Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, February 10, 2016

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ ተጠየቀ!!!

በኢትዮጵያ ውስጥ አላግባብ የሕዝብን ሃብት ከሕወሓት መንግስት ጋር በመተባበር ዘርፈዋል እየተባሉ በሰፊው ተቃውሞ የሚቀርብባቸው ሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆነውን ፔፕሲን እና የፔፕሲ ምርቶችን ሕዝቡ ያለመጠጣት ተአቅቦ እንዲደረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ::
በሶሻል ሚድያዎች እና በስልክ መል ዕክቶች በሃገሪቱ በሰፊው እየተካሄደ ባለው በዚህ ቅስቅሳ ‘ቦይኮት ፔፕሲ’ የሚል ጽሁፍ ያለበት እና ከአጠገቡም የአላሙዲን ምስል ያለበት ነው:: የዚህ ቅስቀሳ አስተባበሪዎች በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ሕዝብን እንቅስቃሴ እያካሄደ ያለው ሕዝብ መሆኑ ታውቋል::
በአማራ ክልል ከዚህ ቀደም አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ሕዝብ በስብሰባ ላይ ክብሩን በሚነካ መንገድ ከተሳደቡ በኋላ ሕዝቡ የብ አዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን አንጠጣም በሚል ቦይኮት መጥራቱ ይታወሳል:: አሁን አላሙዲ በኦሮሚያ የወርቅ ማዕድኑን ሳይቀር መውሰዳቸውን ተከትሎ በተጠራው ሕዝባዊ የአላሙዲንን ምርቶች የመጠቀም እቀባ በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል ይጠበቃል ተብሏል::
በሶሻል ሚድያዎች እና በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ሕዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ/ መጠጣት እንዲያቆም የሚጠይቀው በራሪ ወረቀትን ከላይ ለግንዛቤ አቅርበነዋል::
በምርቶች ላይ ያለመጠቀም ተአቅቦ (ቦይኮት) የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል መሆኑን ፖለቲከኞች ያሰምሩበታል:

No comments:

Post a Comment

wanted officials