Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, February 13, 2016

“እናት ከ3 ቀን በኋላ በቤቷ ሞታ ተገኘች፣ህፃን ልጇ ግን የቡና ዱቄት እየተመገበ በህይወት መገኘቱ ብዙዎችን አስገርሟል”

እናት የልጇን ሁለተኛ አመት የልደት ቀን ልታከብር ሽር እንጉድ በምትልበት ወቅት፣
አገር ሰላም ሰፈር አማን ብላ ለእዚህ ለአንድ ፍሬ ልጇ እና ለእሷ የልደት ማክበሪያ ልብስ ገዛዝታ ጥር 8ቀን አመሻሽ ለይ ልጇን አዝላ ጀሞ ኮንደሚኒየም በሚገኘው የመኖሪያ ቤቷ እንደገባች ሰማን።
ነገር ግን ጥር 9/2008 ዓ/ም የእዚች መልከ መልካም ሴት ቤት አልተከፈተም ወተት አምጭዋ መጥታ ብታንኳኳ አቤት የሚል ድምፅ ጠፋ ወተት አምጭዋም በመጣችበት እግሯ የህፃኑን ወተት መልሳ ይዛው ሄደች፣
በ3ኛ ቀኑ ግን በአስራት መሰወር ግራ የተጋባችዋ ወተት አመላላሽ አስራት ቤት አካባቢ የሚሸት እንዳለ ለጎረቢት ተናገረች።
ጎረቢትም ግራ በመጋባት ስሜት ሁኔታውን ለፖሊስ አመለከተ።
ፖሊስም የአስራትን ቤት ሰብሮ ገባ
ያልተጠበቀ ክስተት እና ሁሉንም ጎረቢት ያስደነገጠ ነገር ታዬ።
እናት አስራት አይወድቁት አወዳደቅ ወድቃ ሞታ ተገኘች።
በተዘጋ ቤት ውስጥ ምንም በሌለበት ገና ምኑንም የማያውቀው አንድ ፍሬ ህፃን እናቱ ለዘላለም ላትመለስ ጥላው ስትሄድ እሱ ግን አስከሬኗን ከፊቱ እያዬ ማልቀስ ደክሞት አይኖቹን እያቁለጨለጨ በባዶ ቤት ውስጥ ተገኘ።
ይህ ልጅ ለሶስት ቀናት የቆየው በቅርቡ ያገኘውን የተፈጨ የቡና ዱቄት እየተመገበ እንደሆነ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች አጫውተውኛል።
እኔም ይሄን አሳዛኝ ታሪክ ከሰማሁ ጀምሮ አስራት እንዴት ሞተች?ከሞተች በኋላስ እንዴት ሶስት ቀን ቆየች?የሚሉት ጥያቄዎች ተፈጥረውብኛል የጀሞ አካባቢ ፖሊስ ግን ምርመራውን አጠናክሮ እንደቀጠለ ሰምቻለሁ።
የምስኪኗ እህታችን አስራትም የቀብር ስነ ስርአቷ የጥምቀት በአል እለት ተፈፅሟል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials