5 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ
በሃዋሣ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ የገቡ 3 ህፃናት ህይወታቸው አለፈ፡፡ ዕድሜያቸው 8‚ 12‚ እና 14 የሚሆናቸው ህፃናት፤ በሽቦ አጥር በተከለለው የዩኒቨርሲቲው የቆሻሻ ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ በአጥር ተንጠላጥለው በመግባት ለመዋኘት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ወደ ፍሳሽ ማጠራቀሚያው የገቡት አራት ህፃናት ሲሆኑ ከሁለት መንትያ ወንድማማቾች መካከል አንደኛው ወደ ማጠራቀሚያ ውስጥ ሳይገባ በመቅረቱ ህይወቱ የተረፈ ሲሆን፤ የስምንት አመቱ ህፃን መንትያ ወንድሙን ጨምሮ ሁለት ጓደኞቹ በገንዳው ውስጥ ገብተው በመቅረታቸው ሁኔታውን ለሰዎች ነግሮ፣ የህፃናቱ አስከሬን ከገንዳው ውስጥ ሊወጣ ችሏል፡፡
የህፃናቱ የቀብር ስነስርዓት ከትናንት በስቲያ በስላሴ ቤተክርስቲያን የተፈፀመ ሲሆን በህፃናቱ ሞት የአካባቢው ነዋሪዎች በእጅጉ አዝነዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለፍሳሽ ማጠራቀሚያ ባዘጋጀው ገንዳ ውስጥ የተጠራቀመውን ፍሳሽ እያጣራ መልሶ ለአገልግሎት እንዲውል በሚያስችል ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፤ ማጠራቀሚያው ግን በበቂ ሁኔታ በአጥር ተከልሎና ጥበቃ ተመድቦለት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባ ነበር ብለዋል፡፡
ስለጉዳዩ እንዲነግሩን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
በሌላ በኩል ከሰሞኑ ርዕደ መሬት ጋር በተያያዘ አዋሣ ዩኒቨርሲቲ ለ15 ቀናት በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 5 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትናንት ዝዋይ ላይ በተፈጠረ መኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡

No comments:
Post a Comment