Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, February 24, 2016

የኦሮሞን ትግል የሚመሩ ወጣቶች ቃል ገቡ “በማንኛውም ብሔረሰብና የግለሰብ ንብረት ላይ ጥቃት አናደርስም፤ ትግላችን ከስርዓቱ ጋር ነው”

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ለሻሸመኔ አቅራቢያ በሆነችው አባሮ መንደር የተደረገው ቃል ኪዳን ለሕወሓት መንግስት ትልቅ ኪሳራ ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች:: እንደፖለቲካ ተንታኞች ገለጻ የሕወሓት መንግስት የተለያዩ የሃይማኖት እና የብሄር ካርታዎችን እየመዘዘ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ለማሰናከልና ከሌላው ሕዝብ ጋር ለማቃቃር የሚሠራውን ተንኮል ያከሸፈ; ያሳፈረም ነው::


Screen Shot 2016-02-19 at 8.24.23 PM
ለሻሸመኔ ቅርብ በሆነችው አባሮ መንደር በተደረገ ይህንን ተቃውሞ በሚመሩ ወጣቶች ዛሬ ቃል በተገባው ቃል መሠረት የኦሮሞ ሕዝብ ትግል በስልጣን ላይ ካለው መንግስት ጋር እንጂ ከሌሎች ወንድማማች ሕዝቦች ጋር አይደለም:: የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከገዳዩ መንግስት ጋር ነው ሲሉ እነዚሁ ትግሉን የሚመሩ ሰዎች አብራርተው በቃል ኪዳናቸውም “ትግሉን ከሃይማኖት እና ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ሊያደርጉ የሚሞክሩ ካሉ የኦሮሞ ልጆች ሳይሆኑ ከሃዲዎችና የኦሮሞ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው” ብለዋል::
“በኦሮሚያ እየተደረገ ባለው ትግል ‘በማንኛውም ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት አናደርስም።’; ‘በማንኛውም የግለሰብ ንብረት ላይ ጉዳት አናደርስም።’ ሲሉ ቃል የገቡት እነዚሁ የትግሉ አራማጆች አብዮታችን በስር ዓቱ ላይ ነው ብለዋል::
ምንጭ: –

No comments:

Post a Comment

wanted officials