(ዘ-ሐበሻ) ምዕራብ አርሲ በተለያዩ ከተሞች የተቀጣጠለው የሕዝብ አመጽ ዛሬ በኮፋሌ እና በዋቤ ከተሞች ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ::
በተለይ በኮፋን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኘውና ሌሎች መንገዶች ሙሉ በሙሉ በሰልፈኞች የተዘጋ ሲሆን የፌደራል ፖሊስም በሰልፈኞቹ ላይ እርምጃ ቢወስድም ተቃውሞውን ሊያስቆመው እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች አስታውቀዋል::
የድንጋይ መከላከያ የለበሱና ጠመንጃ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት የኮፋሌ ከተማን ቢወሯትም የህዝቡን ቁጣ ማቆም ተስኗቸዋል::
በተመሳሳይ በቡሌ ሁራም እንዲሁ የህዝቡ ተቃውሞ ቀጥሏል::
የፌደራል መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት በቴሌቭዥን ወጥተው በኦሮሚያ የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ ተቆጣጥረን አስቁመነዋል ቢሉም ዛሬም በተለያዩ ከተሞች የሕዝቡ ቁጣ አይሎ ውሏል::
No comments:
Post a Comment