Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, February 18, 2016

ሰልፈኞች ንብረትነቱ የሕወሓት የሆነ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ አቃጠሉ – ወደ አ.አ. የሚያገናኙ መንገዶች በ20 አቅጣጫዎች በሰልፈኞች መዘጋታቸው ተሰማ

ሰልፈኞች ንብረትነቱ የሕወሓት የሆነ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ አቃጠሉ – ወደ አ.አ. የሚያገናኙ መንገዶች በ20 አቅጣጫዎች በሰልፈኞች መዘጋታቸው ተሰማ

ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ስም ከፍቶት ሆንም ግን አንዳችም ቀን የትግራይን ሕዝብ ጠቅሞ የማያውቀው ኤፈርት ስር የሚገኘው ይኸው የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት ቦቴ በሰልፈኞች ከተቃጠለ በኋላ ወደዚያው ለመንዳት የሚፈልጉ ሹፌሮች ስጋቱ እንዳየለባቸው ለማወቅ ተችሏል::
ይህ የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆነው ቦቴ መኪና የተቃጠለው ባቱ ከተማ ውስጥ ነው::
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የሚያስኬዱ በርካታ መንገዶች በሰልፈኞች መዘጋታቸው ተሰምቷል:: በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ 20 አካባቢዎችሕዝብ መንገድ ዘጋግቶ ተቃውሞውን እየገለጸ ባለበት በዚህ ሰዓት የአጋዚ ሰራዊት መንገዶችን ለማስከፈት ወደ ህዝቡ እየተኮሰ እንደሚገኝ የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ::
እንደ መረጃዎች ከሆነ በአሁኑ ወቅት በነዚህ መንገድ በተዘጋጋባቸው አዲስ አበባን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በሚያገናኙ መንገዶች ማንናውም መኪና የማይተላለፍ ሲሆን የጸጥታ ስጋቱም እንዳየለ ነው::
Oromo

No comments:

Post a Comment

wanted officials