Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 23, 2016

ኑ፣ የአድዋን የድል በዓል በፌስቡክ እናክብር

ኑ፣ የአድዋን የድል በዓል በፌስቡክ እናክብር
‪#‎by‬ Eduardo Byrono
የአደዋን ጦርነት በተመለከተ ያላችሁን ምስሎች ፣ የምታውቁትን መረጃወች በመለጠፍ እና ያነበባችሁትን መጽሀፍ በመጠቆም ከ120 ዓመት በፊት አደዋ ዘምተው ሃይማኖታችንን ሊቀይር ባህላችንን ሊያጠፋ አገራችንን ሊወርስ እንደ ፍልፈል ድንበር ፈልፍሎ የመጣውን እስከአፍንጫው የታጠቀውን የጥሊያን ጦር ድባቅ መተው በኩራት ያለፉትን አያት ቅድም አያቶቻችን የዘመኑ ስልጣኔ ያበረከተውን ፌስቡክን በመጠቀም እናስታውሳቸው።
ይህን ከአዲስ አበባ ወደ አደዋ የሚተመውን ጦር የሚያሳይ ምስል “An old battle” በሚል ርዕስ ስር በአደዋ ጦርነት ጊዜ ኢትዮጲያ ውስጥ በነበረ ኦገስተስ ዋይልድ በተባለ እንግሊዛዊ የጦርሜዳ ጋዜጠኛ ከጻፈው መጽሀፍ ላይ የተወሰደ ነው።
ጉዞው ከአዲስ አበባ እስከ አደዋ ድረስ 13 ቀን እንደፈጀ የተለያዩ የታሪክ ጻሐፊወች ጽፈውታል። በጦርነቱ ከሞተው በመንገድ ላይ በተለያየ ድንገተኛ ህመም በረሃብ በውሃ ጥም ያለቀው ጦር እንደሚበልጥ የታሪክ አዋቂወች ይናገራሉ። አጤ ምንሊክ የአገሬ ሰው በምትችለው ሁሉ እርዳኝ ብለው በአዋጅ በተመጸኑት መሰረት መሳሪያ የሌለው ህዝብ ድንጋይ እና ሽመል ይዞ ወደ አደዋ መዝመቱ ተጽፎል።
አያ መብራቴ የተባለ የደብረብርሃን ሰው በአገሬ ምድር እኔ ባልኖርበት ሚስቴ እና ልጆቼ በነጻነት ይኖሩበታል ብሎ ከጅረት የለቀመውን አለት ታጥቆ ጭብጦ በስልቻው አጭቆ ወደ ፍልሚያው ጭው ባለ በረሃ እንደነጎደ በታሪክ ተነግሯል።
የአያ መብራቴ እጣፋንታ አይታወቅም እኛ ግን እናስታውሰዋለን።

No comments:

Post a Comment

wanted officials