Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 8, 2016

ሃገርና ቅርስ ሽያጩ ይቁም!! – በኢየሩሳሌም የሚገኘዉ ንግሥት ዘዉዲቱ ህንፃ


Jerusalem123-satenaw.jpg (277×169)
ሃገር ቅርስ ነዉ ቅርስ ሃገር ነዉ፡፡ ቅርስ ሲሸጭ አገር እና ማንነት አብሮ ይሸጣል፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ለዚህ ትዉልድ ብዙ ታሪካዊ ቅርሶችን አዉርሰዉን አልፈዋል፡፡ ይህን አኩሪ ታሪክ እና ቅርስ የተረከብን ትዉልዶች በዚህ ዘመን ከማህጸኗ ለወጡ የእንግዲህ ልጆች የአገራችንን ቅርስና ክብር አሳልፈን በመስጠታችን  የአገራችን ህልዉና በከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ ይህ ከአንድ ጎጥ የተፈለፈለ የማፍያ ቡድን ከባዕዳን ጋር በመመሳጠር የኢትዮጵያን የረዥም ታሪክ እና ዓለም አቀፋዊ ክብር በማጥፋት ይኸዉ ለ25 ቆይቷል፡፡ በአገር ዉስጥና እጁ በሚደርስበት ሥፍራ ሁሉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉነትን በማጥፋት ዘመቻ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ ይኸዉም ኢትዮጵያ በረዥም ጊዜ ታሪካዊ ትስስር ካላቸዉ  አገሮች አንዷ እስራኤል ነች፡፡ ይህች አገር የዓለማችን የፖለቲካ እና የሃይማኖት እንብርት ነች፡፡ ከእስራኤል የሚነሳ ነፋስ በሁሉም አገር በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ሁሉንም ያነቃንቃል፡፡  ለዚህም ቀደምት ኢትዮጵያዉያን ነገስታትና የነገስታቱ ቤተሰቦች በተለያዬ መንገድ አገራቸዉን የሚያስጠራና የሚያኮራ ቅርስ በዚች የዓለም እንብርት ጥለዉልን አልፈዋል፡፡
ከነዚህም በንግሥተ ሳባ፣ አጼ ዮሐንስ ፣አፄ ሚኒሊክ፣ንግስት ጣይቱ፣ንግስት ዘዉዲቱ፣ አፄ ሃይለስላሴ እና ብዙ የነገስታቱ ቤተሰቦች በኢየሩሳሌም ለሚገኘዉ የኢትዮጵያ ገዳም ያወረሱትና በከፊል በመንግሥት ደረጃ የሚተዳደሩ ጥንታዊ ቦታዎችና ቅርሶችን ጥለዉልን አልፈዋል፡፡  ከነዚህ ቅርሶች መካከል የኢትዮጵያ ህዝብ ባላወቀዉ መልኩ የተሸጡ አሉ አሁንም በስፋት ለመሸጥ የተዘጋጁ እንዳሉ ፍንጮች እየወጡ ነዉ፡፡ ለዚህም ለማስረጃ ያክል የአጼ ሃይለስላሴ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ወደ እንግሊዝ ከመሄዳቸዉ በፊት አርፈዉበት የቆዩበትን ቤትና ቦታ የንጉሳያኑ ቤተሰብና የኢትዮጵያ መንግሥት  የይገባኛል ክርክር ለብዙ ዓመታት ሲካሄድ ቆይቶ በንጉሳዉያኑ ቤተሰብ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ የንጉሳያኑ ቤተሰብ  1.5 ሚሊዮን ዶላር ለባእዳን  አሳልፈዉ ሽጠዉታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከ30 ዓመታት በኢየሩሳሌም ምእመናን ማህበር በተሰባሰቡ ኢትዮጵያዉያን የተገዛ ቤት እና የብዙ ኢትዮጵያን በሐዘንና በማህበራዊ ጉዳዮች የሚገናኙበት ቤትም ያለምንም ካሳ ተወስዷል፡፡
የንጉሳዉያኑ ጠበቃ የነበረዉ በተዘዋዋሪ እራሱ ህንጻዉን ከገዛ በኋላ በአሁኑ ወቅት ይህን ቦታ በ11 ሚሊዮን ዶላርለሽያጭ አቅርቦት ይገኛል፡፡ የዚህ ቦታ ያለአግባብ በመሄዱ በምንቆጭበት ስዓት የኢትዮጵያ መንግሥት በአንባሳደር ህላዌ እና በገዳሙ ዉስጥ በተሰገሰጉ የህዋት መነኮሳት ጋር በመመሳጠር በ1928 እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር የታነጸዉን የእቴጌ ዘዉዲቱ ህንፃ ንግስቲቱ በዘመኑ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ለነበሩ ቅዱሳን አባቶች ድጋፍ ይሆን ዘንድ ከህንጻዉ ከሚገኘዉ ኪራይ ሲሶዉን እንዲተዳደሩበት ለኢትዮጵያዉያን በቅርስነት ያስረከቡትን ህንጻ በእድሳት ስም በብዙ ሚሊዮን ዶላር በሚስጢር በመሸጥ ለገዥዎቹ ለማስረከብ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ ቀደም ሲል ወያኔ ይህን ታሪካዊ ህንፃ ለመሸጥ በተደጋጋሚ ለገዳሙ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም በወቀቱ በነበሩ አባቶች ጥንካሬ እየተከላከሉ እስካሁን ደርሷል፡፡
የህወሀት መንግሥት ይህን ለማድረግ ለምን ፈለገ ለሚለዉ ቅርሱ በኢትዮጵያዉያን የቆመ እና ኢትዮጵያን የሚወክል በመሆኑ ይህን ማጥፋት የግድ ስለሚለዉ ብቻ ነዉ፡፡ ሁሉም ነገር በራሱ ዘዉግ ብቻ የቆመ እና በራሱ ዘዉግ እንዲኖር የሚፈልግ ጠባብና ስግብግብ ቡድን እንጂ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሌለዉ በመሆኑም ጭምር ነዉ፡፡ ይህን ከዳር ለማድረስ የራሱን ዓላማ አስፈጻሚ መነኮሳት በገዳሙ ዉስጥ እና ከዉጭ ሌሎች ኃላፊነት የጎደላቸዉን ሰዎች በማደራጀት የቅርስ ሽያጭ ዓላማዉን ለማስፈጸም ከመጨረሻዉ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ህወሃት በአገር ዉስጥ እና በአገር ዉጭ ሃገርንና ቅርስን እንዲሁም ህዝብን  በማጥፋት ተግባር  ላይ ተጠምዶ  ይገኛል ለዚህም በአሁኑ ስዓት በኦሮሞ እና በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለዉን መመልከት በቂ ነዉ፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዉያን ዘርና ሃይማኖት ሳይለየን አገርንና ቅርሳችንን ከህወሃት ጥፋት ለማዳን ሁሉም በአንድነት መነሳት እንዳለበት ሊታመን ይገባል ለዚህም፡-
1/ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ደም እና አጥንት ገብረዉ ያስረከቡንን ቅርስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጠበቅና ጠብቆም ለትዉልድ የማስረከብ ኃላፊነት እንዳለባት በመረዳት የበኩሏን ድርሻ መወጣት ይገባታል፡፡ ይኸዉም አብዛኛዎቹ ቅርሶች በቤተ ክርስቲያኗ ስም ስለሚገኙ እና በመነኮሳት ስም በዘርና በጎጥ ተደራጅተዉ በገዳሙ ላይ እና በቅርሱ ላይ እያደረሱ ያሉት ጥፋት ከፍተኛ እንደሆነ በመንበሩ ላይ የተቀመጡት አቡነ ማቲያስ በሚገባ የሚያዉቁት በመሆኑ የተሸከሙትን ሃላፊነታቸዉን በመዘንጋት ለሚደርሰዉ ጥፋት ታሪክ ይቅር የማይለዉ እና ለዚህ ቅርስ መጠበቅ ብለዉ ህይወታቸዉን ባጠፉት አባቶች ነፍስ በእግዚአብሔርም የሚያስጠይቅ መሆኑን መረዳት ይገባል “ፈሪሃ እግዚአብሔር እና ዕምነት ካለ ?”፡፡
2/  በእስራኤል የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ቤተ እስራኤላዉያን በአንድ በመተባበር በጉዳዩ ላይ ግልጽ ማብራሪያ  ከሚመለከታቸዉ አካላት መጠየቅ የደረሱበትን ለህዝብ ማሳወቅ ግድ ይላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እራሳቸዉን በማደራጀት በእስራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያዉያን ቅርሶች በዝርዝር መያዝ እና ለወደፊት ህገወጥ ሽያጭ እንዳይካሄድ በህግ የሚታገድበትን መንገድ ማፈላለግ ተቀዳሚ ተግባራቸዉ ሊሆን ይገባል፡፡
3/ በመላዉ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በተለይ የኢትዮጵያ ቅርስና ባለአደራ ጠባቂ እንዲሁም ሌሎች መንግስታዊ  ያልሆኑ ድርጅቶች እራሳቸዉን በማቀናጀት በእስራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያዉያን ቅርሶች የሚጠበቁበትን መንገድ ማመቻቸት እና አሁን ለሽያጭ በቀረበዉ የንግስት ዘዉዲቱ ህንጻ ላይ ተቃዉሟቸዉን ለእስራኤል መንግስት ማሳወቅ አስፈላጊ ነዉ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!
ጽናት ዘላለም
Source-zehabesha.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials