በሻሸመኔና ዝዋይ የተቀሰቀሰው ጸረ ወያኔ ተቃውሞ ተቀጣጥሏል ወደ መሃል ሃገር የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል
የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ የተያያዘውን ትግል ስም ለማጥቆር ሲል በብሄሮች መካከል የሃይማኖት ግጭት ያለ ኣስመስሎ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው።በደቡብ ኢትዮጵያ ሻሸመኔ የተነሳው ጸረ ሕወሓት ተቃውሞ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ከባሌ ተነስቶ ወደ መሃል ሃገር የሚያስገቡ መንገዶች ከመዘጋታቸው የተነሳ የአከባቢው የትራንስፖርት እና የመንግስት ስራዎች ግንኙነት ቆሟል:: እንዲሁም በዝዋይ ባቱ የተነሳው ተቃውሞ ተከትሎ የአግኣዚ ሰራዊት ወታደሮች ተማሪዎችን ሲያሳድዱ የተስተዋለ ሲሆን በከተማዋ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን በአከባቢው የተሰማሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ሪፖርት አድርገዋል::በምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ የ60 አመት አዛውንት የሆኑት ወይዘሮ ጁሃራ ሙሳ የተገደሉ ሲሆን እንዲሁም ሌላ አዛውንት ሴት ቆስለው በጋራሙለታ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ::በተጨማሪ መረጃ በዚሁ ወረዳ አደም አብደላ የተባለ ገበሬ መገደሉ ታውቋል:: በምጥራብ አርሲ ኮፈሌ አከባቢ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን በአከባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች የላኩት መረጃ ሲጠቁም የአግኣዚ ጦር ከዚህ ቀደም ሙስሊም ወንድሞቻችንን እንደጨፈጨፈው አሁንም የኮፈሌን ሕዝብ በተኩስ እያሸበረው እንደሚገኝ መረጃዎቹ ጠቁመዋል::በጠዋት በ6 ወታደራዊ ካሚዮን ተጭኖ ወደ ኮፈሌ የዘለቀው የአግኣዚ ጦር አከባቢውን እያሸበረው እንደሚገኝ ታውቋል::
No comments:
Post a Comment