Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, February 10, 2016

አንድ የመተማ ነዋሪ 6 የወያኔ ወታደሮችን ረሽኖ በመጨረሻ እራሱን በክብር አሰናበተ

ባሳለፍነው ሳምንት በመተማ ወረዳ ውስጥ ከቅማንት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለአማራ መብት ሲቆረቆር የነበረን ወጣት ለማፈን በአካባቢው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባሎች ወደ ልጁ ቤት ይሄዳሉ። ልጁ እጁን አልሰጠም ተኩስ ገጠማቸው ። እናም 6 ወታደሮችን ገደለ ። በመጨረሻም በእራሱ መሳሪያ እራሱን አጠፋ።
አካባቢው ላይ ለአማራነት የሚቆረቆሩ የተወሰኑ ወገኖቻችን ታስረዋል። እስረኞች ከአካባቢው ወጥተው ወደ ሌላ ቦታ እንዳይወሰዱ የታጠቁ ወገኖቻቸው በር በሩን ይዘው ሌት ተቀን በመጠበቅ ላይ እንዳሉ የቤተ አማራ ምንጮች አሳውቀዋል። ብዙ ልጆች መሳሪያ ታጥቀው ሸፍተዋል። የቅማንቱ ጉዳይ እንደገና ሊያገረሽ እንደሚችል ተፈርቷል። በሕወሓት የሚታገዙት የቅማንት ጠበቃ ነን ባዬች አሁንም ትንኮሳቸውን አለተውም።
የቴዎድሮስ አንበሶች ድንበራቸውን እና አማራነታቸውም በደማቸው አስከብረው ሊያልፉ ተዘጋጅተዋል።
የሞተውን ጀግና ወንድማችንን ነብስ ይማር!
!

No comments:

Post a Comment

wanted officials