Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 29, 2016

ኢሳትበሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ያሳፈረ ተሽከርካሪ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት ደረሰበት

በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ያሳፈረ ተሽከርካሪ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት ደረሰበት




(የካቲት 15 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ ወታደሮች አሳፍሮ በደቡባዊ ሶማሊያ ይጓዝ የነበረ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት እንደደረሰበት የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘገቡ።
ሊጎ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው የቦንብ አደጋ በርቀት መቆጣጠሪያ የተቀነባበረ መሆኑና በተሽከርካሪው ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱን ራዲዮ ሸበሌ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አስደምጧል።
በወታደራዊ ተሽከርካሪው ላይ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎም በኢትዮጵያ ወታደሮችና በአልሻባብ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንም የራዲዮ ጣቢያው አመልክቷል።
ይሁንና በሁለቱም ወገኖች ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ መረጃ አለመገኘቱን ያስታወቀው የራዲዮ ጣቢያው አልሻባብም ሆነ የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ሃይል በጉዳዩ ላይ ምላሽን ከመስጠት መቆጠባቸውን አክሎ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት በተናጠል በአልሻባብ ታጣቂ ሃይል ላይ እየወሰደ ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማጠናከር ሲል በቅርቡ ተጨማሪ አንድ ሺ ወታደሮችን ወደሶማሊያ ማሰማራቱ ይታወሳል።
ይኸው ወታደራዊ ሃይል በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ሶማሊያ በአልሻባብ ቁጥጥር ስር ያሉ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ውጊያን እያካሄደ እንደሚገኝ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ይገልጻሉ።
ኢትዮጵያ ከአራት ሺ በላይ የሆኑ ወታደሮችን በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ስር አሰማርታ ብትገኝም ቁጥሩ ይፋ ያልሆነ የተናጥል ወታደርን በማሰማራት ከአልሻባብ ጋር ውጊያን እያካሄደች ትገኛለች።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአምስት ሃገራት የተውጣጡ ከ20 በላይ ሰላም አስከባሪዎች በሶማሊያ የሚገኙ ሲሆን፣ ታጣቂ ሃይሉ ግን አሁንም ድረስ የሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ሆኖ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials