Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 15, 2016

የኢትዮጵያ ስደተኖች ማህበር ሊቀመንበር ከስውዲን ሃገር ለቀው እንዲወጡ የስውዲን ኢምግሬሽን ቦርድ ወሰነ። ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖችን አስቆጥቶል።

የኢትዮጵያ ስደተኖች ማህበር ሊቀመንበር ከስውዲን ሃገር ለቀው እንዲወጡ የስውዲን ኢምግሬሽን ቦርድ ወሰነ። ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖችን አስቆጥቶል።
አቶ ኤፍሬም አክሊሉ የኢትዮጵያ ስደተኖች ማህበር ሊቀመንበር ከመሆናቸዉም በተጨማሪ ምንም እንኩዋን በአም ሃገራት ተቀባይነትን ባያገኝም በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ አርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን ድርጅቱ በሚያካሂዳቸዉ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ በከፍተኛ ንቃትና ተሳትፎአቸዉ የሚታወቁ ሲሆን በስዊድን ሃገር የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ በተመሰረተው ክስ ላይም የጎላ ተሳትፎ ማድረጋቸዉ የአደባባይ ምስጢር ናቸዉ።
አቶ ኤፍሬም አክሊሉ በስዊድን እስቶኮልም እና በአከባቢው በሚደረጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳታፊ በመሆን በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ የተንሰራፋውን እጅግ አስከፊ አንባገነናዊ አገዛዝ ከሃገራችን እንዲነቀል ባለበት ሃገር በሙሉ አቅማቸዉ የሚሰሩ ጠንካራና ፀኑ አላማ ያነገቡ የግፈኛዎች እራስ ምታት የሆኑ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ  በዚህም ምክንያት ግፈኛዉ ኢትዮጵያ መንግስት በስዊድን ሀገር በሚገኘዉ ኤንባሲዉ አማካኝነት ከዚህ ስራቸዉ እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ የማስፈራራት ጥረቶችን ማድረጉ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ኤንባሲዉ በሚያዘጋጃቸዉ ማናቸዉም ዝግጅቶች ላይ እንዳይገኙ እቀባ ተደርጎባቸዋል። እንደማሳያነትም  በ12/12/2015 ቀን የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባዘጋጀዉ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ አቶ ኤፍሬም እንደ አንድ ዜጋ በቦታዉ በተገኙበት አጋጣሚ በአንባሳደር ወይንሸት ታደሰ ቀጥተኛ ትእዛዝ የኤንባሲ ቅትረኞች ክብራቸዉን በማዋረድ ስብናቸዉን በመግፈፍ ከአዳራሽ ተጎትተዉ እንዲወጡ መደረጉ የቅርብ  ጊዜ ተዝታ ነዉ።
በዚህ ደረጃ በኢትዮጵያ አንባገነናዊ መንግስት የሚፈለን ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ማለት ለጅብ ስጋ እንደማቅረብ ነው! ይህ ፍፁም ሰብዓዊነት የጎደለው እና ኤፍሬም አክሊሉ ለግፈኛ ጨቃኝ መንግስት ለሞት አሳልፎ የሚሰጥ ውሳኔ ለሰብአዊነት ትኩረት ከምትሰጥ ሃገር ስዊድን የማይጠበቅ ነው።  ይህም የዓለም አቀፍ የስደትኞች መብትን የሚፃረር ከመሆኑም በላይ በስውዲን ሀገር የተወለዱ ልጆቹን ከአባታቸው ጋር አብረው የመኖር መብትንም የሚጋፋ ነው።
የኢትዮጵያ የስደተኖች ማህበር በሊቀመንበሩ ላይ የስዊድን ማይግሬሽን ቦርድ የወሰነውን ውሳኔ አጥብቆ የቃወማል ጉዳዩንም በጥሞና ተመልክቶ ውሳኔውን  እንደሚቀይር እምነቱ የፀና ነው።
Source
http://www.esmsweden.org/news/

No comments:

Post a Comment

wanted officials