠፊነት እንቆጠብ፤ሌሎችም ባለማወቅ ወደስለላ ተግባር እንዳይገቡ ሼር በማድረግ ተባበሩ፡፡እኔ ከምሰራበት የመንግስት ስራ የለቀቅሁ ይህን መሰል ቆሻሻ ስራ ላለመስራት ነው፡፡ሴትነቴንና መልከ ቁመናየን በመጠቀም የስለላ ተግባር እንድሰራ ይጨቀጭቁኝ ነበር፡፡አልሰራም ስላልኩ ብቻ የተለያየ ጥቅማጥቅም ላይ እንዳልሳተፍ አደረጉኝ፤ ከዚያም አልፎ እስር ቤትም አስገቡኝ፤ ከስር ስወጣ ወደ ስራየ አልተመለስኩም፤አሁንም ሊያስሩኝ አንዴ አርባ ምንጭ አንዴ አዲስ አበባ እየፈለጉኝ እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ግን አንድ ሳላደርግ ላለመታሰርና ላለመሞት እንደወሰንኩ ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡ሞት ገና ስንወለድ የተሰጠን የማይቀር እዳ/እረፍት ነው፡፡መሞት ላይቀር ህይወት ትርጉም ካጣ ትርጉም ያለው ሞት መሞት ህያውነት ነው፡፡
ድል ለሰፊው ህዝብ!

ትንሳዬ ሃገር

No comments:

Post a Comment

wanted officials