Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, February 21, 2016

‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ የሱዳኑን ድንበር ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር እንዲሆን አደረገ፡፡



‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ የሱዳኑን ድንበር ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር እንዲሆን አደረገ፡፡
====================================================
የወሓት አገዛዝ የሱዳን መንግስት በሽፍትነት ዘመኑ ለዋለለት ውለታ ምላሽና ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ጠረፍ ለጠረፍ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመግታቱ ረገድ የሚደረግለትን ትብብር ለማፅናት ከሁመራ እስከ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 1600 ኪሎ ሜትር ርዘማኔ ያለው፣ 30 ኪሎ ሜትር ደግሞ ወደ ውስጥ የሚገባ ሰፊና ለም መሬት ቆርሶ ሰጥቷል፡፡
መሬታቸው ተነጥቆ ለሱዳን በመሰጠቱ በ2002 ዓ.ም ብቻ 37 ባለሀብቶች ውልቃቸውን በመቅረት ተፈናቅለዋል፡፡
1. ነጋ ደስታ 21. ማማይ ሽፈራ
2. አስረሱ ደስታ 22. አጥናው አማረ
3. ተፈሪ 23. ኃይሌ ተክሌ /ቢራ/
4. ጌታቸው 24. ሀጎስ
5. ሰረበ 25. ካሳ እንዳለው
6. ቻሌ ፈንቴ 26. ቻሉ ኑራይኔ
7. አዳነ ባብል 27. ደምለው ኑራይኔ
8. ብርሃኔ ጌታቸው 28. ብዙነህ ፀጋ
9. መለስ አስማማው 29. ግርማው ተዘራ
10. ታፍሮ 30. ገ/መድህን መንግስቴ
11. ጌታቸው ግደይ 31. ጌታቸው ሐጎስ
12. አብርሃም 32. አርአያ
13. ንጉሴ ገ/ሊባኖስ 33. አሰማራው መኮንን
14. ሲሳይ ሽሬ 34. ጌጡ ማለደ
15. አበባው 35. ግደይ አቡሃይ
16. ጌታሁን ሽባባው 36. አለልኝ አጣናው
17. ንጉሴ 37. ፈጠነ አዳነ
18. በያን
19. ደለለኝ መንግስቱ
20. ስመኘው ብርሃኔ
ስለሆነም በአካባቢው ከፍተኛ ተቃውሞ በመነሳቱ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ግጭት፣ አለመረጋጋትና ውጥረት ሰፍኗል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ይህን የህዝብ ተቃውሞ ለመደፍጠጥ በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ከማስፈሩ ባሻገር የመሬቱን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጎታል፡፡
የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ክትትልና ቁጥጥር ዋና አዛዥ በሚል ብርጋዴር ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ ህዝብ የመጨፍጨፍ ሙሉ ስልጣን ከአገዛዙ ተሰጥቶታል፡፡ ኮሎኔል ተስፋዬ ዘውዴ የተሰኘው ህወሓታዊ ደግሞ የድንበር ጥበቃ ሻለቃ በሚል ሽፋን የተደራጀውን ገዳይ ቡድን እንዲያዝ ተመርጦ ማንኛውንም እርምጃ በህዝቡ ላይ እንዲወስድ መመሪያ ተሰጥቶታል፡፡
በተጨማሪም 24ኛ ክፍለ ጦር መሬቱ በተሰጠበት አካባቢ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በኮሎኔል ተስፋዬ ዘውዴ የሚመራው ረሻኙ ሻለቃ ጦር ድጋፍ ሲያስፈልገው እንዲሰጥ ከላይ ከአገዛዙ ጥብቅ ትዕዛዝ እንደተላለፈለት ታውቋል፡፡

‪#‎ምንጭ‬ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

No comments:

Post a Comment

wanted officials