Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, February 28, 2016

ነፃነት በነፃ አይገኝም

አድ አዳማ ከኖርወይ (Add Adama from Norway).
በዚህ በአለንበት አለም ብዙ ነገሮች ነፃ ተብለው ሲታድሉ አይተን ይሆናል ነገር ግን ያ ነፃ የተባለው ነገር በፍፁም በነፃ የተገኘ አይድለም ቢያንስ እሱን ለማምረት የተከፈለ ዋጋ አለ። ስለዚህ ሁል ግዜ ነፃ የሚለውን ስንሰማ ከዛ በፊት የተከፈለ ዋጋ እንዳለ ማሰብ አለብን። ነፃነት ማለት ደሞ እስኪገኝ ድረስ የተወሰነ ትውልድን ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ከተገኘ በሗላ ደሞ በደንብ ለሚጠብቀው ማሕበረሰብ በሰላምና በፍቅር እያኖረ የሚያቆ ታላቅና ልዩ ሀይል ነው። ነፃነትን ማግኘት ደሞ የሚቻለው በአንተ ላይ እንዲሆን የማትፈልገውን ነገር በሌላ ላይ ሳታድረግና መብትን ለማስከበር የማይመችህን ነገር በሙሉ ከፊትህ ስታስወገድ ነው።በአሁኑ ሰአት ለኦሮሞ ሕዝብ የማይመቸው ነገር ቢንሮር ኢዲሞክራሲያዊ የሆነው የTPLF አገዛዝ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ይህ ከዚህ በፊት የተጠቀሰውን ነፃነት ለማምጣት ቆርጦ ተነስቶ በመላው ኦሮሚያ ባዶ እጁን በጭካኔያቸው ወድር ከሌላቸው የአጋዚ ወታደሮች ጋር ለአፉት 3 ወራቶች ተፋጧል አሁንም እየተፋጠጠ ነው ።
Oromo
በአሁን ሰአዓት መላው የኦሮሞ ሕዝብ ለነፃነቱ እየታገለ ያለው የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ዋጋዎች እየከፈለ ነው። ዛሬ በየትኛውም የስራ መስክ ያለ ኦሮሞ በልዩ ክትትል ስር ወድቁዋል, ይህ ልዩ ክትትል ግን ተቁዋሞውን አልገታው ይልቁንም አባሰው እንጂ። ዛሬ ለአቅመ አዳም የደረሱ ኦሮሞች እንደወጉ እንደባህላቸው ሆ ብለው ጨፍረው መጋባት የጥይት ውርጅብኝ ያስወርድባቸዋል። ታድያ በሰርጋችን ላይ ሰው ሞቶብናል ብለው ሐዘን አይደለም የተቀመጡት ይልቁንም ወቅቱ የሐዘን ሳይሆን የትግልነው ብለው ሬሳ ይዘው ቀጥታ ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ነው የተመሙት። ከየመስርያ ቤቱ ተመንጥረው ሲባረሩ፣ሲፈናቀለ እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሐገሪቷ ውስጥ ሕግና ስርዓት የለም በማለት ሕዝባዊ ተቁዋሞውን ነው የተቀላቀሉት። ያለምን ጥፋት እስርቤት በሚባለ የስቃይ ቦታ ተሰቃይተው ከወጡ በሗላ ወያኔዎች እንደሚሉት ልክ ገብተው ቁጭ አይደለም የሚሉት እንደውም አንድ በምዕራብ አርሲ የሚኖሩ አቶ በዳሶ የተባሉ ግለሰብ በቪኦኤ ትዝታ የሻሸመኔውን ተቃውሞ ለሚዲያ ስለተናገሩ ችግር ይደርስቦት ይሆን ብላ ስትጠይቃቸው “ችግርማ የልመድኩት ነው። ሰው ገላውን እታጠበ ሌላው ውሀውን ቢጨምርበት ሌል ምን የተለየ ነገር ይመጣበታል። ሕይወቴን በእስር ቤት ያሳለፍኩ ስለሆነ የፈለገው ቢመጣ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ሀቅ ከመናገር ወደሗላ አልልም” ሲሉ በማያወላዳ ሁኔታ መልሰዉላታል(ማዳመጥ ለምትፈልጉ ይህን ሊንክ ክፈቱ http://amharic.voanews.com/content/america-norway-england-issue-travel-warning-to-oromia-region/3195461.html)።ይህ ከላይ የተጠቀሰው ሁሉ ደሞ የሆነው የተለየ ሀፂያት ሰርተው ሳይሆን ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ነው ።ሌላው የሚደንቀው ነገር በአጋዚ ጥይት ተመተው ለመሞት የሚያጣጥሩት ውድ የኦሮሞ ልጆች የመጨረሻ ቃላቸው ታጋይ ይወድቃል ትግሉ ግን ይቀጥላል የሚል የጀግንነት ትምህርት ነው።
በአጋዚ ጥይት ሞት፣ በአጋዚ ጥይት መቁሰል፣ከስራ ገበታ መፈናቀል፣ የውሸት ፕሮፓጋንዳና ክሶችና የመሳሰሉት ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ትግልን ወደፊት ይገፋው ይሆናል እንጂ ፈፅሞ እንደማያቆመው የኦሮሞ ሕዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለወያኔዎች ነግሯቸዋል። ከዚህ በሗል የሐጎስ ጌትነት እና የጫላ ሎሌነት አክትሞዋል በማለት በማያሻማ መልኩ እየነገራቸው ይገኛል። ታዲያ ታላላቅ ውሽቶችን በመናገር የሚታወቀው የመንግስት አፈ ቀላጤው አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ሐቅ መዋጥ እየተናነቀው ሲያሻው በኦሮሚያውስጥ የተነሳውን ተቃውሞ ተቆጣጥረነዋል፣ ሲያሻ ደሞ ተቃዉሞው በሌሎች ብሔር ላይ ያተኮረ ነው፣ ሲያሻው ደሞ ተቃዉሞው እምነት ተኮር ነው፣ ሲያሻው ደሞ ተቃዉሞው የሚመራው በታጠቁ ጋንጎች ነው እያለ ደጋግሞ ሲቀባጥር ይሰማል። ለኔ እንደሚገባኝ ከሆነ ይህ የአቶ ጌታቸው አባባል አንድም ከቀቢፀ ተስፋነት የተነሳ ይሚመልሱት አልያም የፈለኩትን ብልስ ሚዲያው ያለው በጄ ነው የኢትዮዽያ ህዝብ ያለምንም አማራጭ እኔ ነው የሚያዳምጠው በሚል ይመስላል። ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ ለአቶ ጌታቸው ረዳና መሰሎቻቸው የሚለው ነገር ቢንሮ ይህ አላስፈላጊ መዘላበድ ፈፅሞ አያዋጣም። በአሁኑ ሰዓት የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነቱን ለመጎናፀፍ የሚያስፈልገውን መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው። በሆኑም ዛሬ በተንሹ የተጀመሩት እርምጃዎች እንደ እስረኛ ማስፈታት፣ መንገድ መዝጋት፣የኦሮሞ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ የተዝጋጁ ወታደራዊ ተቁዋማትን ማቃጠል፣ በኢንቨስትመንት ሰበብ በግፍ የተወሰዱ የእርሻ መሬት ማቃጠል ከመሳሰሉት አልፎ ወደ ተባብሰው ቀውስ ከመገባቱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የህዝቡ ጥያቄ ቅንጣት ታህል ሳትሸራረፍ መመለስ አለበት።
ዛሬም የኦሮሞ ህዝብ ትግል ብቻውን የትም አይድርስም የሚሉ አካሎች አሉ። ምናልባት የሌላው ሕዝብ አሁን መነሳት ትግሉን ያፋጥነውና ለወያኔ መከራዋን ይጨምርባት ይሆናል ።ይህ ማለት የኦሮሞ ሕዝብ ትግሎን አቁዋርጦ ሌላው እስኪነሳ መጠበቅ አለበት ማለት ደሞ አይደለም። እናም ሌላው ሕዝብ ተነሳም አልተነሳም ልክ ከዚህ በፊት እንደፃፍኩት ትግሉ ይቆማል የሚቆመውም ከድል በሗላ ብቻ ነው። ከመቼውም በላይ ነፃነት በነፃ እንደማይገኝ አውቆ ህፃን አዋቂ ተማሪ ገበሬ ሳይል ሁሉም የኦሮሞ ሕዝብ አስፈላጊውን መስዋእትነት እየከፈለ ይገኛል። ሰላማዊ ትግሉም እያደገ በአሁኑ ወቅት ቀላላል የሚባሉ እርምጃ መውሰድ ደረጃ ላይ ደርስዋል። እርምጃውም እንደ አስፈላጊነቱ ወያኔ እጅዋን እስክትሰጥ ድረስ ያድጋል ይቀጥል።ነፃነት በነፃ ስለማይገኝ መሬት ላይ ቁጭ ብላችሁ የተጀመረ ትግልን ከመተቸት ተቆጠቡ ወይ ደሞ እናንተም ታገሉ እላለሁ ።
የዘወትር ፀሎቴ ፈጣሪ የማይቀረውን ድል ያፍጥንልን!!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials