Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 15, 2016

የአየር ኃይሉ አብራሪ መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤርትራ በረሃ ላይ ይገኛል!

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ከባልደረባው መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ ጋር በመሆን ሰኔ 2 1997 ዓ.ም ኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በመያዝ የህወሓትን አገዛዝ ተቃውሞ ጅቡቲ ገብቷል፡፡

በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ ውጤት መጭበርበር በመቃወም ለሰልፍ አደባባይ የወጡ ኢትዮጵያዊያንን እንዲደበድብ ትዕዛዝ በመሰጠቱ ነበር ይህን እርምጃ የወሰደው፡፡

መቶ አለቃ አብዮት ከባልደረባው በኃይሉ ገብሬ ጋር በጅቡቲ መንግስት ነበር ለህወሓት ተላልፈው የተሰጡት፡፡ ከዚያም ለሦስት ዓመታት ያለምንም ፍርድ በስውር ቦታ ጨለማ ክፍል ውስጥ ታስረው ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ቆዩ… ቀጥሎም መቶ አለቃ አብዮት 15 ዓመት እና መቶ አለቃ በኃይሉ ደግሞ እድሜ ይፍታሽ እስር ተበየነባቸው፡፡

በመጨረሻም መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ አራቱን አመታት በዝዋይ እስር ቤት ሦስቱን ዓመታት ደግሞ በቃሊቲ ወህኒ ባጠቃላይ አስር የመከራ ጊዜያትን አሳልፎ ለመፈታት ቻለ፡፡ አብዮት እንደተፈታም ብዙ ሳይቆይ ወደ ኤርትራ በረሃ ወርዶ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሏል፡፡

መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው እንዴት ወደ ጅቡቲ እንደሄዱና ለ10 ዓመታት በህወሓት የተፈፀመበትን ግፍ፣ ሰቆቃና መከራ /የመቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬን ጭምር/ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ በዝርዝር ተናግሯል፡፡
12670063_1660011987572380_5819490915981918008_n

No comments:

Post a Comment

wanted officials