ከ እስራት ስወጣ አንቺን ሆነ ቤተሰቦችሽን አልምራችሁም ብሎ ዝቶብኛል” ከሳሽ የሰጠችው ቃል
ከታምሩ ገዳ
የ33 አመቱ ጎልማሳ ማሃድ ኢዳን እና ስሟ ለጊዜው ያለተገለጸው የ 20 አመቷ እጮኛው ቀደም ባለው ቅራኔያቸው ሳቢያ ማሃድ ከ እንግሊዝ ፖሊሶች የክስ ፋይል ውስጥ የወድቃል ። ማሃድም ይህንን ከሁለት አመት በፊት የተደርገ ቅራኔን እና የክስ ፋይል ውድቅ እንዲሆንለት እጮኛው አንድ መወጫ ዘዴ ካላፈላለገች ብቸኛው መፍትሔ የአርሷ ህይውትን ማጥፋት ብቻ አንደሚሆን ይዝታል፣ ያሰፈራራታልም እንደ ከሳሽ እማኝነት ቃል እና የፖሊስ ሪፖርት ዘገባ።
ከ ዋና መዲናይቱ ሎንዶን በማእከላዊ ምእራብ አቅጣጫ ከምትገኘው በኮቨንተሪ ከተማ ውስጥ ነዋሪ የነበረው በትውልዱ የጎረቤት ሶማሊያ ተወላጁ ማሃድ የቀደሞው የሴት ጓደኛውን ቀደም ባለ ግጭት ሳቢያ ከፊቷ ላይ በቡጢ በመማታት ለቀረበበት የፖሊስ የክስ ቻርጅ ወድቅ እንድታስደርግለት፣ አሊያም እንደሚገድላት ይዝትባታል ። የፍላጎቱ ያለመሳካት ያሰጋው እና ያበሳጨው ተከሳሹ ማሃድ የቀደሞ ጓደኛው ባለፈው መሰከረም 2013 አኤ አከ አንድ የመኪና ማቆሚያ (ፓርክ )ውስጥ ከመኪናዋ ውስጥ ሳለች በቢላ ካጠቃት በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ “እግሬ አውጪኝ” በማለት በኢትዮጵያ ውስጥም ደብዛውን በማጥፋት ለሁለት አመታት ይደበቃል።
ከዚያም በሁዋላ ክሱ ተረሳስቶልኝ ይሆናል ከሚል ሕሳቤ ወደ እንግሊዝ ለመመለስ ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ ምድር ሊያስገባው የሚችለው የመግቢያ ቪዛን ለማግኘት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲያመለክት ፖሊስ በምደረ እንግሊዝ ውስጥ ሲያሰሰው የከረመው እና በወንጀለኞች የአሰሳ መዝግብ ( ክራይምስ ዎችስ ) ውስጥ ስሙ የተካተተው ማሃድ ባለተጠበቀ ሁኔታ የት እንደሚገኝ ለእንግሊዝ ፖሊሶች ትልቅ ፍንጭ ሰጣቸው ። ፖሊሶቹም ግለሰቡ ወደ እንግሊዝ ተመልሶ እንደሚ መጣ በተሰፋ እና በምስጢር ሲጠባበቁት ቆይተው ባለፈው ነሃሴ 2015 እ ኤ አ ከ ሎንዶኑ አለማቀፉ የሂትሮው አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሰ ከ እጃቸው ወድቋል።
እንደ ኮቨንተሪ ቲሊግራፍ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ክሱን በሕግ ጥላ ስር ( በ እስር ቤት ) ሆኖ ሲከታተል የቆየው ተከሳሹ ማሃድ ሰሞኑን በዋለው ችሎት የቀደሞ የሴት ጉደኛውን በቡጢ በመማታት እና እካላዊ ጉዳት በማድረስ ፣ አጮኛውን በቢላዋ ለመግደል በመሞከሩ ፣ የአይን እማኞችን በማሰፈራራት ፣ የተከለከለ መሳሪያ (ቢላዎ )በሕዝዊ ስፍራ( አደባባይ )ይዞ በመገኘቱ እና የህግ አግባብን ለማዛባት ሲል አገር ጥሎ ወደ ኢትዮጵያ በመሰደድ ባደረጋቸው ጥፋቶቹ ተከሶ ግለስቡም ለ ቀረቡበት ክሶችን ጥፋተኛነቱን በማመኑ የ11 አመት እስራት ለሕዝብ ደህንነት (ጥበቃ) ሲባል የተጨማሪ 4 አመታት በድምሩ የ 15 አመት እስራት ተፈርዶበታል።
በአንድ ወቅት የልብ እና የፍቅር ጭምር ጓደኛው የነበረችው በሁዋልም ለተደራራቢ በደሎች የተዳረገችው የቀደሞ እጮኛው ከ ፍርድ ቤቱ ወሳኔው በሁዋላ ለዜና ሰዎች በሰጠችው አስተያየት”መቼም ይሁን መቼ ከእስራት ሰወጣ አንቺን አገድላለሁ፣ አንቺን ባጣ እንኳን ቤተሰቦችሽን እልምራቸውም በማለት ዝቶብኛል።” ስትል ግለሰቡ በእርሷ ላይ ያሳደረውን አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ፣ በቤተሰቦቿ ላይም የጣለውን ስጋት ገልጻለች።ታዲያ የህግ ታራሚው ሃማድ እስራቱን ሲጨርስ ዛቻውን ተግባራዊ ያድርገው አሊያም በተቃራኒው ከእስራቱ በመታረም ጥሩ ዜጋ በመሆን ወደ ማሕበረሰቡ ስለ መቀላቀሉ ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ይሆናል።

No comments:
Post a Comment