(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ የመጡበትን ሥራ አጠናቀው ወደ አስመራ ተመለሱ::
ሊቀመንበሩ ባለፈው ቅዳሜ በካናዳ ቶረንቶ ከተማ ከተመረጡ የየከተማው የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ጋር ዝግ ስብሰባ አድርገው ነበር:: ድርጅታቸው ከዚህ ዝግ ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫም የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን አስታውቋል::
የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ዛሬ አስመራ በሰላም መግባታቸው የተረጋገጠ በፊት በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደአስፈላጊነቱ ከአስመራ ወደ ሌሎች ሃገሮች በፈለጉት ሰዓት ለሥራ ጉዳይ እንደሚወጡና እንደሚገቡ መግለጻቸው ይታወሳል::
ሕወሓት የሚያዛቸው ሚድያዎች ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለለአጭር ጊዜ የሥራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ ከመጡ በኋላ “በቃ አይመለሱም አንደኛቸውን ነው የመጡት” በሚል ሰፊ ፕሮፓጋንዳ መክፈታቸው ይታወሳል::
No comments:
Post a Comment