ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በመንግስት ድጋፍና ቅስቀሳ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ብዙዎችን እያስቆጣ ነው።
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰልፉ ጋር በተያያዘ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጣቸውን እየገለጹባቸው ካሉት ምክንያቶች መካከል አንደኛው በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግድያ ለመቃወም ባዲስ አበባና በአንዳንድ ከተሞች ለማድረግ ያቀረቡት የሰልፍ ፈቃድ ጥያቄ በተከለከለበት ሁኔታ፤ መንግስት “ወልቃይት -ትግራይ ናት” የሚል ሰልፍ በማስደረጉ ነው።
ይህም በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ ህዝቦች በሁለት አይነት ህግ እንደሚገዙ የሚያሳይ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ገዥው ፓርቲ አንድኛውን ልጅ-ሌለኛውን የእንጀራ ልጅ አድርጎ የሚያሳየው ሆን ብሎ በህዝቦች መካከል ጥላቻን ለመፍጠር ከሚከተለው የመከፋፈል ፖሊሲው በመነሳት ነው ብለዋል።
ሌላው አስተያየት ሰጭዎቹን ያስቆጣው ነገር ሰልፈኞቹ የያዟቸው መፈክሮች የኢትዮጰያውያንን ጨዋነነት፣ መከባበርና አብሮ የመኖር ባህል የሚንዱ መሆናቸው ነው።
እነኚሁ በመንግስት ፖሊሶች ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገላቸው “ወልቃይት የትግራይ ናት” እያሉ ሰልፍ የወጡት ስዎች ባደባባይ ከያዟቸው መፈክሮች መካከል አንዱ ፦” አተነካኩነ! ት እግሰታችንን አታስጨርሱን! ትእግስታችን ካለቀ ግን የምንሰጣችሁን ምላሽ ታውቁታላችሁ!!” የሚል ነው።
ሰልፉ የተዘጋጀውም ሆነ ይህ የእብሪት መፈክር የተጻፈው “እኛ ወልቃይቶች አማራዎች እንጂ ትግራዮች አይደለንም!” እያሉ በመታገል ላይ ያሉትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወልቃይቶችን ለመቃወም መሆኑ ግልጽ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ በ አነደ ታላቀ ሀዘበ ላይ በዚህ ደረጃ መሳለቅ ተዋልዶና ተጋብቶ በሚኖረው ህዝብ መካከል የማይጠፋ እሳት መለኮስ ነው ብለዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ በመጨረሻም፦”የዚህ አይነት ተንኮለኛ ስርዓት ለትግራይም ሆነ ለተቀረው ህዝብ የማይበጅ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጰያዊ እጅ ለ እጅ ተያይዞ ሊያስቀግደው ይገባል” ብለዋል።

No comments:
Post a Comment