ኢሳት ዜና ፦ በቀጣዮቹ ሶስት ወራቶች ውስጥ አለም አቀፍ
እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መላክ ካልጀመረ ከ10 ሚሊዮን ሰዎች ለእለት የሚበሉት እንዳማይኖራቸው የተባበሩት መንግስታት
ድርጅት በድጋሚ አሳስቧል። የበጋ ወቅቱ እየተጠናከረ መምጣቱንና የእርዳታ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት የድርቁ
አደጋ ወደ አሳሳቢና አስከፊ ድረጃ እየተሸጋገረ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ
የተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎችም የግንቦት ወር ከመግባቱ በፊት አለም አቀፍ እርዳታ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ
የተባበሩትመንግስታት ድርጅት አመልክቷል። ይሁንና ለዚሁ ድጋፍ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብም በቂ ምላሽ አለመገኘቱ
ስጋትን ፈጥሮ እንደሚገኝ የድርጅቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው የአለም አቀፍ
ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ የእርዳታ ጥሪ በቂ ምላሽ ባለመስጠታቸው የድርቁ አደጋ ትኩረት እየሳበ መምጣቱን በመግለጽ ላይ
ሲሆን፣ አንዳንድ የእርዳታ ተቋማት ድርቁ ወደ ረሃብ ሊለወጥ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩንም አስታውቀዋል።
No comments:
Post a Comment