(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው አርብ በም ዕራብ አርሲ በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ የፌደራል ፖሊሶች ንጹሃን ዜጎችን ከገደሉ በኋላ በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎ በዛሬው ዕለት 8 የፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተሰማ:: ይህ የሟች ወታደሮች ቁጥር ሊጨምር ይችላል እየተባለም ነው::
ፖሊሶቹ ለተቃውሞ በወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥይት ተኩሰው ከገደሉና ካቆሰሉ በኋላ ሕዝቡ በዚህ በመቆጣት በፌደራል ፖሊሶቹ ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል:: በዚህም መሠረት በአደባባይ የወደቁት የፌደራል ፖሊሶች ሬሳ ሲጎተት እንደዋለና በየቦታው እንደወደቁም ተዘግቧል::
በም ዕራብ አርሲ አጄ ከተማ እንዲሁም በሻሸመኔ እና ሲራሮ ከተሞች ውጥረቱ እንዳለ ነው:: ሕዝብና የፌደራል ፖሊሶች ተፋጠዋል::
No comments:
Post a Comment