Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, February 14, 2016

ለሱዳን መሬት ተቆርሶ መሰጠቱን የተቃወሙ የጎንደር ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች በደህንነቶች እየታፈኑ አድራሻቸው በመጥፋት ላይ ነው፡፡

89acd-ethiopia-sudan-border-protest11-300x216


ህወሓት ከዚህ ቀደም ማለትም በ2002 ዓ.ም ቆርሶ ለሱዳን የቸረውን መሬት ለማፅናትና ሌሎችን ተጨማሪ ሰፋፊና ለም መሬቶች ለመስጠት ውስጥ ለውስጥ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ የተቃወሙና አገርና ህዝብን የመሸጥ ስውር ደባቸውን ያጋለጡ በርካታ ወጣቶችና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች በደህንነትና በታጠቁ ኃይሎች ታፍነው እየተወሰዱ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡
ታፍነው ተወሰወደው የት እንዳሉ የታዎቁት ሰዎችም ቢሆን በቤተሰብ እንዳይጠየቁ እገዳ ተጥሎባቸው የማያባራ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ፡፡
በምዕራብ አርማጭሆ ህዝብ ዘንድ የጎላ ተሰሚነት ያላቸው አቶ ኃይሌ ማሞ የተባሉት ግለሰብ ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠውን መሬት በሚመለከት ባሳዩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ምክንያት በቤተሰባቸውም ሆነ በአካባቢው ህብረተሰብ እንዳይጎበኙ ታግደው ሰቆቃና ግፍ በተሞላበት እስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ህወሓት ለሱዳን እየቆረሰ በመስጠት ለይ ከሚገኘው መሬት ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ያነሱና ያነሳሉ ተብለው የተገመቱ 50 የምዕራብ አርማጭሆ ነዋሪዎች ስም ዝርዝራቸው ወጥቶ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials