Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 31, 2015

Police suspects journalist Getachew Shiferaw and four others inciting violence through social media

Court grants the police twenty eight days in the case against journalist Getachew Shiferaw and four Blue party members ,
Detainees to be charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism proclamation.
A court in Addis Abeba has today granted the police investigating the case of Getachew and three members of Blue party 28 more days to further investigate detainees.
According to the party’s online publication Negere Ethiopia, police suspects the detainees inciting violence through the social media and recruiting for Genbot 7, an opposition party in arm struggle.
- See more at: http://www.satenaw.com/ethiopia-police-suspects-journalist-getachew-shiferaw-and-four-others-inciting-violence-through-social-media/#sthash.hRne4Iu5.dpuf
Court grants the police twenty eight days in the case against journalist Getachew Shiferaw and four Blue party members ,
Detainees to be charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism proclamation.
A court in Addis Abeba has today granted the police investigating the case of Getachew and three members of Blue party 28 more days to further investigate detainees.
According to the party’s online publication Negere Ethiopia, police suspects the detainees inciting violence through the social media and recruiting for Genbot 7, an opposition party in arm struggle.
- See more at: http://www.satenaw.com/ethiopia-police-suspects-journalist-getachew-shiferaw-and-four-others-inciting-violence-through-social-media/#sthash.hRne4Iu5.dpuf
getachew-1-720x445


Court grants the police twenty eight days in the case against journalist Getachew Shiferaw and four Blue party members ,
Detainees to be charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism proclamation.
A court in Addis Abeba has today granted the police investigating the case of Getachew and three members of Blue party 28 more days to further investigate detainees.
According to the party’s online publication Negere Ethiopia, police suspects the detainees inciting violence through the social media and recruiting for Genbot 7, an opposition party in arm struggle.
- See more at: http://www.satenaw.com/ethiopia-police-suspects-journalist-getachew-shiferaw-and-four-others-inciting-violence-through-social-media/#sthash.hRne4Iu5.dpuf

Ethiopia: Police suspects journalist Getachew Shiferaw and four others inciting violence through social media

 

Court grants the police twenty eight days in the case against journalist Getachew Shiferaw and four Blue party members ,
Detainees to be charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism proclamation.
A court in Addis Abeba has today granted the police investigating the case of Getachew and three members of Blue party 28 more days to further investigate detainees.
According to the party’s online publication Negere Ethiopia, police suspects the detainees inciting violence through the social media and recruiting for Genbot 7, an opposition party in arm struggle.

Ethiopia: Police suspects journalist Getachew Shiferaw and four others inciting violence through social media

getachew-1-720x445
1
Share
0
 
1
 
1
Share

 Court grants the police twenty eight days in the case against journalist Getachew Shiferaw and four Blue party members ,
Detainees to be charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism proclamation.
A court in Addis Abeba has today granted the police investigating the case of Getachew and three members of Blue party 28 more days to further investigate detainees.
According to the party’s online publication Negere Ethiopia, police suspects the detainees inciting violence through the social media and recruiting for Genbot 7, an opposition party in arm struggle.
- See more at: http://www.satenaw.com/ethiopia-police-suspects-journalist-getachew-shiferaw-and-four-others-inciting-violence-through-social-media/#sthash.hRne4Iu5.dpuf

በድርቁ ምክንያት 400ሺ ህጻናት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸው፣ አንድ ሚሊዮን ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ

1796634_222183061305326_875283870_n



በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከ 400ሺ የሚበልጡ ህጻናትን ለአሳሳቢ የጤናና የአካል ችግር አጋልጦ እንደሚገኝና ጉዳት የሚደርስባቸው ህጻናት ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።
ለተረጂዎች የሚያስፈልገው ድጋፍ በበቂ ሁኔታ በመቅረብ ላይ አለመሆኑ ችግሩን እያባባሰው እንደሆነም ድርጅቱ ገልጿል። ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን ሰዎች መካከል ወደ ግማሽ የሚጠጉት ህጻናት መሆናቸውን ያስታወቀው ዩኒሴፍ ከእነዚሁ መካከል ከ 400ሺ የሚበልጡት ለከፋ የጤናና የአካል ጉዳይት ተዳርገው እንደሚገኙ አመልክቷል።
የህጻናቱ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ሲገልፅ የቆየው ይኸው ተቋም፥ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የህጻናቱን ህይወት ለመታደግ ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በቀጣዩ ጥቂት ወራቶች ውስጥ የተረጂዎች ቁጥር ወደ15 ሚሊዮን ያሻቅባል ተብሎ በመጠበቁም ለጉዳት የሚጋለጡ ህጻናት ቁጥርም አብሮ እንደሚጨምር ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በድርቁ ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ መድረሱን ያወሳው ድርጅቱ በሀገሪቱ ያለዉ የድርቅ አደጋ ከተገመተዉ በላይ መሆኑንም አመልክቷል።
የህጻናት አድን ድርጅቶች ጥምረት በበኩሉም ልዩ ድጋፍና ክትትልን የሚፈልጉ ህጻናት በቂ ድጋፍ እያገኙ አለመሆኑ ስጋት መፍጠሩን ገልጿል።
ይኸዉ ከ180 በሚሆኑ ወረዳዎች ዉስጥ ተከስቶ ያለዉ የድርቅ አደጋ እስከቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድርስ ቀጣይ በመሆኑም አስከፊ የጤናና የአካል ጉዳት የሚደርስባቸዉ ህጻናት ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ጥምረቱ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የአለም አቀፉ ማህብረሰብ የገባዉን ቃል ባለመጠበቁ ሳቢያ ቸግሩ እየተባባሰና የተረጂዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን በደጋሚ አስታዉቋል።

ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡
ፓርቲው ‹‹ሕዝባዊ መንግስት መመስረትና የሐገር ሉዓላዊነት መጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ነው›› በሚል ዛሬ ታህሳስ 20/2008 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አበበ አካሉ ናቸው፡፡
ሰማያዊ በመግለጫው፣ ‹‹በሀገራችን የደረሰው ግፍና በደል የማስቆምና ህዝባዊ መንግስት የማቋቋም፣ የሀገርን ብሄራዊ ክብር የማስጠበቅ ኃላፊነት የጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው›› ብሏል፡፡ በመሆኑም ‹‹…ሁሉም ዜጎች አርዓያቸው የሆኑትን የቁርጥ ቀን ልጆች የመስዋዕትነት ጥሪ በመቀበል ቆርጠው እንዲነሱና የድርሻቸውን እንዲወጡ…›› ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ፋና ወጊና የነቁ ዜጎች የእሳት ራት እየሆኑ ነው ያለው ሰማያዊ፣ ‹‹አርዓያዎቻችንን እያስበላን ዝም ማለታችን አገዛዙ እድሜውን ለማራዘም›› ተጠቅሞበታል ሲል ገልጾዋል፡፡ መንግስት ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲ አባላትንና አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችንና ንቁ ዜጎችን በጅምላ እያሰረ መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውሷል፡፡
በሌላ በኩል የሐገር ድንበርንና ሉዓላዊነትን የሚጠብቁ ዜጎችን መንግስት ‹‹ሽፍቶች›› ሲል መጥራቱ ታሪካዊ የክህደት ምስክርነት በገዛ ዜጋ ላይ መስጠት ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው አውግዟል፡፡
(ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዞ ቀርቧል)
Semayawi Party- Ethiopia's photo.
Semayawi Party- Ethiopia's photo.

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከ500 በላይ አባላት ታስረውብኛል፣ ግጭቱን ተከትሎ እስከ 4ሺ ሰዎች ታስረዋል አለ

ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ እንደዘገበው:-
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባና 6 ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ500 በላይ አባላት ሰሞኑን እንደታሠሩበት ፓርቲው ገለፀ፡፡ የኦፌኮ ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ ጉርሜሣ አያኖ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር፣ አዲሱ ቡላላ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ደረጀ መርጋ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ፣ መ/ር አለሙ አብዲሳ ፀሐፊ፣ መ/ር ታሪኩ ኦዲተር፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ ም/ዋና ፀሐፊ እንዲሁም አቶ በቀለ ገርባ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ሰሞኑን በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡
ከፓርቲው አማካሪ ም/ቤት አባላት መካከልም የታሠሩ እንዳሉ የገለፁት ዋና ፀሐፊው፤ ከዞን አመራሮች የቄለም ወለጋ ዞን አመራር አቶ መሠረት ዳባ፣ የምስራቅ አርሲ ዶዶላ አመራር አህመድ ኢቦ፣ የባሌ አመራር አቶ ሁሴን አምዳ፣ የሆሮ ጉዱሩ አቶ ደገባስ ዋቀዩ፣ የኢሊባቡር አመራር አቶ እስማኤል ሁሴንና አቶ ያዛቸው አብዲሣ ታስረዋል ብለዋል፡፡
የወረዳ አመራሮችና ባለፈው ግንቦት በምርጫ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጨምሮ እስከ 500 የሚደርሱ የፓርቲው አባላት በተለያዩ አካባቢዎች መታሠራቸውን አቶ በቀለ ገልፀው፤ ፓርቲው ባለው መረጃ መሰረት በአጠቃላይ ተቃውሞውን ተከትሎ የታሠረው ሰው ብዛት እስከ 4ሺ ይደርሳል ብለዋል፡፡
ከ300 በላይ የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎች እንዳሉ የተናገሩት ዋና ፀሐፊው፤ በግጭቱ የቆሰሉ ከ1500 በላይ ተጎጂዎች በወሊሶ ሉቃስ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ በሚኒልክና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል

አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች? – በዘላለም ክብረት

 

ዘላለም ክብረት
ዘላለም ክብረት
ሕሩይ ሚናስ አስደናቂ ሰው ነው፡፡ የገበሬ ልጅ፣ በአስራዎቹ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ፡፡ ከዛም የአብነት ተማሪ ሆነና ቅዳሴና ቅኔ ሞካከረ፡፡ እሱ አልሆን ሲለው ጎዳና ወጥቶ ጎዳና አዳሪ ሆነ፡፡ ቀጠለና የለማኝ መሪ (sighted guide) ሆነ፡፡ እሱም ሲያልፍ ‹ለምን አልማርም?› ብሎ ትምህርት ተማረና ዩንቨርሲቲ በገባ በዓመቱ ‹ማርክሲስት› ሆነ፡፡ ትምህርቱንም ለአቢዮቱ ሲባል ተወውና መፅሃፍ ነጋዴ ሆነ፡፡ ማርክሲስት ነጋዴ! ‹ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣኦት› እንዲሉ የትናንት ቀዳሹ ሕሩይ ዛሬ ማርክስዚምን ወደደ፡፡ የሕሩይ ማርክሲዝም ከትናንት ማንነቱ እጅግ በተለየ መንገድ ወሰደው፣ የመፅሃፍ አርታኢነት፡፡ መፅሃፍ ሲያነብ፣ ሲተረጉም፣ ሲፅፍና የአርትኦ ስራ ሲሰራ ውሎ ጫት ይቅማል፤ በዛ ላይ አረቄም ይሞካክራል፡፡ በመጨረሻ አበደ፡፡ ከዛ በኋላ ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ብዙ ያሳዝናል፡፡
በኋላ ከአዕምሮ ሕመሙ ሲያገግም ግን የሚገርም ነገር አደረገ፡፡ ‹እብድ› እያለ ሲያደርጋቸው ነበሩትንና የሚያስታውሳቸውን ነገሮች ሁሉ በተርታ ፅፎ ‹እብዱ› በሚል ርዕስ መፅሃፍ አሳተመ፡፡ ይህ መፅሃፉ ለሕሩይ ከብዙ ስራዎቹ አንዱ ነው፡፡ ስለ አዲስ አበባ ለመፃፍ ከሕሩይ የተሻለ ምሳሌ ማግኝት ይከብዳል፡፡ እሱም ‹ወይ ዐዲስ ዓበባ› በሚል ርዕስ (እውነትን መሰረት ያደረገ) መፅሃፍ ፅፎ አዲስ አበባ ከሩቅ ሲያይዋት ምን እንደምትመስል ይተርካል፡፡ በሕሩይ የገጠር ሕይወት አይን አዲስ አበባ ገነት ነበረች፡፡ ሕሩይ እንዲያውም በመደነቅ ‹‹ለካ የዐዲስ ዓበባን ሰው ፎቶ እያነሱ ነው ወደ ገጠር ‹ምስለ መላዕክትና ሰማዕት› እያሉ የሚልኩልን›› በማለት እሱ ከሚያውቀው ገጠርና ሕዝቡ አንፃር አዲስ አበባ ገነት፣ ነዋሪዎቿም መልዓክት እንደሆኑ ይገልፃል፡፡ ገነት ሆና ከሩቅ የታየችው አዲስ አበባ ሲገባባት ጎዳና ላይ አስተኝታዋላች፣ ‹አቢዮተኛ› አድርጋዋለች፣ አሳብዳ አስለፍልፋዋለች … በስተርጅናውም ‹ከጋራ ኮንዶሚኒየም ቤቶቿ› በአንዱ ይኖር ዘንድ ፈቅዳለታለች፡፡ ሕሩይ አዲስ አባባን ከሩቅ አይቶ ጎምጅቶባታል፡፡ አዲስ አበባን ጉያዋ ስር ሆኖም ተሰቃይቶባታል፡፡ ዛሬ ደግሞ አዲስ አበባ ሕሩይን እንከባከብኻለሁ እያለችው ነው፡፡ ሕሩይ ሚናስ – ራሱን ‹አውግቸው ተረፈ› ብሎ የሰየመ ሰው፡፡
ይህ የሕሩይ ብቻ ታሪክ አይደለም፡፡ የብዙ ኢትዮጵያዊያንም እንጂ፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባን ከከተማም በላይ የስልጣኔ ምልክት አድርጎ ነው የሚቆጥራት፡፡ እንዲያውም ሌሎች ከተሞች የሚለሙት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ነዋሪዎች እንዲዝናኑባቸው ሁሉ እስኪመስል ድረስ የሌሎች ከተሞችን ዕድገት ሁሉ ወሳኟ አዲስ አበባ እየሆነች ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ‹የአዲስ አበባ እንግዶች መጥተዋል› ከተባለ ነገሩ ትልቅ ነው፡፡ አንዳንዴማ ‹እሷ እኮ አዲስ አበባ ቤት አላት› ሲባል ሁሉ ነው ሃብት የሚቆጠረው፡፡
አዲስ አበባ አንድ ከተማ ብቻ ነች ማለት ከባድ ነው፡፡ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ 3.6 በመቶው ብቻ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚኖረው ቀሪው የሀገሪቱ ሕዝብ ያለ አዲስ አበባ ምንድን ነው? እስኪባል ድረስ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለተባለው ዓለም የስበት ማዕከል (center of gravity) ናት፡፡
1. “Addis Ababa: The 3rd most ‘Primate City’ on earth”
ጅኦግራፈሩ ማርክ ጀፈርሰን በጎርጎሮሳዊያን አቆጣጠር በ1939 አንድ የከተሞች እድገት ምጥጥን (balance) የሚገልፅ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ የአውራ ከተማ (Primate City) ፅንሰ ሃሳብን፡፡ እንደ ጀፈርሰን አገላለፅ አንድ ከተማ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ሌሎች ከተሞች መካከል በሕዝብ ቁጥር ትልቁ ሲሆንና የሕዝብ ቁጥሩም በሁለተኝነት ከሚከተለው ከተማ በእጥፍ ሲበልጥ ያ ከተማ ‹አውራ ከተማ› (Primate City) ይባላል፡፡ (በኋላ በጀርመናዊው ጅኦግራፈር ዋልተር ክራይስትለር የተፈጠረው የCentral Place Theory (CPT) በበኩሉ አውራነት የሚለካው አውራው ከተማ ከተከታዩ በሁለት ዕጥፍ ከበለጠ ነው በማለት ሌላ መከራከሪያ አቅርቧል)፡፡ ለማንኛውም ጀፈርሰን ይሄን የከተማ አውራነት መስፈርት (primacy rule) ካስቀመጠ ከአስር ዓመታት በኋላ በተለምዶ ‘Zipf’s law’ የሚባለውና በሳይንሳዊው አጠራር ‘Rank Size Rule’ እየተባለ የሚጠራው የምጥጥን (proportionality) ሂሳብ በአሜሪካዊው የስነ ቋንቋ ምሁር ጆርጅ ዚፒፍ ብቅ አለ፡፡ ዚፒፍ ምጥጥኑን ከቋንቋ ጋር አያይዞ ያቀረበው ቢሆንም በኋላ ወደሌሎች ጉዳዮችም አድጓል፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ዚፒፍ ሎው የአንድ ሀገር የከተማ እድገት ጤነኛ ነው የሚባለው በአንድ ሀገር ውስጥ ካለው በሕዝብ ቁጥሩ ትልቁ ከተማ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚገኝው ሁለተኛው ከተማ በሕዝብ ትልቁ የሆነውን ከተማ ግማሽ ያክል ሕዝብ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሶስተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሲሶ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል፡፡ አራተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሩብ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል… እያለ ምጥጥኑን ይቀጥላል፡፡
እንግዲህ ይሄን ህልዮታዊ መነሻ ይዘን፡፡ የአውራ ከተማ መኖር ምንን ያመላክታል የሚለውን ጉዳይ ስናይ ነው የሕልዮቶቹ መሰረት የሚገለፅልን፡፡ አንድ ሀገር አውራ ከተማ አላት ማለት አውራ የተባለው ከተማ የሀገሪቱ የትኩረት ነጥብ (national focal point) ነው ማለት ነው፡፡ ከዛም ባለፈ ያ ከተማ የሀገሪቱን ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በዋነኛነት በያኝ (strong pull factor) ነው ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሀገሪቱ የንጉሳዊ ግርማ (King Effect) ሰለባ ነች ማለት ነው፡፡ ስለ ሀገሪቱ ማውራት ማለት ስለ አውራው ከተማ ማውራት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በመዓከሉ (center) እና በዳር ሀገሩ (periphery) መካከል የእኩልነት ሚዛን እጅግ ተዛብቷል (imbalance) እንደማለት ነው፡፡
1.1. ሁለተኛ ከተማ (Secondary City)
በሌላ በኩል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአውራ ከተማን ፈተና ለመከላከልና ፍትሃዊ የከተማ እድገት እንዲኖር ሲባል የዓለም ባንክን ጨምሮ ብዙ ፖሊሲ አውጭዎች የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) አማራጭን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ማለት ከትልቁ ከተማ ባለፈ በሀገራት ውስጥ ከትልቁ ከተማ ብዙም ያልራቁ (አንዳንዶች ከ500,000 – 3,000,000 ነዋሪ ያለባቸው ከተሞች ሲሉ ሁለተኛ ከተማነትን ያብራራሉ) አማራጭ ከተሞችን መፍጠር ነው፡፡ ደቡብ ምስራቅ እስያ በዚህ በኩል በጣም የተሳካለት የዓለማችን ክፍል ነው፡፡
1.2. ኢትዮጵያስ?
የኢትዮጵያን ጉዳይ ስንመለከት ከላይ ከቀረቡት ሕልዮቶችና የፖሊሲ አውጭዎች ምክረ ሃሳብ እጅግ በተቃራኒው እናገኛታለን፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን በሃምሌ 2007 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ 973 ከተሞች እንዳሏት የገለፀ ሲሆን፤ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብም 19 በመቶ የሚሆነው (ይህ አሃዝ አከራካሪ ነው) በከተማ ውስጥ ይኖራል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ 973 ከተሞች ቢኖሯትም ከአምስቱ የከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የሚኖረው፡፡ በሌላ አነጋገር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ (አዲስ አበባን ሳይጨምር) ከአንድ መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው አስራ ስድስት ከተሞች ያሉ ሲሆን፤ የአስራ ስድስቱ ከተሞች ሕዝብ ተደምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነው፡፡
የማርክ ጀፈርሰንን የአውራነት ሕግ (primacy rule) እዚህ ላይ አምጥተን ስንመለከት አዲስ አበባን ከአውራም አውራ ሆና እናገኛታለን፡፡ ይሄም የሚሆነው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው ትልቅ ከተማ (አዲስ አበባ) በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ሁለተኛ ትልቅ ከተማ (በሃምሌው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን ሪፖርት መሰረት አዳማ ከተማ ናት ሁለተኛዋ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ) በእጥፍ ከበለጠ አውራ ከተማ እንደሚባል ከላይ ያየን ሲሆን፣ በዚህ ስሌት መሰረትም አዲስ አበባ ከተከታዩ አዳማ ወደ አስራ አንድ እጥፍ እንደምትበልጥና ይሄም አዲስ አበባ ከታይላንዷ፣ ባንኮክና ከፔሩዋ ሊማ ቀጥላ በዓለም ላይ ሶስተኛዋ አውራ ከተማ ሲያደርጋት በአፍሪካ ደግሞ አንደኛዋ ያደርጋታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ግዝፈቷ የዚኮፍን የምጥጥን ሎው እንኳን መተግበር ማሰብም ከባድ ያደርገዋል፡፡ ይህ የተዛባ ምጥጥን አዲስ አበባ ከመመስረቷ ጀምሮ የተፈጠረ ነው ማለት ደግሞ ከባድ ነው፡፡ የአለፈውን የመቶ ዓመት እድገት እንኳን ብንመለከት በ1910 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 65,000 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥርም በጊዜው ከሀረር ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነበር፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ 1935 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 100,000 ሆነ፡፡ ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በ1961 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 443,728 ደረሰ፡፡ አሁንም ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታትም በኋላ በ1984 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 1,423,111 ደረሰ፡፡ በመጨረሻም ከ35 ዓመታት በኋላ በ2015 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ከእጥፍ በላይ ጨምሮ ዛሬ 3,194,000 ደርሷል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት በጊዜው በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛ ከነበረችው የሀረር ከተማ ጋር ተመጣጣኝ ቁጥር የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ዛሬ በሁለተኝነት ከምትገኝው አዳማ ከተማ አስራ አንድ እጥፍ በልጣ በአውራ ከተማነት በሩቅ ተቀምጣለች፡፡
ስታንሊ ብሩን የተባሉ ፀሃፊ ‹‹የአውራ ከተማ መኖር በራሱ የሀገሪቱ እድገት ጤናማ እንዳልሆነና የተዛባ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡ ይሄም ማዕከሉ (center) ከዳሩ (periphery) አለመመጣጠናቸውን ያስገነዝበናል› ይላሉ፡፡ እንግዲህ የአሁኗ ኢትዮጵያን ፍትሃዊነት አዲስ አበባ በደንብ የምትገልፃት ይመስላል፡፡
አዲስ አበባ በታሪኳ ሶስት ጊዜ ከዋና ከተማነቷ የመቀየር እጣ ፋንታ ተጋርጦባት እንደምንም አልፋዋለች፡፡ የመጀመሪያው በአፄ ምኒልክ ዘመን በአካባቢዋ ያለው የማገዶ እንጨት በማለቁ ምክንያት ዋና ከተማው ወደ አዲስ ዓለም ለመቀየር በታሰበበት ወቅት ባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ መጥቶ አዲስ አበባን ከመቀየር አድኗታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ጣሊያን አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት አዲስ አበባ ተራራማ ከተማ ላይ በመሆኗ ጣሊያኖቹ የራሳቸውን የቅኝ ግዛት ዋና ከተማ (colonial city) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ለመመስረት ጥረት አድርገው በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ሊተዉት ችለዋል፡፡ እንዲሁም አፄ ኃይለስላሴ የቀደመውን የተንቀሳቃሽ ዋና ከተማ (roving cities) ልምድ ለማስቀጠልና የራሳቸውን ዋና ከተማ ለማቋቋም በማሰብ ባህርዳርን ዋና ከተማቸው ለማድረግ አስበው እንደነበር ታሪክ ፀሃፊው በላይ ግደይ ‹አዲስ አበባ ያብባል ገና› ባሉት መፅሃፋቸው ላይ ይጠቁማሉ፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን ‹ሀገር› ናት፡፡ የበታቾቿን በሩቅ የምታይ ከተማ፡፡
በሌላ በኩል እነ ዓለም ባንክ እያስተዋወቁት የሚገኝው የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) ፅንሰ ሃሳብም በአሁኗ ኢትዮጵያ ቦታ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በፖለቲካና የንግድ ማዕከልነት የአውራዋን አዲስ አበባን ሚዛን የሚገዳደር አይደለም፤ ተስፋ እንኳን ያለው ከተማ አለ ማለት በጣም ከባድ ነው፡፡ ይህ የአዲስ አበባ አውራነትም ከተማዋን በሀገሪቱ ውስጥ በነዋሪ ደረጃ የመሰረታዊ አገልግሎቶች በቀላሉ የሚገኝባት (the highest concentration of basic service facilities per population) ቀዳሚ ከተማ አድርጓታል፡፡ ይሄም ከተማዋን ‘privileged position’ ያሰጣት ከመሆኑም ሌላ፤ አዲስ አበባን እጅግ ግዙፍና የማይደረስባት አይነት ከተማ አድርጓታል፡፡
ከአዲስ አበባ ምስረታ ጋር ተያይዘው ከሚነገሩ አፈ ታሪኮች አንዱ፣ የአፄ ምኒልክ ሃይለ መለኮት አያት የሆኑት ንጉሰ ሸዋ ሳህለስላሴ በአንድ ወቅት ጉለሌ የሚገኝ አንድ ዛፍ ስር ቁጭ ብለው ‹እዚህ አካባቢ የልጅ ልጆቼ ትልቅ ከተማ ሲመሰርቱ ይታየኛል› ብለው ነበር ይላል፡፡ ሳህለስላሴ የዛሬዋን አዲስ አበባ ቢያዩ ‹እንዴ እኔ በራዕይ ያየሁት እኮ ሀገር አይደለም ከተማ ነው› ብለው መደናገራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡
የፌደራል ሀገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየን ፌደራሊዝም ‹አውራ ከተማን› (Primate City) ያጠፋል፡፡ የደቡብ ምስራቅ ተሞክሮ እንደሚያሳየን ደግሞ ልማታዊ መንግስት በዛ ያሉ ሁለተኛ ከተሞችን (Secondary Cities) ይፈጥራል፡፡ አውራዋ አዲስ አበባ የአውራዎች አውራ እየሆነች እየሄደች ሲሆን፡፡ አውራ ብቻ ሳትሆን ሁለተኛ ከተማም (Secondary City) ራሷ አዲስ አበባ ነች፡፡ አዲስ አበባ ብቻዋን እንዲህ ገዝፋ የአውራም አውራ እስክትሆን ድረስ ፖሊሲ አውጭዎቹ የት ሂደው ነው ብሎ መጠየቅ እዚህ ጋር ተገቢ ነው፡፡ የአሁኗ አዲስ አበባ ሕጋዊ (Legal status) ምንድን ነው ብለንም መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡
2. አዲስ አበባ ምንድን ናት?
ኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትን በሕገ መንግስት ደረጃ ከተቀበለች ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትም በሕገ መንግስት ደረጃ ዘጠኝ ክልሎችንና አዲስ አበባን እንደ አንድ የፌደራል ከተማ አስተዳደር (ድሬ ዳዋ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለው የይገባኛል ጥያቄ ‹ዘላቂ የሆነ ሕጋዊ መፍትሔ እስኪያገኝ› ለፌደራል መንግስቱ ተጠሪ በመሆን በአዋጅ ቁጥር 416/1996 የተቋቋመች የከተማ አስተዳደር ናት) በማድረግ ተቋቁሟል፡፡ በሕገ መንግስቱም ሆነ በኋላ ከተማዋን በሕግ ለማቋቋም በወጡት ቻርተሮች የከተማዋ ሕጋዊ ‹ስታተስ› (ከዋና ከተማነት ባለፈ) በግልፅ ባለመቀመጡም የከተማዋ ‹ስታተስ› ለተመሳሳይ ጥያቄ የተለያዩ መልሶችን እየሰጠ ቀጥሏል፡፡ ዓለም ላይ ባሉ የተለያዩ የፌደራል ስርዓቶች ዋና ከተማ ከዚህ በሚከተሉት ሶስት ጎራዎች በአንዱ ላይ ይመደባል፡፡ ራሱን የቻለ ክልል (City State)፣ በሕግ በፌደራል ቀጠናነት የተመደበ ከተማ (Federal District)፣ እና በአንድ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ ከተማ (A City in A State)፡፡ ኢትዮጵያም በሕግ የፌደራል ስርዓትን ያቋቋመች ሀገር በመሆኗ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በየትኛው ጎራ ትመደባለች ለሚለው ጥያቄ አንድ አይነት መልስ ማግኝት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ አስቸጋሪ ሁኔታም ነው በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ውዝግብ እንዳይፈታ አይነተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሶስቱ መደቦች አንፃር የአዲስ አበባን ‹ስታተስ መመልከት› ጉዳዩን በበለጠ እንድንረዳው ይረዳናልና እሱን እንመልከት፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ምንድን ናት?
2.1. ራሷን የቻለች ክልል (City State) ናት
የፌደራል ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገሮች ከሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች አንዱ ዋና ከተማን መምረጥና መሰየም ነው (የስዊዘርላንድ ሕገ መንግስት በሕገ መንግስት ደረጃ ዋና ከተማ ከመሰየም የተቆጠበውም በዚህ ውዝግብ ምክንያት ነው)፡፡ የፌደራል ስርኣት የመንግስት ስራን በማዕከሉ መንግስትና በክልሎች መካከል የሚከፍል በመሆኑ ዋና ከተማዋን የትኛው ክልል ላይ ማድረግ አለብን የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ ነው፡፡ እንደ ጀርመን እና ቤልጅየም ያሉ የፌደራል ሀገሮች ለዚህ መፍትሔ ብለው ያቀረቡት ሀሳብ ዋና ከተማውን ራሱን የክልል ማዕረግ በመስጠት ከፌደራሉም ሆነ ከክልል መንግስታት ነፃ ማውጣትን ነው፡፡ በመሆኑም በርሊን በአሁኑ ወቅት ከአስራ ስድስቱ የጀርመን ክልሎች አንዷና ዋና ከተማ ስትሆን የቤልጀሟ ብራሰልስም ከቤልጅየም ሶስት ክልሎች አንዷ በመሆን የተፎካካሪዎቹ ፍሌሚሽና ዋሎን ክልሎች አስታራቂ ሁና በመሃል ትገኛለች፡፡
ታዲያ አዲስ አበባ ከዚህ ሞዴል ጋር ምን አገናኛት? በርግጥ አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገመንግስት ያቋቋመው ዘጠኝ ክልሎችን ብቻ ነው፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ከነዚህ ክልሎች ውጭ ናት፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባን በዋና ከተማነት ያቋቋመው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49ን በጥልቀት ስንመለከት በንዑስ አንቀፅ ሁለት ላይ አዲስ አበባን ራሷን በራሷ የማስተዳደር ሙሉ መብት ይሰጣታል፡፡ ይህ አንቀፅም በሽግግር መንግስቱ ወቅት በአዋጅ ቁጥር 07/1984 እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር በመሆን የተቋቋመችውን አዲስ አበባን መንፈስ ያጠናክራል፡፡ ይሄንም ስንመለከት አዲስ አበባ በተግባር (de facto) ራሷን የቻለች ክልል ትመስላለች፡፡ በነገራችን ላይ አዲስ አበባ ራሷን ችላ በሕግ ደረጃ (de jure) ክልል እንድትሆን ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የሚጎተጉቱ አካላት ብዙ ናቸው፡፡
2.2. የፌደራል ቀጠና (Federal District) ናት
በሌላ በኩል የፌደራል ዋና ከተማን የመምረጥ ፈተና ለማለፍ በዛ ያሉት ፌደራል ሀገሮች ዋና ከተማዋን በፌደራል ቀጠናነት (Federal District) በሕግ በመከለል ተጠሪነቷን ሙሉ ለሙሉ ለፌደራል መንግስት የማድረግን አሰራር ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አሜሪካና ሕንድ ናቸው፡፡ አሜሪካ ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ግዛቶች መሬት በመውሰድ ዋሽንግተን ዲሲን በዋና ከተማነት ሰይማ (ስፋቱ ከአስር ማይል መብለጥ የለበትም የሚል ገደብ በማስቀመጥ) ተጠሪነቷን ለኮንግረስ አድርጋለች፡፡ ሕንድም ዴልሂን ዋና ከተማና የፌደራል ቀጠና አድርጋ ተጠሪነቱን ለምክር ቤት አድርጋለች፡፡ ይህ አይነት የዋና ከተማ አደረጃጀት የራሱ የሆነ (በተለይም ከምርጫ፣ ግብር እና የክልሎች መብት አንፃር) ችግሮች ያሉበት ነው፡፡ ከታች ለማየት እንሞክራለን፡፡
አዲስ አበባን ስንመለከት የህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (3) እና (4) አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌደራሉ መንግስት መሆኑን በመግለፅ የአዲስ አበባ ቀጠና የፌደራል ቀጠና እንደሆነ በተዘዋዋሪ ያስረዳል፡፡ ይህ ብዙ ሰዎች የሚስማሙበት ሃሳብ ቢሆንም ተያያዥ ችግሮች ግን በየጊዜው መነሳቸው አልቀረም፡፡
2.3. በአንድ ክልል የምትገኝ አንድ ከተማ (A City in a State) ናት
ሌላው ከፌደራል ዋና ከተማ አመሰራረት ጋር ተያይዞ የሚቀርበው መፍትሔ ደግሞ ዋና ከተማዋን ከክልሎች (States) በአንዱ ከተማ ላይ ማድረግና ክልሎች ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ማድረግ የሚለው ነው፡፡ የዚህ መፍትሔ ምሳሌ ተደርጋ የምትቀርበው ካናዳ ነች፡፡ የካናዳዋ ዋና ከተማ ኦታዋ ከካናዳ ስድስት ክልሎች አንዷ በሆነችው ኦንታሪዎ ግዛት ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ኦንታሪዎም እንደ ዋና ከተማ መቀመጫ ክልልነቷ ከኦታዋ ማግኝት የሚገባት ጥቅም በሕግ የተደነገገና የፀና ነው፡፡ ይህ አካሔድ በሌሎች ክልሎች ዘንድ ቅሬታ ይፈጥራል የሚል ትችት ይቀርብበታል፡፡
የአዲስ አበባን ጉዳይ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ደግሞ ከላይ በጠቀስነው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (5) ላይ ‹የኦሮሚያ ክልል […] አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሃል ላይ የሚገኝ በመሆኑ […] ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል› ይላል፡፡ ይሄም ማለት በሌላ አነጋገር አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ነች እንደማለት ነው፡፡
2.4. ቻርተርድ ከተማ (Chartered City) ናት
አዲስ አበባ ሶስቱንም የፌደራል ዋና ከተማ ባህሪ አዳለ በመያዝ በየትኛው ሕጋዊ ‹ሰታተስ› ላይ እንዳለች ግራ የምታጋባ ከተማ ነች፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ ከተማዋ በራሴ ቻርተር የምትተዳደር ከተማ (Chartered City) ነኝ በማለት ራሷን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቻርተር 87/1989 አቋቁማለች (ቻርተሩ በ1995 በአዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 ሙሉ ለሙሉ ተሸሽሏል፡፡ እንዲሁም በ1996 በአዋጅ ቁጥር 408/1996 በከፊል ተሻሽሏል)፡፡ ይህ በዋናነት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የከተማ ድህነትን ለመቀነስ እንደስትራቴጅ እየተወሰደ ያለ የአወቃቀር አይነት አዲስ አበባ ለምን እንደመረጠችው ብዙም ግልፅ ባይሆንም፤ በሁሉም ቻርተሮች ላይ ዋነኛ ዓላማው ‹የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን እንዳለው […] በሕገ መንግስቱ በመደንገጉ› ምክንያት እንደሆነ ተገልፆ እናገኛለን፡፡ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ ነች ማለትም ከላይ 2.1 ላይ ለማመላከት የተሞከረውን የክልል ማዕረግ (status of state) የሚያጠናክር ሃሳብ ሆኖ የከተማዋን ስታተስ ለመወሰን ከላይ ያየናቸውን የዋና ከተማ ብያኔ ክርክር የበለጠ ያጦዘዋል፡፡
እንግዲህ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል ናት፣ ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስቱ የሆነች የፌደራል ቀጠና ናት፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ናት እንዲሁም በራሷ የቆመች ቻርተርድ ከተማ ነች የሚሉ የራሳቸው አሳማኝ ምክንያት ያላቸው መከራከሪዎች ይቀርባሉ፡፡ ይህ ግልፅነት የጎደለው የከተማዋ ‹ስታተስም› አሁን ከተማዋን አስመልክቶ ለሚነሱ ውዝግቦች መነሻና መድረሻ ነው፡፡
3. ‹የአንተም ተው፣ አንችም ተይ ፌደራሊዝም› እና መዘዙ
[የኢትዮጵያ የሕገ መንግስት ኮሚሽን] ሰብሳቢ [አቶ ክፍሌ ወዳጆ] [የኮሚሽኑ] አባላት ተሳትፎና ኮሚሽን የሥራ ሒደት በተመለከተ አልፎ አልፎ አባላት በስብሰባ ላይ ያለመገኝት ሁኔታ በማሳየታቸው የስራ መጓተት እየተከሰተ መሆኑን፣ ከፓናሎች የሚጠበቁ ሪፖርቶች በተፈለገው ጊዜ ሊቀርቡ እንዳልቻሉና ይኸውም የፓናል አባላቶች በስብሰባ አለመገኘት ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልፀው፣ ለመጪው ጊዜ በእያንዳንዱ ስብሰባ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ በበቂ በመዘጋጀት ለውሳኔ የሚያበቃ ሰፈ ግንዛቤ በመጨበጥ መገኘት ከእያንዳንዱ አባል እንደሚጠበቅ አሳስበው፣ […] የአዲስ አበባን የመናገሻ ከተማነት ደረጃ (status) እና ወደፊት አከላለስ ሊኖራት የሚችለውን ቦታ አስመልክቶ በሚዘጋጀው የመወያያ ሰነድ (working paper) ውስጥ እንዴት ማስቀመጥ እንደሚቻል ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡››
ይህ ሐሳብ የተገለፀው የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለማርቀቅ የተቋቋመው የሕገ መንግስት ኮሚሽን ሰብሳቢ በነበሩት አቶ ክፍሌ ወዳጆ ጳጉሜ 1- 1985 በኮሚሽኑ 39ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ እንደ ሰብሳቢው ሐሳብ ከሆነ ሕገ መንግስትን ያህል ሰነድ ለማርቀቅ የተዋቀረው ኮሚሽን አባላት በኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው አሳስቧቸውና የአዲስ አበባን ደረጃ (status) ገና ሳይወስኑ እስከ አሁን መቆየታቸው አሳስቧቸው ነው፡፡ ሰብሳቢው አቶ ክፍሌ ይሄን ቢሉም ይሄን ማስጠንቀቂያ በተናገሩበት እለት እንኳን ከ27 የኮሚሽኑ አባላት መካከል ስምንት የሚሆኑት አልተገኙም ነበር፡፡ አዲስ አበባን አስመልክቶ የቀረቡት ጉዳዮች በሕገ መንግስታዊው ጉባኤ የተወሰነ ውይይት ቢደረግበትም፣ በኮሚሽን ደረጃ ብዙም ውይይት እንዳልተደረገበት በጊዜው የኮሚሽኑ አባል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገልፃሉ፡፡ እንግዲህ ያ በቸልተኝነት የታለፈ ጉዳይ ነው አንዱ የዛሬው ችግር መነሻ፡፡ አዲስ አበባ የክልልም፣ የፌደራል ግዛትም እንዲሁም የአንድ ክልል ከተማ መልክ ይዛ ከሶስቱ አንዱን መሆን አለመቻሏ በጊዜው ሲሟገቱ የነበሩ ሁሉንም አካላት ለማስደሰት በሚል የታለፈ ጉዳይ ይመስላል፡፡
የተለያዩ ምሁራን አዲስ አበባን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሱ ሕገ መንግስቱ መመለስ አለመቻሉን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ መሰረታዊዎቹን ጥያቄዎች እዚህ ላይ ማንሳት ተገቢ ስለሚሆን አንስተን እንመልከታቸው፡፡
1. የአሜሪካ ዋና ከተማ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ በተቋቋመችበት ወቅት መሬት ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ስቴቶች ተቆርጦ ተሰጥቷት ነው የተቋቋመችው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ቨርጅኒያ መሬቴን መልሽልኝ በማለት መሬቷን በሕዝበ ውሳኔ መሬት የማስመለስ ሒደት (retrocession) መሰረት አስመልሳለች፡፡ ሜሪላንድም እስከ አሁን አልጠየቀችም እንጂ ብትጠይቅ ልታገኝ እንደምትችል የሕገ መንግስት ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ አዲስ አበባ የምትገኝው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ታዲያ ኦሮሚያ ‹መሬቴን ራሴ አስተዳድራለሁ› ብትል በምን አግባብ ነው መልስ የሚሰጠው?
2. አሁንም እዛው ዋሽንግተን ዲሲ እንቆይና ባራክ ኦባማን ጨምሮ ብዙ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ዋሽንግተን ዲሲ ራሷን የቻለች ሃምሳ አንደኛ የአሜሪካ ‹ስቴት› ብትሆን ፍላጎት እንዳላቸው (ከመራጭነት መብት አንፃር) ይገልፃሉ፡፡ ሐሳቡ ወደ ፊት ሊተገበር የሚችል ጉዳይ እንደሆነም ምሁራን እያስረዱ ይገኛሉ፡፡ አዲስ አበባ ራሴን ችዬ ክልል ልሁን ብትል በምን አግባብ ነው የሚስተናገደው ለሚለው ጥያቄ የራስን ክልል የመመስረት መብት የሚሰጠው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 47 (2) መብቱን የሚሰጠው ‹ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች› ሲሆን አዲስ አበባ በምን ጎራ ላይ እንደምታርፍ ምንም የተገለፀ ነገር የለም፡፡
3. አዲስ አበባ አሁን ባላት ቁመና ቻርተርድ ከተማ እንደሆነች ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ ቻርተርድ ከተሞችን (Chartered Cities) ከሌሎች ከተሞች (General Law Cities) የሚለያቸው ዋነኛው ጉዳይ ደግሞ የፌደራልንም ሆነ የክልል መንግስታትን ጣልቃ ገብነትን የሚያስወግድ አሰራር መተግበራቸው ነው፡፡ ታዲያ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ እንደመሆኗ ‹የፌደራል መንግስቱን ጣልቃ ገብነት አልፈልግም› ብትል ሕገ መንግስቱ ምን መልስ ይሰጣል?
እነዚህን ሕልዮታዊ ጉዳዮች ያነሳነው የአሁኑ የኢትዮጵያ ፌደሬሽን በተግባር የሌለ ብቻ ሳይሆን በአወቃቀር ደረጃም የማይመልሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መኖራቸውን ለማመላከት ነው እንጂ፤ ‹ጠያቂም መላሽም› እንደሌለ መረዳት ከባድ ሆኖ አይደለም፡፡
አዲስ አበባም ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊ እንዲሁም መዋቅራዊ ችግሮቿ ሰንገው በያዟት በዚህ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን [የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› ተብሎ የተሰየመው የሃያ አምስት አመታት ዕቅድ ብቅ ያለው፡፡
4. ‹[የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› እና አዲስ አበባ
ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በጣሊያን ኔፕልስ ከሴፕቴምበር 02 እስከ 07 – 2012 ነበር የተካሔደው፡፡ ፎረሙ በተባበሩት መንግስታት ከተቋቋመበት ከ2002 ጀምሮ ባሉት አስር ዓመታት ውስት ለስድስተኛ ጊዜ ስብሰባ ማድረጉ ነበር፡፡ ከመላው ዓለም ከመጡ የተለያዩ ሀገር ተወካዮች አማካኝነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን የፎረሙ ዋነኛ አጀንዳም ‹Urban Future› የሚል ሲሆን በዋናነትም አራት መሰረታዊ ጉዳዮችን እንደመወያያ ይዞ ተካሂዷል፡፡ ከነዚህ አራት የውይይት ርዕሶች መካከል ቀዳሚው ‹Urban Planning: Institutions and Regulations› የሚል ነበር፡፡ በውይይቶቹ መጨረሻ ‹የዓለም የከተሞች ማንፌስቶን› ጨምሮ የተለያዩ የውይይቱ ውጤቶች ይፋ የተደረጉ ሲሆን፤ ከነዚህ የውይይቱ ውጤቶች መካከልም የዓለም ከተሞች የተቀናጀ የልማት ዕቅድን (Integrated Development Plan – IDP) ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚመክረው (recommendation) ይገኝበታል፡፡ ይህ በተባበሩት መንግስታት ደረጃ የቀረበው በ2012 ቢሆንም ከዛ በፊት በ2007 ‘Leipzig Charter on Sustainable European Cities’ የአውሮፓ ሀገሮች ይሄን የተቀናጀ አካሄድ በከተሞቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተስማምተው ነበር፡፡
ከዚህ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች የተቀናጀውን አካሄድ ተግባራዊ ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን (ከ2012 -2017) እና የኬኒያዋ ናይሮቢ (ከ2014 -2019) በዚህ ረገድ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ እንዲያውም በሃገሪቱ ላሉ ከተሞች አጠቃላይ የተቀናጀ የልማት ዕቅድን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያ እስከማውጣት ደርሳለች፡፡
4.1. የተቀናጀ የልማት ዕቅድ (Integrated Development Plan – IDP) ምን ለማለት ነው?
አንድ አይነት እና ወጥ የሆነ መልስ ማግኝት ባይቻልም የተለያዩ ከተሞች ከሰጡት የተለያየ ትርጉም አንፃር ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን፡፡ 1. ሁሉም መሰረተ ልማት ላይ የሚሰሩ አካላት (የትራንስፖርት፣ የመብራት፣ የቤቶች ወዘተ) ተቀናጅተው ለተመሳሳይ ግብ እንዲተጉ ማድረግና 2. እቅዱን ያወጣው አካል ከእቅዱ ባለቤት (የከተማው ነዋሪ) ጋር አሳታፊ (participatory) በሆነ መንገድ በየጊዜው በመወያየት ተቀናጅቶ የሚሰራበት አካሄድ ነው፡፡ እንደ ናይሮቢ ያሉ ከተሞች በተቀናጀ የልማት ዕቅዳቸው የመሰረተ ልማት አገልግሎት (በተለይም ትራንስፖርት) በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች (surroundings) ጋርም ለማቀናጀት ሙከራ አድርገዋል፡፡
በዚህ ጊዜ አዲስ አበባም በ1996 አዘጋጅታው የነበረው የከተማ ልማት እቅድ (ማስተር ፕላን) የትግበራ ጊዜው እያለቀ ነበርና የራሷን አዲስ ዕቅድ ለማዘጋጀት ቢሮ ከፍታ እንቅስቃሴ የጀመረችበት ጊዜ ነበር፡፡ መጀመር ብቻም ሳይሆን ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በተካሔደበት በመስከረም 2005 ለእቅዱ የሚያስፈልገውን መረጃ ለቀማ እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋ እቅዱንም በጥቂት ወራት ውስጥ አጠናቅቄ ይፋ አደርጋለሁ ብላ ነበር፡፡ እንደተባለው እቅዱ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደተጠናቀቀ ውስጥ ለውስጥ የተነገረ ሲሆን የመጀመሪያውንም ተቃውሞ በግንቦት 2005 ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በወጣ መግለጫ አስተናግዳ ከዛ በኋላ የሆነውና እየሆነ ያለው ጉዳይ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ እዚህ ላይ ትክክለኛውን አከራካሪ ጉዳይ ለመለየት እንችል ዘንድ የእቅዱን መሰረት እና ይዘት ማየት ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡
4.2. ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› ዘመነኛው ካርድ
‹‹የህዝባችን ኑሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገር ስትሆን ነው፡፡ አገራችን በአለም አቀፋዊው ኢኮኖሚያዊ ትብብር ውስጥ የሚኖራት ድርሻና ከዚሁ የምታገኝው ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ ሊያድግ የሚችለው በኢንዱስትሪ የበለፀገች ስትሆን ነው፡፡ በመሆኑም የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴያችን ግብ በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገርን መፍጠር መሆን አለበት፡፡ ሌላው ቀርቶ የግብርናና የገጠር ልማት እንቅስቃሴያችን የመጨረሻው ግብ አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች እንድትሆን ማድረግ ነው፡፡››
ይህ ሀሳብ የተገለፀው በ1994 በወጣው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የግሉን ባለሃብት የኢንደስትሪያላይዜሽኑ መሰረት ማድረግና ግብርናው ኢንደስትሪውን እንዲመራው ማስቻል (Agriculture Development Led Industrialization – ADLI ) መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ አስቀምጦ ያልፋል፡፡ ከዚህ ስትራተጅ የተከተሉት የእድገትና እና ትራንስፎርሜሽን እቅዶችም ዓላማቸው ግብርና የሚመራውን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ኢንደስትሪ መር ማሸጋገርን (transformation) ዓላማ አድረገው የተቀረፁ ናቸው፡፡ ቁጥሮች እንደሚነግሩን ግን ኢሕአዴግ በኢንደስትሪው መስክ አልተሳካለትም፡፡ ኢንደስትሪው ያለፉት 50 አመታትን ተመሳሳይ መንገድ ይዞ የሚያዘግም ነው፡፡ ኢንደስትሪውን ይመሩታል የተባሉት ግብርና እና የግል ባለሃብቱም ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ብዙም በአካባቢው አይታዩም፡፡
ኢንደስትሪው የትም እንዳልደረሰ እና ‹ትራንስፎርም› የሆነ ብዙም ነገር እንደሌለ የተረዳው ኢሕአዴግ በድንጋጤ (frustration) የደቡብ ምስራቅ እስያ ተሞክሮ የሆነውን መንግስት መር (statist) ኢንደስትሪያላይዜሽን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ኢንደስትሪውን ይመራዋል የተባለው ገበያና የግል ባለሃብትም ከአመራርነት ወርደው ቦታቸውን ለመንግስት አስረክበው ይገኛሉ፡፡
እንግዲህ በዚህ የኢሕአዴግ የኢንደስትሪያላይዜሽን ድንጋጤ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ [የተቀናጀ] የልማት ፕላንም› የመጣው፡፡ የፕላኑ ዋነኛ ግብ ‹ሀገሪቱ የሰነቀችውን የኢንደስትሪ ሽግግር ዕውን መሆን ወሳኝ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የኢንዱስትሪ ልማት ማስተናገድ [የሚችል ክልል መፍጠር]› እንደሆነ በእቅዱ መግቢያ ላይ ተገልፆል፡፡ (ክልል የተባለው ምን እንደሆነ ወደታች የምናው ጉዳይ ነው)፡፡ በእቅዱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ‹‹ክልሉ የሀገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአጠቃላይ የዕቅዱ ዋና አካል የሆነውን የኢንደስትሪ ሽግግር በተለይም እውን በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል››፣ ‹‹ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ››፣ ‹‹በ2030 በምስራቅ አፍሪካ ተወዳደሪ የሆነና በኢኮኖሚ ውስጥ መሪ ሚና የሚጫወት ማዕከል መፍጠር››፣ ‹‹የከተማዋን እና የዙሪያ ኦሮሚያ አካባቢን በጋራ በአፍሪካ ቀንድ ቀዳሚ የኢንዱስትሪ ክልል ማድረግ›› ወዘተ የሚሉ የዕቅዱ ዋነኛ ትኩረት ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› እንደሆነ የሚያመላክቱ ጉዳዮችን እናያለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ የአሁኑን ጨምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጁትን እቅዶች ስንመለከት ‹የዘመኑ መንፈስ› እንደሚመራቸው እናያለን፡፡ የመጀመሪያውና በ1986 የተዘጋጀው እቅድ ዋነኛ ትኩረቱ ‹ሰላማዊ ከተማ› መገንባት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ በ1996 የፀደቀው የከተማዋ የልማት እቅድ ደግሞ በጊዜው የኢሕአዴግ ዋነኛ ማጠንጠኛ የነበረውን ‹ኢንቨስትመንት› መሰረት ያደረገ ሲሆን በጊዜው የከተማዋን መሪ ፕላን ለማጽደቅ በከተማዋ አዲስ ነጋሪት ጋዜጣ ላይ በወጣው አዋጅ ቁጥር 17/1996 ላይም እንደተገለፀው ‹‹[…] ኢንቨስትመንትን በተሳለጠና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማካሔድ [ማስቻል]…›› እንደሆነ ተገልፆ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹የዘመኑ መንፈስ› ኢንደስትሪያላይዜሽን ነውና እቅዱ ዋነኛ ትኩረቱን ኢንደስትሪ ላይ ማድረጉ የሚጠበቅና የሚገርም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከተማዋ የምስራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን ኢንደስትሪ የምትገነባበት በቂ ቦታ የላትምና አወዛጋቢውን መስፋፋት ለማድረግ ተነሳች ማለት እንችላለን፡፡ ይሄ እንዴት ሆነ?
4.3. መሪ እቅድ (Master Plan) ወይስ አዲስ ክልል (New State)?
ሰኞ ግንቦት 18፣ 2000 በጊዜው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩት በአቶ መኩሪያ ሀይሌ እና ከአዲስ አበባ አስራ ሰባት እህት ከተሞች አንዷ በሆነችው የፈረንሳዩ፣ የሊዮን ከተማ ምክትል ከንቲባ Monsier Hubert Julien-Laferriere መካከል አንድ የትብብር ሰነድ ተፈረመ፡፡ የትብብር ሰነዱ በሁለቱ ከተሞች መካከል የተደረገው የአምስት ቀናት ውይይት ውጤት ነበር፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ ያቀረበው የፌደራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 450/1997 ከተሰጡት ስልጣኖች አንዱን በመጠቀም ሊዮን ከተማ አዲስ አበባን ልትረዳ የምትችልባቸው ሶስት አጀንዳዎችን አቀረበ፡፡ እነዚህም ሶስት አጀንዳዎች፡
1. የአዲስ አበባ ከተማን መሪ እቅድ (Master Plan) የመከለስ ስራ፣
2. በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ መካከል በጋራ ለመፍጠር ስለታሰበው ክልላዊ እቅድ (Regional Planning) እና፣
3. ስለ አዲስ አበባ ከተማ የውስጥ የልማት ስራ (Local Development Plan – LDP) ናቸው፡፡
በውይይቱ ማጠናቀቂያም በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ በመደረሱ የሁለቱ ከተሞች አቻ ባለስልጣናት የትብብር ሰነዱን ተስማምተው ፈረሙ፡፡ የመሪ እቅዱ እና የውስጥ የልማት ስራው ከዚህ በፊት የተለመዱ ጉዳዮች በመሆናቸው ብዙም ግርታን የሚፈጥሩ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መካከል ሊፈጠር የታሰበው ክልላዊ የልማት እቅድ የተለመደ ስላልነበር አፈፃፀሙን ለማየት የሚያጓጓ ነበር፡፡ የዚህ ክልላዊ እቅድ መነሻ ግን አሁንም ወደኋላ ወደ 1996 ይወስደናል፡፡ በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 በአንቀፅ 8 (2) ላይ ‹የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን ከመዘጋጀቱ በፊት [ከኦሮሚያ ክልል ጋር] በፈቃደኝነት በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የአዲስ አበባና አካባቢዎች ፕላን እንዲዘጋጅ አስተዳደሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል› በማለት ክልላዊ እቅድ መታቀድ ከጀመረ ቆየት ያለ ጊዜ እንዳስቆጠረ ያመላክተናል፡፡
አሁን መንግስት ያዘጋጀው የተቀናጀ የጋራ የልማት እቅድ ሰነድም (የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ እዚህ ላይ ያገኘው ሰነድ) እነዚህን የኋላ ታሪክ በመያዝ ክልላዊ እቅድን (Regional Planning) ከመሪ እቅድ (Master Plan) በመቀየጥ የተዘጋጀ ነው፡፡ ያለውን የፌደራል ስርዓት አይተን ትግበራው ምን ሊመስል ነው ብለን ማሰብ የሚከብደን አይነት እቅድም ነው፡፡ የእቅዱ ስያሜ እንኳን መሪ እቅድ (Master Plan) ሳይሆን ክልላዊ እቅድ (Regional Plan) ነው፡፡ ግቡም አዲስ አበባን በ 100 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ የሚከብ ሰፊ ክልልን ማልማት ነው፡፡ 36 ከተሞችን እንደሚያካትትም ተጠቅሷል፡፡ ከአዲስ አበባ ሌላ በስም በእቅዱ ላይ ተጠቅሰው የምናገኛቸው ከተሞችም ዱከም፣ ገላን፣ ሰበታ፣ አዋሽ፣ ለገዳዲ፣ ለገጣፎ (ሁሉም በኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞችን ማለት ነው) ናቸው፡፡ በልማት እቅዱ ውስጥ የተካተተው አካባቢም 85 በመቶው ገጠር እንዲሁም 15 በመቶው ደግሞ የከተማ አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በአምስቱ ኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አምስት ከተሞችን ውስጥ በ25 ዓመታት ውስጥ ከ30 ሺህ እስከ 40 ሺህ ነዋሪዎችን ማስፈርን በእቅድነት ይዟል፡፡ ይሄም ዓላማ ያደረገው ‹የክልሉን ነዋሪ ከአስከፊ ድህነት ማላቀቅ› ነው የሚል ሲሆን፤ እዚህ ላይ የየትኛውን ክልል ነዋሪ ማለታችን ተገቢ ነው፡፡
እነዚህን ጉዳዮች ስንመለከትም እቅዱ በዋናነት ክልላዊ እቅድ እንጂ የከተማ መሪ እቅድ እንዳልሆነ ለመረዳት ብዙም አያዳግተንም፡፡ ሰፊ የገጠር አካባቢን (85 በመቶው የእቅዱ አካባቢ) አካልሎ ግቡን ኢንደስትሪያላይዜሽን ማድረጉንም ስናይ ‹ግዙፏ አዲስ አበባ በተግባር ደረጃ (de facto) የራሷ የሆነ ክልል (አስረኛዋ የኢትዮጵያ ክልል) ለመመስረት ጥረት እያደረገች ነው እንዴ?› ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ከላይ የጠቀስነው አደናጋሪው በፌደራል ስርዓቱ ውስጥ የአዲስ አበባ ‹ስታተስ› ጉዳይም እዚህ ላይ መሰረታዊው የጥያቄ ነጥብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
4.4. ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ እና ‹እቅዱ›
ከላይ በተራ ቁጥር 3 ላይ ሕገ መንግስቱ በተረቀቀበት ወቅት የነበረው የአዲስ አበባን ‹ስታተስ› ግልፅ ያለማድረግ ችግርና አዲስ አበባ ከምትገኝበት ኦሮሚያ ክልል ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ግልፅ ያለማድረግ ችግር ሕልዮታዊ ጥያቄዎችን ለማንሳት ሙከራ አድርገናል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ በተግባር እያጋጠሙ ያሉ ቸግሮችን በማንሳት የወደፊቱን ሁኔታ ለማየት እንሞክር፡፡
አብዛኛው የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል ውዝግቦች የሚነሱት ከድንበርና ከሉዓላዊነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ያለ ቅጥ እየተስፋፋች ነው፣ የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ እያጠፋች ነው፣ በሕገ መንግስቱ ለኦሮሚያ ክልል የተሰጣት ልዩ ጥቅም እስከ አሁን በሕግ ባለመወሰኑ ጉዳዩን አወሳስቦታል ወዘተ የሚሉ ትችቶች እየቀረቡ እስከ አሁን ቀጥሏል፡፡
4.4.1. ድንበር
የአዲስ አበባ ስፋት ባለፉት ሃምሳ አመታት ከእጥፍ በላይ አድጓል፡፡ በ1953 በሔክታር 21,800 የነበረው የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት በ1986 ወደ 53,014 ሔክታር ሰፍቶ፤ አሁን ያለውን የ54,000 ሔክታር ስፋት ደግሞ በ1996ቱን በከተማዋ መሪ ዕቅድ የተሰፈረላት ነው፡፡ በሀምሳ ዓመታት ውስጥ ከተማዋ በእጥፍ ያደገች ቢሆንም በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ግን አሁን ካላት ስፋት ብዙም የተለየ ነገር አላሳየችም፡፡ የከተማዋ ከኦሮሚያ ጋር ያላት የድንበር ውዝግብ ዋነኛ መነሻ የሆነው የድንበሩ አለመካለል (demarcation ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ውዝግቦች በጊዜው እንደሚነሱ ይሰማል፡፡ ተሾመ ያሚ የተባሉ የሕግ ባለሙያም በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ጥናት የኮልፌ-ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጋር እንዲሁም የንፋስ ስልክ-ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሰበታ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ ይገልፃሉ፡፡ እንዲሁም የገቢ ምንጭን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ኤጀንሲ ቢሮ ከአዲስ አበባ አቻው ጋር የተወዛገበባቸው አካባቢዎች እንዳሉ አያይዘው ይገልፃሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ግን መንግስት ሕጋዊ መፍትሔ ከመስጠት እና የሕግ አፈታቱን ከማሳደግ ይልቅ ተለመደውን ፖለቲካዊ መፍትሔ እየሰጠ ችግሩ አሁንም በዘላቂነት ያልተፈታ ጉዳይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
አዲስ አበባ አሁን ካላት ቦታ ውጭ (54,000 ሔክታር ወይም 527 ኪሜ ስኩየር) መስፋት አትችልም ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሕጋዊ መፍትሔ የሚሰጠን በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 ሲሆን አዋጁም ‹‹[የአዲስ አበባ የ] መስፋፊያ አካባቢ [የሚባለው] በማስተር ኘላኑ የቦታ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከልሎ ባለ የአርሶ አደር ወረዳዎች ስር የሚገኝ የለማ እና ወደፊት የሚለማ መሬት የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡›› በማለት ከተማዋ አሁን ካላት ቦታ ውጭ እንደማትስፋፋ ይገልፃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመመስረቻ ቻርተር 87/1989ም ሆነ ይሄን ቻርተር ሙሉ ለሙሉ ያሻሻሉት አዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የድንበሩ ጉዳይ ‹ወደፊት በውይይት ይካለላል› ከማለት በስተቀር ያስቀመጡት ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ መለጠጥ ያሳሰበው እና ይሄም መገታት አለበት ብሎ ያሰበው የኦሮሚያ ክልል በ2000 የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚል አዲስ ዞን የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልልን ግንኙነት ለማሳለጥ በሚል ሰበብ አቋቁሟል፡፡ አሁን የቀረበው ‹የልማት እቅድ› ደግሞ የልዩ ዞኑን ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በማስገባት ሌላ አዲስ መካረር ፈጥሯል፡፡
4.4.2. ቋንቋ
የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ስቴት ለዋና ከታማዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሰጠሁት መሬት ይመለስልኝ በማለት መሬቷን በ1846 አስመልሳለች፡፡ በሌላ በኩል አሁን ያለችውና መሬት ከሜሪላንድ ‹ስቴት› ወስዳ የቆመችው ዋሽንግተን ዲሲ ‹ራሷን የቻለች ክልል ትሁን የሚለውም› ሃሳብ ብዙም ተቃውሞ አይቀርብበትም፡፡ ለዚህም ለስላሳ ግንኙነት ዋነኛው መሰረትም የዋሽንግተን እና የዙሪያዋ ያለው የባህልና ቋንቋ መመሳሰል ነው፡፡
በተቃራኒው አዲስ አበባ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ካለው ቋንቋ የተለየ ነው፡፡ አዲስ አበባ አማርኛን ታወራለች ዙሪያዋ ደግሞ ኦሮምኛን ይናገራል፡፡ የቋንቋ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ‹አዲስ አበባ ለአማርኛ፣ አማርኛ ለአዲስ አበባ› ባሉት ፅሁፋቸው የአማርኛንና የአዲስ አበባን ግንኙነት ሲያስረዱ፡
ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ በኋላ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በየምክንያቱ ወደ ከተማዋ በመግባት በጉርብትና አብረው መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ ይህም ሁኔታ ሕዝቦችን ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪነት ወደ አንድ የጋራ ቋንቋ ተጠቃሚነት አሸጋገረ:: ልሳነ ዋህድ የነበረው ብሄረሰብ ልሳነ ክልዔ እየሆነ መጣ። አማርኛ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ከተመኛውን ሁሉ የሚያገናኝ የጋራ ቋንቋ ሆነ፡፡
አዲስ አበባና አማርኛ፣ ለርስበርሳቸው ብሎም ለመላው ኢትዮጵያ የለውጥ ተምሳሌት ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ብሄረሰብ በቤቱም ሆነ በአደባባይ የሚናገረው የራሱን ቋንቋና አማርኛን ነው ለማለት ይቻላል፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ በአደባባይ ሁሉም የሚናረው አማርኛን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መርካቶ የሚሰማው ቋንቋ ሌላ ሳይሆን አማርኛ ነው፡፡ አዲስ አበባ የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌት እንደሆነች ሁሉ፣ አማርኛም የዚሁ መግለጫ ነው፡፡ ከሁሉም ይወስዳል፣ መልሶ ለሁሉም ያሰራጫል፡፡ ሁሉንም ያገናኛል፣ ከሁሉም ቃል ይወስዳል፣ ለሁሉም ቃል ይሰጣል፡፡
በማለት ይገልፃሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አዲስ አበባን ያለ አማርኛ ማሰብ በፍፁም የማይቻል ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በዙሪያዋ ያሉት የአዲስ አበባ ከባቢዎች ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ‹ይህች እንደ አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ስልጣኔ ምልክት እየተደረገች የምትታይ ከተማ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ያለውን ኦሮምኛ ቋንቋ ያጨቁነዋል› የሚለው ሃሳብ የሚሰነዝሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ክልላዊ የልማት እቅድ ቀርቧል፡፡ እቅዱም ከቋንቋ ጋር በተገናኝ ያለውን ተቃውሞና ውዝግብ የበለጠ አክርሮታል፡፡
4.4.3. የገበሬ መሬት ለከተሜ?
ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሌላው እየቀረበ ያለው ጉዳይ አዲስ አበባ በሰፋች ቁጥር ገበሬዎችን እያፈናቀለች ቤት አልባ ታደርጋለች የሚለው ሲሆን፡፡ የተለያዩ ጥናቶችም ይሄን ያመላክታሉ፡፡ ፈየራ አብዲ የተባሉ አጥኝ አዲስ አበባ ከምስረታዋ ጀምሮ አሁን ያለችበትን ስፋት ለሜድረስ በዓመት በአማካኝ 400 ሔክታር ያህል ስትሰፋ ነበር ይላሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ከተማዋ በሕግ አግባብ ልትሰፋ የምትችለው ከተማዋ በቻርተር ከተማነት በተቋቋመችበት አዋጅ ቁጥር 87/1989 ላይ የተገለፀውን ‹የአዲስ አበባ ከተማ የከተማውን ክልል እና በመስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ያጠቃልላል›› ተብሎ በተገለፀው አግባብ ወዳሉት ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 (4) ላይ ‹‹የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኝትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው፡፡›› ተብሎ የተከበረውን የገበሬዎችን መብት ይጥሳል የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ነገር ግን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8 ላይ ‹‹መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኝው ተመጣጣኝ የካሣ ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል […] [መሬቱን] ሊወስደው ይችላል›› ተብሎ በመደንገጉ ይህ የገበሬዎች መብት ገደብ ያለው ነው የሚለው ሃሳብም እዚህ ላይ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡
ነገር ግን አሁን እየቀረበ ያለው ‹የተቀናጀ የጋራ እቅድ› ዓላማው ኢንደስትሪያላይዜሽን እንደሆነ ያስቀመጠ ሲሆን 1.1 ሚሊዮን ሔክታርን ያቀፈና 17 የሚሆኑ ወረዳዎችን የያዘ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ ይሄም እጅግ ብዙ የገጠር ቀበሌዎችን እንደሚያካትት ግልፅ ነው፡፡ ኢንደስትሪያላይዜሽንን መሰረት ያደረገ እቅድ በዚህ ያህል ቦታ ሲታቀድ ገበሬዎችን በገፍ አያፈናቅልም ብሎ ማሰብ ራስን ከማሞኘት ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም፡፡ መፈናቀሉንም ‹ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ስለተገን› ነው ብሎ ማሰብ የባሰ ሞኝነት ነው የሚሆነው፡፡
ሲጠቃለልም አዲስ አበባ በተሳሳተ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሌሎች ከተሞች በሀገሪቱ ውስጥ የሉም እስኪባል ድረስ ያለልክ ገዝፋለች፡፡ በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እቅድ አካባቢያዊ እቅድ ከመሆን ይልቅ ሀገራዊ እቅድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሃሉና በዳር ሀገሩ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ከመስራት ይልቅ አሁንም በፖሊሲ ደረጃ የአዲስ አበባን ግዙፍነት በበለጠ የማስቀጠል አካሔድ ነው አሁን እየተካሔደ ያለው፡፡ ይህ አካሔድ ደግሞ በፌደራል ስርዓት ሊኖር የሚገባው ግልፅ የሆነ ድንበር እና ‹ስታተስ› ካለመኖሩ ጀምሮ የተነሳ ሲሆን፤ በተግባርም ችግሮችን በፖለቲካዊ ውሳኔ አድበስብሶ የማለፍ ውጤት ሲጠራቀም ቆይቶ አሁን ላይ የደረሰ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ የገዘፈ እቅድን (ያውም ‹መሪ እቅድ› ይሆን ‹ክልላዊ እቅድ› በግልፅ ያልተቀመጠ እቅድ) ከአንድ ከተማ ጋር አያይዞ ማቅረብም ለጉልበተኛው የከተማ ገዥ ልሒቅ ተጨማሪ ሃይል በመስጠት ገበሬውን ከራሱ መሬት ወደ ጭሰኝነት የሚገፋ ነው የሚሆነው፡፡ ላልተሳካ ኢንደስትሪያላይዜሽን መሰረታዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የፌደራል ስርኣቱን በግዴለሽነት በመግፋትና በመሰለኝ ለማሳካት መሞከር ነገም ሌላ ችግር ነው የሚመዘው፡፡ ሕሩይ ሚናስን ከሩቅ ገነት ሁና በመግነጢሳዊ ሃይሏ ስባ ቤተኛ ያደረገችው አዲስ አበባስ እስከ መቼ ነው ሀገሪቱ በፖሊሲ ክሽፈት እየወደቀች ያለችውን የተለያየ ፈተና ለማለፍ መሳሪያ የምትሆነው? የፌደራል ስርዓቱስ እስከ መቼ ነው ሕጋዊነትን ሳይተዋወቅ የሚዘልቀው

Wednesday, December 30, 2015

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃዥተዋል “መሬት ቆርሰን አልሰጠንም… ነገር ግን ሱዳን ድንበር ውስጥ ገብተው የሚያርሱ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ”

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃዥተዋል “መሬት ቆርሰን አልሰጠንም… ነገር ግን ሱዳን ድንበር ውስጥ ገብተው የሚያርሱ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ” | ቪዲዮ

ዛሬ ፓርላማ ላይ የቀረቡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ድንበር ቆርሰን አልሰጠንም… ግን በሱዳን መሬት ውስጥ ገብተው እያረሱ ያሉ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ” ሲሉ ተናገሩ:: በቅርቡ የድንበር ማካለል እናደርጋለን ያሉትና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው የቀረቡት አቶ ኃይለማርያም በሱዳን መሬት ላይ ገብተው እያረሱ ያሉትን ባለሃብቶች ድንበሩ እስከሚካለል ድረስ አትንኩብን ስንል የሱዳን መንግስትን ጠይቀናል ብለዋል:: ቭዲዮውን ይመልከቱ::

Hailemaria

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49454

በእስር ላይ የሚገኙት እስራኤላዊው የትድሀር ኩባንያ ባለቤት ተደበደቡ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በተመሠረተባቸው ክስ ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙት የትድሀር ኤክስካቬሺን ኤንድ ኧርዝ ሙቪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ እስራኤላዊው ሚናሼ ሌቭ ዮሴፍ፣ በሌላ የውጭ አገር እስረኛ ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቆመ፡፡
ሚስተር ዮሴፍ በእስር ላይ በሚገኙበት በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እስር ቤት ውስጥ ታኅሳስ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ጉዳት የደረሰባቸው፣ የሱዳን ዜግነት ባለው ሌላ እስረኛ መሆኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የድብደባው ምክንያት እስካሁን አለመታወቁን የገለጹት የሪፖርተር ምንጮች እንደተናገሩት፣ ሚስተር ዮሴፍ ጭንቅላታቸውን በተደጋጋሚ ተመትተው ራሳቸውን በመሳታቸው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ገብተዋል፡፡
ተጐጂው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አንድ ቀን አድረው ታኅሳስ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ማረሚያ ቤት የተመለሱ ቢሆንም፣ በአንድ ጆሯቸውና በዓይናቸው ላይ የደረሰባቸው ጉዳት ስላለ በማረሚያ ቤቱ ክሊኒክ ውስጥ እየታከሙ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የተደብዳቢው ሚስተር ዮሴፍ ባለቤት ሚስ አናት ሌቪ ባለቤታቸው በጣም መጐዳታቸውን በመግለጽ፣ የባለቤታቸው ጉዳት መጠን ስለማይታወቅ መንግሥት ፈቅዶላቸው ወደ አገራቸው በመውሰድ እንዲያሳክሙ እየጠየቁ መሆኑንም ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ደብዳቢው ድርጊቱን ከፈጸመ ጊዜ ጀምሮ ለብቻው እንዳሰረውም ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ሚስተር ዮሴፍ የተደበደቡበትን ምክንያትና ስለደብዳቢያቸው ለማወቅ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል የቀድሞ አምባሳደርና ሌላ እስራኤላዊ ታኅሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ማረሚያ ቤት ሄደው የጠየቋቸው ቢሆንም፣ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ከተጐጂው ስላገኙት መረጃ ከመናገር መቆጠባቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡
በሚስተር ዮሴፍ ላይ ደርሷል ስለተባለው ድብደባና ጉዳት ማብራሪያ ለማግኘት፣ የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ኃላፊዎችንና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

Dawit Solomon Yemesgen's photo.

ሰበር ዜና ወያኔ የሚመራዉ የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ወታደራዊ ደህንነት በትናንትናዉ እለት ከ900 በላይ ወታደሮች ማጣቱን ለጠ/መከላከያ አሳዉቋል።





በዚሁ መረጃ መሰረት ወታደራዊ ደህንነቱ እንዳሳወቀዉ የሰሜኑ እዝ ዘመቻ መምሪያ እና ስምሪቱ ተመጣጣኝ የሆነ አስተላለፍ የላቸዉም! የወታደራዊ ፖለቲካ መምሪያዎችም በንቃትና በወቅታዊ ሁኔታዎዎች ከተጻራሪዎች አንሰዉ ተገኝተዋል! ሰራዊቱ የመዋጋት መንፈሱ ደካማ ነዉ! መግባባትና መከባበር በዉስጡ ጠፍቷል! የጎሳ መናጎጡ በእጅጉ እየከረረ በመምጣቱ አደጋ ላይ ነን
በተለይ በሰራዊቱ ዘንድ አስደንጋጭ ተብሎ የተወሰደዉ ከሰሞኑ በተደረጉ ዉጊያዎች ከተጻራሪ ሐይሎች የተኩስ እሩምታ የሰሙ ገበሬዎች ከኍላችን እየመቱን መሐል ላይ አጣብቂኝ ዉስጥ እየገባን ነዉ ሰራዊታችን ወደ ፊትና ወደ ኋላ መዋጋት ተስኖት እጁን እየሰጠ ሲሆን ከጀርባ የሚደበድቡን የራሳችን ሰራዊቶች ናቸዉ በማለት እርስ በእርሱ እስከመሞሻለቅ ደርሷል በዚህና በተለያዩ ምክንያቶች በሰሞኑ ብቻ በተደረጉ ጥቃቶች 900 ያህል ወታደሮች ተሰዉረዋል ሲል ብሶቱን አስተላልፏል።
ድል ለኢትዮ ጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

d2256-amharademocraticmovementforce-ethiopia2

የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ተሰማ

የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ተሰማ

481154_550780071735675_4995213108371569437_nየህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ስላለ የወሰደውን 100 ሺሕ ሔክታር፣ መጋዘን፣ የሠራተኞች ተገጣጣሚ ቤትን ለጨረታ ቢያቀርብም እስካሁን በሃራጅ ተሽጦ ባንኩ ሊያገኘው የቻለው 2.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የካሩቱሪ ዳይሬክተር ራማክሪሽና ካሩቱሪ ለ100 ሺህ ሔክታር ሊዝ መሬት አንድ ጊዜ የሚከፈል 5.6 ሚሊዮን ዶላር በባንክ እንዳይከፍል ታዞ በጥሬ ገንዘብ ጉዳዩ ለሚመለከተው ግለሰብ መክፈሉን መናገሩ ይታወሳል። መንግስትን የሚወክለው ግለሰብ መጀመሪያ 5.6 ሚሊዮን ዶላር ተቀብሎ በኋላ ካሩቱሪ መክፈል የማይችለውን 55.8 ሚሊዮን ብር እንዲበደር

Ethiopian government charging 1000 birr to release bodies of people killed in protest in Oromia

Ethiopian government charging 1000 birr to release bodies of people killed in protest in Oromia

  

The Ethiopian government is charging 1000 birr (50 USD) to families who went to morgues to collect bodies of their loved ones who were killed in the anti-government protest in Oromia, Chairman of the Oromo Federalist Congress, Dr. Merara Gudina told ESAT on the phone.
5000
Dr. Merara said families of the victims were also forced to sign a letter saying their loved ones were killed “while taking part in terrorism activities,” before they receive the bodies.
The news came as a shock to Ethiopians but many say they were not surprised as it is the nature of the brutal government in Ethiopia. “Oromia region is under a military rule,” Dr. Merara said from Addis Ababa.
OFC estimates at least 85 people were killed in the last three weeks and over 2000 were rounded up and detained by the regime’s Special Forces. Dr. Merara said some of those arrested were members of his party who took part in the last election and who have nothing to do with the protest.
Source: ESAT News (December 23, 2015)

Tuesday, December 29, 2015

ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ነው | በወታደሮች ተገደው የተደፈሩ ሴቶች አሉ

 

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰማ::
ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት መደፈራቸውን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል::
ፖሊሶች ሴት ተማሪዎችን መድፈራቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል::
ambo 2
ambo 3
ambo
 

Monday, December 28, 2015

ፕ/ት ባራክ ኦባማ የገና በአል ዋዜማን ለማክበር በተሰባሰቡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት የደረሰባቸው የሟቹ ወገኖችን አጽናኑ

 


የአሜሪካው ፕሪዜዳንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ( በታህሳስ 2, 2015 አ. ኤ. አ )በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት በሰምበርላንዲኖ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሁለት ባል እና ሚስት አሸባሪዎች የገና በአል ዋዜማን ለማክበር በተሰባሰቡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ባደረሱት ጥቃት አንድ ኤርትራዊ ወገናችንን ጨምሮ 14 ነጹሃን ሰዎች መሞታቸውን እና 21 መቁሰላቸውን ተከትሎ ፕ/ቱ ሰሞኑን የሟቶች ቤተሰቦችን በግንባር ተገኝተው ማጽናናታቸው ታውቋል።
ob
Obama e
obma
ባለፈው አርብ የሟቾች ቤተሰቦችን ለመጎብኘት ወደ ሰንበርላንዲኖ ጎራ ያሉት ኦባማ የሟቾች ቤተሰቦችን ከ አንድ መለሰተና ደረጃ የት/ቤት ቤተ መጽህፍት ውስጥ ለ ሶስት ሰአታት በፈጀ የተናጥል ውይይት “እግዚ አብሔር ያጸናችሁ “ በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል ። የአክራሪዎቹ ሰለባዎች ከሆኑት መካከል የ60 አመቱ ኤርትራዊው የሆኑት የጤና ጥበቃ ሰራተኛው ኣቶ ይሳቅ እሚኖ የተባሉት ወገናችን ቤተሰቦችን በግንባር ያነጋገሩ ሲሆነ የሟች አቶ ይሳቅ ልጆችን ቀረብ ብለው ያነጋገሩት ኦባማ “እናንተ የይሳቅ ምትኮች (አሻራዎች ) ናችሁ”በማለት አጽናንተዋል።
የአቶ ይሳቅ ወንድም የሆኑት አቶ ሮቤል ተክለ አብ በበኩላቸው ለተለያዩ የዜና ስዎች በሰጡት አሰተያየት “የፕ/ቱ አቀራረብ ቤተሰባችንን ከዚህ ቀደም በአካል የሚያውቁ የመሰል ነበር። ወንድሜ ይሳቅ በሕይወት በነበረበት ወቅት ለፕ/ት ባራክ ኦባማ ልዩ ፍቅር እንደነበረው ይናገር ነበር ። ኦባማ በ2009 እኤአ ለፕ/ትንት ባእለ ሰሜታቸው ላይ እንዲገኝ ወንድሜ የእንግድነት ጥሪ ወረቀት ተልኮለት ነበር። ሰለ ነገ ብዙ መናገር ባልችልም ከፕ/ት ኦባማ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ በጣም ገንቢ እና አጽናኝ ነበር “ብሏል። እ አኤ አ በ 2000 ለተሻለ ሕይወት ከ ኤርትራ ምድር ወደ አሜሪካ (ካሊፎርኒያ) የተሰደዱት ሟች አቶ ይሳቅ ለ 11 አመታት በጤና መኮንንት ያገለገሉ ሲሆን በ አሁኑ ወቅት የኮሌጅ ተማሪዎች የሆኑት ዮሴፍ፣ ብሩክ እና ሚልካ የተባሉት 3 ልጆቻቸውን በማሳደግ ለወግ ለማእርግ ለማብቃት ደከመኝ ሰለችኝ ሳይሉ ሲጥሩ ሕይወታቸው በድንገት የተቀጩ ታታሪ አባት እንደነበሩ የወንድማቸው /የእህታቸው ልጅ ዛኬ ገ/ኪዳን ያወሷቸዋል።
ሴት ልጃቸው ሚልካ ይሳቅ በበኩሏ ሰለወላጅ አባቷ ኣቶ ይሳቅ ስትናገር” አባቴ ርሁሩህ ሰው ነበር ። እናቴን ለምን እንዳገባት ሲነግረኝ አርሷን የመሰለች መለከመልካም እና ጥሩ ሴት ልጅ (ሚሊካን)ለማፈራት ሰለ ፈልግ በማሰብ እንደ ነበር ይመክረኝ ነበር። አባቴ ዛሬ በሁለት እግሮቼ ያለፈረሃት ቆሜ አንድሄድ ያስቻለኝ ታላቅ አባት ነበር። በማለት ሰለአባቷ ለጋሽነት፣ ግልጽነት እና የፍቅር ሰው መሆን ለ ሎሳንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ተናግራለች።
ይህ በዚህ እንዳለ የአሜሪካው የፈደራል የምርመራ ቢሮ(FBI) ለአቶ ይሳቅ እና ሌሎች 13 ሰላማዊ ዜጎች ሞት መንሰኤ ናቸው ያላቸው ባል እና ሚስቱ ሳይድ ሪዝዋን ፋሩክ እና ታሽፊን ማሊክ ከመቼ ጀምሮ ወደ አክራሪነት እንደተለወጡ ቁርጥ ያለ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸው እና መረጃውንም ለማገኘት ከወራት በላይ እንደሚፈጅባቸው ሃሙስ ታህሳስ 24 2015 ለንባብ የበቃው ሎሳንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ዳስሶታል።
የፈርንጆቹን የገና በአልን ከውይት ሃውስ ቤተመንግስታቸው ውጪ ለማክበር ሻንጣቸውን ከመሽንከፋቸው በፊት ከቀዳማዊት እመቤት ሚሺል ኦባማ ጋር ሃዘንተኞችን ለማጽናናት በአካል ሰምበርላንዲኖ ከተማ የተገኙት የ ልእለ ሃያሏ አገር አሜሪካ፣ ፕ/ት ኦባማ ለሁሉም ሃዘንተኛ ቤተሰቦች በጋራ ፣ በአንድነት እና በፍቅር መኖር የአሜሪካ እና የሕዝቧ ታላቁ የባሕል እሴት እንደሆነ እና በዚህም ጊዜ ሁሉም ወገኖች ለዚህ መሰሉ ድርጊት ተግባራዊነት ተግተው እንዲሰሩ ምክራቸውን እና ጥሪያቸውን አሰተላልፈዋል። በተለይ ደግሞ “ላለፉት ሁለት ሺህ አመታት የክርስቶስን መወለድ (የገና በእልን ሲያከብሩ የነበሩ የመካከለኛው ምስራቅ ዜጎች (ኢራቅ እና ሶሪያ) በአሁኑ ወቅት እራሱን የ እስልምና መንግስት እያለ የሚጠራው በአክራሪው ኢይሲስ እየደረሰባቸው ባለው ግድያ እና መዋከብ ሳቢያ የጌታ የአየሱስ ክርስቶስ መወልድን ለማብሰር ደውል እንዳይደወሉ እና ጸሎት እንዳያደርጉ የተገደዱት ክርስቲያኖችን ልናሰባቸው እና ልንጸልይላቸው ይገባል።” ሲሉ በፈርንጆቹ ገና ዋዜማ ሃሙስ እለት ላይ ከጽ/ቤታቸው የላኩት መልክት ያስረዳል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ አሜሪካ ገብተዋል

Ephrem Madeno
(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የነፃነት ሠራዊቱ ወዳለበት ኤርትራ በረሃ ባለፈው ኦገስት 2015 መጀመሪያ ላይ ከወረዱ በኋላ ሰሞኑን ወደ አሜሪካ እንደመጡ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሩ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለምን ወደ አሜሪካ እንደመጡ በማጣራት ላይ ይገኛሉ::
ሕወሓት በሚመራውና በሚያዝበት ፍርድ ቤት በአንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ “በሃገሪቱ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ፣ በሚዲያ ተቋማትና በባለስልጣናት ላይ አደጋን ለመጣል በሚል ክስ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እጃቸው ከተያዘበት እለት ጀምሮ በ25 ዓመት ዕኑ እስራት እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ፖለቲከኛ ናቸው:: በተጨማሪም ከእነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ክስ ጋር በዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው ይታወሳል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49485

መንግስት የሚጠቀምበት የኦሮሞ ቴሌቭዥን እና ራድዮ ድረገጽን ሃክ ተደረገ

ቦረንቲቻ ቡድን ሕወሓት የሚመራው መንግስት የሚጠቀምበት የኦሮሞ ቴሌቭዥን እና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አደረገ

ይህ ሃኪንግ ቡድን መንግስታዊውን የኦሮሞ ቴሌቭዥንና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አካደረገ በኋላ የራሱን መፈክሮች ለጣጥፎበታል
ይህ ሃኪንግ ቡድን መንግስታዊውን የኦሮሞ ቴሌቭዥንና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አካደረገ በኋላ የራሱን መፈክሮች ለጣጥፎበታል
(ዘ-ሐበሻ) ራሱን ቦረንቲቻ ብሎ የሰየውመና የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ አራማጅ ቡድን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ራዲዮና ቴሌቭዥን ድረገፅን መጥለፉን (Hacked) አስታወቀ::
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረው ሕዝባዊ ቁጣ በሳይበር በኩልም የቀጠለ ሲሆን ቦረንቲቻ የተባለው ቡድን የመንግስት ድረገጾችን ሃክ በማድረግ ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ ይገኛል::
ይኸው የሃኪንግ ቦድን በቅርቡ የመከላከያ ሚንስቴርና የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ድረገፆች ተመሳሳይ ጠልፏቸው እንደነበር ይታወሳል::

Ethiopian: Government threatens Facebook users

 

  

bye-729x445Following the current protest in the country, Ethiopian government is accusing  the social media users saying “they are inciting violence.”
The sole Television station in the country, owned by the government, EBC  is also propagating that the government must shut down the Face book and other social media outlets. EBC also advises the government to put a pressure on face book users.
In different public meetings the ruling party held last week following the protests over the vague Addis Ababa master plan, officials mentioned several times ‘Face book as a threat of the country’ and the means of inciting violence.
It is becoming clear that the government will go further in controlling the plat form and will threat the users very soon as it did on the newspapers and magazines shutdown a year ago.
Many face book users expressed their frustration on the statements of the government officials and told their friends they are quitting face book to avoid any problems from the security agents that may be following them.
Ethiopia is labeled as one the most censored countries in the world by CPJ.
The internet penetration in the country is below 2 present.

Saturday, December 26, 2015

Education bureau shuts down 96 private schools


Education bureau shuts down 96 private schools   
 



The Addis Ababa Education Bureau has shut down 96 private schools for “giving sub-standard education”. The schools were unable to provide the necessary facilities or resources needed to meet standards of educational institutions. Facilities like libraries, sports fields, and educational aids as well as adequate number of teachers were not provided in the schools.
The bureau accused the schools of ‘only chasing after money’, not caring about the environment their students are being taught in. Eighty percent of the 96 schools that were shut down are kindergartens previously banned from registering students this academic year.
“There is a standard for everything. Some of the schools work with unqualified instructors, some teach in congested classrooms, some of them increase fees without any reason. We have the duty to ensure the education quality is maintained,” said Gemechis Tekletsadik, Inspection Officer at the Education Bureau.
All schools were given prior warning and a grace period to meet the bureau’s standards before action was taken, according to Gemechis. “They dismiss good education and instead work at a very poor standard,” he added.
School owners, however, feel like they’re being held to standards without support. “They told us to bring the schools to highest standard in every aspect but the bureau never supported schools to reach that standard,” said a school owner.
Some school owners have lodged an urgent compliant to the bureau, claiming the closure of the schools will push students out of education for the year and put teachers out of a job.
“When investors ask the government to establish a factory, the government gives them incentives like giving them land, a tax holiday and other exemptions. But when one gets into education, there is no incentive. It is sad the government just proclaims it is striving to maintain the quality of education,” an owner reproached.
Owners further criticize the government for overlooking other important aspects affecting standards of education. “When condominiums are constructed in the city, no space is reserved for schools near the condos,” he pointed out.
Currently, over 1,600 private schools are working in Addis Ababa.

C
http://www.capitalethiopia.com/


Friday, December 25, 2015

80 Ethiopian Troops Defected to Eritrea Amid Oromo Protests


Around 80 Ethiopian soldiers defected to Eritrea in the central front (Zalambesa Area) the past few days. Most of the defected soldiers are reportedly from the Oromo ethnic group.
22 defected Ethiopian soldiers in Eritrea
File photo of 22 defected Ethiopian soldiers in Eritrea
Ethiopian soldiers who arrived in Eritrea opposing the racist policy of the TPLF regime disclosed the regime is resorting to increased atrocities by imprisoning members of different ethnic groups.
They noted that many Ethiopian soldiers are defecting to different opposition organizations and fleeing to neighboring countries opposing the brutal and harsh measures the TPLF regime is taking against the Ethiopian people.

Thursday, December 24, 2015

በአዲስ አበባ አንዲት እህት በጠበል ከሆዷ ውስጥ ጥቁር ወፍ ወጣላት

«አንዲት እህት ከሆዷ ውስጥ ጥቁር ወፍ ወጣላት»
በቅዱስ ዮሐንስ ጠበል ከሆዷ ወፍ የወጣላት እኅት
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ጠበል ሰሞኑን ከአንዲት እኅት ከሆዷ ጥቁር ወፍ ወጣላት፡፡ በክርስትና ስሟ መንበረ ማርያም ተብላ የምትጠራው እኅት ለ20 ዓመታት ያህል በሆድ ሕመማት ስትሰቃይ መቆየቷን የምትናገረው መንበረ ማርያም፤ ስቃይዋን በዘመናዊው ሕክምና ለማስታገስ ያልሔደችበት ቦታና ያልወሰደችው መድኃኒት የለም፡፡ ይሁንና የምትወስደው ሕክምና ለጊዜው ስቃይዋን ከማስታገስ በስተቀር ከሕመሟ ልትድን ባለመቻሏ ከዚህ በኋላ ይግደለኝ እንጂ ሕክም ናም ሆነ መድኃኒት መጠቀም የለብኝም፤ ብላ ጠበል ለመጠመቅ እንደ ወሰነች ትናገራለች፡፡ በውሳኔዋም መሠ ረት ወደ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ጠበል በመሄድ ስትጠመቅ በላይዋ ላይ የሰፈሩ 681 አጋንንት እንዳሉ በላይዋ ላይ ያደሩት የሰይጣን ሠራዊት ለፍልፎ በጥቁር ወፍ አምሳል ከሆዷ ውስጥ ሊወጣላት ችሏል፡፡ ምእመናን በዕለቱ ከሆዷ ውስጥ በትውከትነት እንደ ጥይት ተወርውሮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በማየት በቪዲዮ በመቅረጽ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር እንደ መሰከሩ ተገልጿል፡፡
የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ሰምቶ ይህንኑ ወፍ የወጣላትን መን በረ ማርያምንና ያጠመቋትን አባት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱን በማነጋገር ድርጊቱ እንዴትና ምን ይመስል እንደነበር በሰፊው ዘግቧል፡፡
እግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ተዓምሩ ዕፁብ ነው፤ ተነግሮ አያልቅም፤ ይህን ሥራውን መመስከር ደግሞ የእኛ ተግባር ነው፡፡ ለረጅም ዓመታት በሕመም ስትሰቃይ የነበረች በስመ ጥምቀቷ መንበረ ማርያም የተባለች ወጣት የእግዚአብሔርን የድንቅ ሥራው መገለጫ ሆናለች፡፡
ለዚህች እህት እግዚአብሔር ያደረገላት ገቢረ ተአምር ሲሰሙት ለጆሮ የሚከብድ፤ እንዲሁም በወቅቱ ድር ጊቱ ሲፈጸም የተመለከቱ ምእመናንን ሁሉ ያስደመመ ነበር፡፡ «ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ» ነውና ሥረ መሠረቱ ምን፣ እንዴትና መቼ ሆነ? የሚለውን ጉዳይ እሷው ባለታሪኳ እንዲህ ትተርክልናለች፡፡
«ያመኝ የነበረው ገና የአራት ዓመት ልጅ እያለሁ እሰቃይ ነበር፡፡ ለምሳሌ የራስ ምታት፣ ነስር፣ የሆድ ቁርጠት፣ የአንጀት ኢንፌክሽን ወዘተ እየተባለ በመታመም ሁልጊዜ ሐኪም ቤት እመላለስ ነበር፡፡ እናቴ እንደ ነገረችኝ የሕመሙ መነሻ ወተት ነው፡፡ «ወተት ጠጥተሽ የአንጀት ኢንፌክሽን ያዘሽ» ያለችኝ እናቴ በየክሊኒኩ እየወሰደችኝ ስታስመረምረኝ መድኃኒት እንደሚያዙልኝ አጫውታኛለች፡፡ ራሴን ማወቅ ስጀምር ትምህርት ቤት ገብቼ ስማር ሆዴን ያመኛል፡፡ በተለይ በበጋ ወራት ተምሬ ሁለት ወር ክረምት በሚሆንበት ወቅት ክፉኛ ያመኛል» ስትል ተናግራለች፡፡
መንበረ ማርያም በሕመሟ መጥናት ብዙ ጊዜ ሐኪም ቤትና ክሊኒክ ተመላልሳ እንደታከመች ገልጻል ናለች፡፡ ነገር ግን ጠበልስ አልሞከረች ይሆን? የሚለው ጥያቄ አጫረብንና ጠየቅናት፤ እርሷም ስትመልስ «በዚያን ወቅት ቤተሰቦቼ የሚያስቡት ሐኪም ቤት የሚባለውን እንጂ ጠበልን አልነበረም፡፡ እኔም ቢሆን በወ ቅቱ ጠበልን አላሰብኩትም፤ ብቻ ሐኪም ቤት ሔጄ የተለያየ መድኃኒት ይታዘዝልኛል እወስዳለሁ፡፡ ለጊዜው ያስታግሥልኛል፤ ጨርሶ ግን ሊያድነኝ አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስጄ ጥሩ ውጤት በማምጣት አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ የመጀመሪያ ዓመት መማር ስጀምር በሽታው ክፉኛ አሰቃየኝ፡፡ ያስጨንቀኛል፣ ከፍተኛ የራስ ምታት ሕመም ይሰማኛል፤ ማጥናት አልችልም ነበር፡፡ የሴሚስተር ፈተና ደርሶ ሁለት ሳምንት ሲቀረው አንደኛው ዐይኔ ውስጡ ሲቆስል ሌላኛው ዕንባ ማፍሰስ ጀመረ፡፡ ዕንባው ያለምንም ማቋረጥ ለ24 ሰዓታት ይወርዳል፡፡ ቤተሰቦቼ ሁኔታው አላምር ቢላቸው ወደ አንዲት ታዋቂ የዐይን ሐኪም ወሰዱኝ፡፡ እሷም 'በሕይወቴ እንዲህ ዐይነት ነገር ዐይቼ አላውቅም፤ ዐይኗ ውስጥ ቁስል አለና የመታት ነገር አለ ወይ?' ብላ ጠየቀች፡፡ ይሁንና ቤተሰቦቼም ሆኑ እኔ ምንም ነገር የመታኝ ነገር እንደሌለ ለዶክተሯ ነገርናት፡፡ በየሰዓቱ የሚደረግ ጠብታ አዛልኝ ለጊዜው ተሻለኝ፡፡ የከፍተኛ ትምህርቴን ግን ሳልማር ለሁለት ዓመት ያህል አቋረጥኩ» ትላለች የሕመሙን አስከፊነት የምትናገረው መንበረ ማርያም፡፡
መንበረ ማርያም እንደገለጸችልን በጤና መታወክ ሳቢያ ለጊዜው ትምህርቷን ብታቋርጥም ለትምህርቷ ያላት ቁጭት ከፍተኛ ስለነበር በሽታው መጣ ሔድ እያለ ቢያስቸግራትም ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመግባት ትምህርቷን በሥራ አመራር የትምህ ርት ዘርፍ ለአራት ዓመታት ያህል ተከታትላ በ1996 ዓ.ም በዲግሪ ተመርቃለች፡፡
ይሁንና ሌላ ያላሰበችው ችግር ገጠማት፤ ይህስ ምን ይሆን? ለዚህም መንበረ ማርያም ስትናገር «የወር አበባዬ ከመጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን እስከዳንኩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ በጣም እያመመኝ ክፉኛ ያሰቃየኛል፡፡ ስቃዩን ለማስታገሻ እያልኩ ፓ¬ራሲታሞል ክኒን በየአራት ሰዓት ልዩነት ሁለት ሁለት ፍሬ በመዋጥ በቀን 10 ፍሬ እወስድ ነበር፡፡ ሐኪም ቤትም ብሔድ የሚሰጡኝ መርፌ ነው፡፡ አልሻል አለኝ፡፡ የሕክምና ባለሙያዎቹ 'አግብታ ትውለድ፤ ሴቶች እንዲህ ዐይነት ሕመም ሲሰማቸው ይሻላቸዋልና መውለድ አለብሽ' ብለው አስተያየት ይሰጡኛል» ትላለች፡፡
እንደ መንበረ ማርያም አገላለጽ ብዙ ጊዜ መድኃኒትም መዋጥ ሌላ ችግር /Side-effect/ ስላለው መድኃ ኒት መውሰዱን ታቋርጣለች፤ «ከድጡ ወደ ማጡ» እንዲሉ ይባስ ብሎ በየወሩ ያማት የነበረው እንደ አዲስ የማያቋርጥ የማኅፀን ሕመም ይሰማት ጀመር፡፡ በዚህን ጊዜም በታወቁ የማኅፀን ሐኪም በመታየት በወር አበባ ሳቢያ የተነሣ በማኅፀኗ ውስጥ ትናንሽ ዕጢዎች እንዳሉ ይነገራትና የወር አበባዋ ከመምጣቱ በፊት ለአንድ ሳምንትና ከመጣም በኋላ ለአንድ ሳምንት የሚወሰድ ከባድና በጣም ውድ የሆነ መድኃኒት ይታዘዝላ ታል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ዓመት በፊት ነው፡፡
«በዚህን ጊዜ የመጨረሻ ቁርጥ ውሳኔ ወሰንኩ» ትላለች መንበረ ማርያም፡፡ «መሞቴ ለማይቀር ነገር ለምን እሰቃያለሁ? በመድኃኒትስ ለምን እቃጠላለሁ?» በማለት ወደ ጠበል ቦታ ለመሔድ ወሰነች፡፡ ጠበሉን እንድትሞክር ያነሣሣትና ምክንያት የሆነቻት ደግሞ ጓደኛዋ እንደሆነች ተናግራለች፡፡ «አንድ ጓደኛዬ እንደ እኔ ዓይነት ሕመም ይሰማት ስለነበር ጻድቃኔ ማርያም ሔዳ ጠበል ጠጥታ እንደዳነች ነገረችኝ፡፡ እኔም ጠበል መጠጣትና መጠመቅ እንዳለብኝ መከረችኝ፡፡ መድኃኒቱን አቋርጬ ጠበል መጠመቅ ጀመርኩ፡፡ እየጾምኩ በተከታታይ ጠበሉን ስጠጣና ስጠመቅ በየወሩ የወር አበባዬ ሲመጣ ያመኝ የነበረውን ተወኝ፡፡ በመቀጠል ከማኅፀኔ ሥጋ ነገር ተቆርጦ ወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ቤተሰቦቼ «እጢው ወጣልሽ» በማለት ተአምር አሉ፡፡ ሥጋ መሰል ባዕድ አካል ከወጣልኝ በኋላ ምንም ዓይነት ስሜት ሳይሰማኝ ጤነኛ ሆንኩ፤ ጠበሉንም አቋረጥኩት» በማለት ገልጻለች፡፡
በዚህ መልኩ ለውጥ ያገኘችበትን ጠበል ስታቋርጥ ዳግም ሕመሙ ጀመራት፡፡ መንበረ ማርያም ትናገራ ለች፡፡ «ጠበሉን ለአንድ ዓመት እንዳቋረጥኩ በሽታው በባሰና በሚያስፈራ መልኩ ተመልሶ መጣ፡፡ እንደገና ጠበሉን መጠጣት ጀመርኩ፤ በዚህን ጊዜም ደጋግሞ የሆነ ነገር በሕልሜ ያሳየኛል፤ በሆነ መንገድ ላይ በጣም ጥቁርና ትልቅ ሰውዬ ዝም ብሎ ቆሞ ዐያለሁ፣ ቀጥሎ እኔ ሕፃን ልጅ ታቅፌ ሳመልጥ እሱ ትልቅ ድንጋይ ይዞ እየተከተለ በማስፈራራት ሲያሯሩጠኝ ዐያለሁ፡፡ ይህን ያየሁት በድሮው ቤታችን መገናኛ አካባቢ ነው፡፡
የመንበረ ማርያም ዋናው ታሪክ የሚጀምርው በግንቦት ወር 2001 ዓ.ም ነው፡፡ በዕለተ ሰንበት እሑድ ቀን ቅዳሴ አስቀድሳ ስትመለስ እንደተለመደው የወር አበባ ይታያትና በቃላት ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ በጽኑ ትታመማለች፡፡ መንበረ ማርያም እንደገለጸችው «መጽሐፈ አርጋኖን ይዛ ከአንዱ ክፍል ወደ አንዱ ክፍል እየተንቆራጠጠች 'ወይኔ! እመቤቴ ኧረ አድኚኝ' እያለች መኝታ ክፍሏ ሆና ስታጣጥር በድንገት በግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ታያለች፡፡ እያጣጣርኩ በክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ድንገት የተሰቀለውን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ቀና ብዬ ማየት ስጀምር የፌዝ ሳቅ መሳቅ ጀመርኩ፡፡ በዚህን ጊዜ ራሴን እየለወጠኝ ነው፤ አልፎ አልፎ እንጂ ምን እንደምሠራም አላውቅም፤ መጣሁልህ ይላል፡፡ እንደዛር ማጓራት ጀመርኩ፤ አባቴ ሲሰማ ደነገጠ፡፡ እሱ እንደነገረኝ ሁለት እጄን ይዞ የቅዱስ ገብርኤል ጠበል እየረጨ 'አንተ ማነህ?' ሲለው 'እባክህ አንተ አታውቀኝም! ዝም ብለህ ነው፤ ተቃጠልኩ ጊዜዬ ሲደርስ የምለቅበት ቀን አለ፡፡ እሷን የያዝኩት ከማኅፀን ጀምሮ ያሳደግኳት እኔ ነኝ' በማለት ለፈለፈ፡፡ በመቀጠል 'እናቷንም የገደልኩ እኔነኝ' ሲል ራሱን ገለጠ» በማለት መንበረ ማርያም አስረድታለች፡፡ እናቷ በካንሰር ሕመም ምክንያት በ1995 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንም ገልጣልናለች፡፡
በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ሳቢያ ማንነቱን የገለጠው ሰይጣን እንደያዛት ስታውቅ፣ የትመጠመቅ እንዳ ለባት ታስባለች፡፡ በመጨረሻም በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ሔዳ ጠበል መጠመቅና መጠጣት ትጀምራለች፡፡ በአምስተኛው ቀን ያደረባት ርኩስ መንፈስ መለፍለፍ ይጀምራል፡፡ በተለይ ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ ስትጠመቅ 681 አጋንንት እንደ ሠፈረባት ይለፈልፋል፡፡ ብዙ ሰው እንደጨረሰና አሁንም ብዙዎችን እንደያዘ ገልጾ እርሷ ላይ ሲደርስ ግን እንደተጋለጠ ተናግሯል፡፡ «ምእመናን እንደነገሩኝ ከሆነ «አንቺ ስትጮኺ እንደ አንበሳ ነው፤ የሚያስፈራና ከአንቺ የሚወጣ ድምፅ አይመስልም ብለውኛል፡፡ እኔ ግን በመሐሉ «መድኃኔዓለም መጣ» የሚል ድምፅ ሰማሁ እንጂ ራሴን አላውቅም፡፡
መጨረሻ ላይ ራሴን ሳውቅ ከእኔ የወጣውን ጥቁር ወፍ ይዘው አሳዩኝ፡፡ አላመንኩም፡፡ ሰው እልል እያለ 'አይዞሽ ተነሽ እመቤታችን ከነልጇ የሠራችልሽ ተአምር በጣም ድንቅ ነው፡፡ ተነሥተሽ ድንቅ ተአምሯን ትመሰክሪያለሽ' አሉ፡፡ ልብሴን ለብሼ ስወጣ ብዙ ምእመናን ቆሞ በሞባይልና በቪዲዮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ይቀርጻል፡፡ ከሆዴ የወጣው ትልቅ አፍ ያለው ወፍ ደም ጎርሶ በሕይወት ለተወሰነ ደቂቃ ልቡ ይመታል፡፡ እኔ ራሴን አላመንኩም፤ ደስታ አይሉት ሐዘን ተደበላለቀብኝ፣ ሰውነቴ ከላይ እስከታች ይርዳል» ስትል የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር መስክራለች፡፡
ሰኔ 10 ቀን ከ681 አጋንንት ውስጥ ሰማንያው ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ ሰኔ 12 ቀን ሌሎች ቀሪዎቹ በጉንዳን መልክ ወጥተናል ብለው በመለፍለፍ ለቀቁ፡፡ በወቅቱም የጠበሉ ቦታ በጉንዳን ተወሮ እንደነበር መንበረ ማርያም ገልጻለች፡፡ ያ በሕልሟ ሲያባርራት ያየችው ጥቁር ሰው እርኩስ መንፈስ እንደሆነና ሕፃኑ ደግሞ መድኃኔዓለም ሆኖ እንዳዳናት አምና ተርጉማዋለች፡፡
መንበረ ማርያም ስለተደረገላት ድንቅ ተአምር ሰኔ 10 እና 21 ቀን 2001 ዓ.ም የእመቤታችን ክብረ በዓል ዕለት በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን በመድረክ ላይ ወጥታ ለሕዝበ ክርስቲያኑ መስክራለች፡፡
በመጨረሻ ያነሣንላት ጥያቄ «የተደረገልሽን ተአምር እንዴት ትገልጭዋለሽ?» ነበር፡፡ እሷም «እግዚአብሔር ያደረገልኝን ድንቅ ተአምር በቃላት ልገልጸው አልችልም፡፡ ኃያሉ እግዚአብሔር እኔን አድኖኛል ምስጋና ይድረሰው፡፡ እኔ ግን የማተኩረው ስለተደረገልኝ ተአምር መመስከር ብቻ ሳይሆን ስለማስተላለፈው ነገር ነው፡፡ ይኽም እግዚአብሔር እንዲህ ማዳን እየቻለ ሰይጣን ሊሰለጥንብን አይገባም፡፡ በሥራ፣ በትምህርት ቤትና በዕለት ተዕለት ሥራችን ላይ ውጤታማ እንዳንሆን መሰናከል እየሆነ ነው፡፡ ሕይወታችንን እያበላሸ መሆኑን አልተረዳንም፡፡ ስለዚህ ስመ ክርስትና ብቻ ይዘን መቀመጥ ሳይሆን በጾም በጸሎት እግዚአብሔርን ማገልገል ይኖርብናል፡፡ ከንስሓ አባት ጀምሮ የሃይማኖት አባቶችም ማስተማር አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ራሱን ይመርምር፤ ክፉ መንፈስን መዋጋት አለበት» ብላለች፡፡
«ማየት ማመን ነው» እንደተባለው በወቅቱ በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም የጠበል ቦታ ሲያጠምቋት የነበሩትና ድርጊቱን የተመለከቱት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱ ስለሁኔታው እንዲነግሩን ጠይቀናቸው እሳቸውም ታሪኩን እንዲህ አወጉን፡፡ «ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፤ ነገሩ ተአምር ነው፡፡ ከዚህ በፊት በእርኩስ መንፈስ የታሰሩ፣ የተተበተቡ ሰዎችን በእግዚአብሔር ኃያልነትና መስቀል በመታገዝ በላያቸው ያለውን አጋንንት አስለቅቄያለሁ፡፡ ይህ ግን ልዩና በሕይወቴም ገጥሞኝ የማያውቅ ነው፡፡ በዕለቱ እኅታችን መንበረ ማርያም ወደምትጠመቅበት ክፍል ስትገባ ጀምሮ በጣም ትጮሃለች፡፡ በመስቀል እያጠመቅሁ ምንድን ነህ? ስለው አጋንንት ነን አሉ፡፡ ቀጥሎ ስንትናችሁ? አልኩት 600 አጋንንት ነን አሉና እውነቱን አውጣ ብዬ አጥብቄ ስይዘው 680 ብሎ ለፈለፈ፡፡ መጨረሻ ላይ 681ኛ ተልከስካሽ የዛር መንፈስ እንዳለ ገልጾ ከሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በአራት ቀናት ውስጥ ተከፋፍሎ ወጣ» ብለዋል፡፡
እንደ እሳቸው አባባል ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም 80ው ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ፤ በነጋታው «593ቱ ጉን ዳን ሆኜ እወጣለሁ» ብሎ ጮኸ፤ ሲለቅ ወዲያውኑ ከየት መጣ ሳይባል አካባቢውን ጉንዳን ወረረው፡፡ በሦስተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ሲወጣ ከሰባቱ አንዷ ብቻ ሴት ሆና ተገኘች፡፡ እሷም «ከውጭ ሀገር ነው የመጣነው፤ ሥራችን ተመሳሳይ ፆታዎችን ማጋባት ሲሆን በውጭው ዓለም አጥለቅልቀነው ወደ አፍሪካና ኢትዮጵያ በብዛት እየገባን ነው» ብላ ተናግራለች፡፡
«በመጀመሪያ ዋናውና አለቃው ' አጋንንት ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ 600ው ሠራዊት ነኝ ብሎ ወጣ፡፡ አለ ቃውን አጋንንት» እንዴት ብለህ ነው የምትወጣው» ስለው እንደ አንበሳ አጓርቼ እወጣለሁ አለ፡፡ ልጅቷ እንደ አንበሳ እያጓራች ሳለ ጥቁር ወፍ በደም ተለውሶ ከሆዷ ውስጥ በአፏ ወጣ፤ ሲወጣም ልክ እንደ አየር ሞገድ ተወርውሮ ገንዳ ነገር ላይ አረፈ፡፡ ይህ እርኩስ መንፈስ ወፍ ሆኖ ሲወጣም ግፊት ስለነበረው እኔን ሁሉ ገፍትሮኛል፡፡ የወጣው ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በመሆኑ ለተወሰነ ደቂቃ የማስካካት ድምፅ አሰምቷል፡፡ ለግማሽ ሰዓት ያህልም በሕይወት ቆይቶ ምእመናን ዐይተውታል፡፡ ድርጊቱ የሁሉንም መንገደኛ ቀልብ የሳበ ስለነበር መናፍቆች ሳይቀሩ ተመልክተው በእመቤታችን ድንቅ ተአምር ተገርመ ዋል፡፡ በተለይ አንድ ከነቀምት የመጣ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በተአምሩ ተደንቆ ሲያለቅስ ዐይቻለሁ» በማለት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አስረድተዋል፡፡
«አጋንንቱ መንበረ ማርያምን እንዴት እንደያዛት ስጠይቀው በተለያየ ምክንያት በይበልጥ በዛር ውላጅ ሲወርድ ሲዋረድ በዘር ሐረግ የመጣ እንደሆነ ለፍልፏል፡፡ ለ20 ዓመታት ያህል በሆዷና በማሕፀኗ ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረስ ያሰቃያት እንደነበር ዘርዝሯል፡፡ በወር አበባዋ ጊዜ ምጥ እያበዛ ያሰቃያት እንደነበር ተናግሯል፡፡ እመቤቴ፣ እመቤቴ እያለች የእመቤታችን ማርያምን ስም እየጠራች አስቸገረችኝ እንጂ ሆዷን ኦፕራሲዮን አስደርጌ በሰበብ ልገድላት ነበር» ሲልም ተናግሯል ይላሉ፡፡
«ድርጊቱ በጣም የሚከብድ እና በእኔ ላይ የደረሰ ያህል ተሰማኝ፤ እኔም በሁኔታው በጣም ያዘንኩበትና ያለቀስኩበት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ድርጊት በእኔ ላይ ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ምን ልሆን እንደምችል ትንሽ ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እሷ ግን እጅግ በጣም ጠንካራ፣ በእምነቷ ጽኑ ነች፡፡ በእምነቷ ጽናት እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን ሠራላት፡፡ አሁን ሙሉ ለሙሉ ጤነኛ ነች ብለዋል፡፡ እርኩስ መንፈሱ አባቷን ሳይቀር ሌሎች ሰዎችንም ይዣለሁ ብሎ በመለፍለፍ ልጅቷ ቤት ድረስ በመሔድ መጥተው እንዲጠመቁ ተናግሬያለሁ» በማለት ሊቀ ትጉኃን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም «የማስተላልፈው መልእክት አለ፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ሥራ ይሠራል፤ እግዚአብሔር እኛ እንድንድን የማያደርግልን ነገር የለም፡፡ ከዚች እኅት ትልቅ ትምህርት አግኝተንበታል፤ የክርስቶስ ስልጣን ይህን ዐይነት የሚሠራ ከሆነ እኛ የት ነን? ብለን ማሰብ አለብን፡፡ ትንሽም ብትሆን እምነት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ጠበሉን፣ እምነቱን ልንጠጣ ይገባል፤ ሥጋና ደሙን ልንቀበል ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከሆነ መዳን እንዳለ ማመን ይገባል» ሲሉ ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱ አስረድተዋል፡፡
በርግጥም መንበረ ማርያምና አጥማቂዋ ሊቀ ትጉኃን እንደገለጡት በየጠበሉ ቦታ ሲታይ በርኩስ መንፈስ በመተት፣ በዛር፣ በአጋንንትና በመሳሰሉት የተያዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ኃይል ሲፈወሱ ማየት ጉድ ያሰኛል፡፡ ሰይጣን የምንፈራው ሳይሆን ታግለን የምናሸንፈው መሆኑን ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊረዳው ይገባል፡፡ አውቆም በጾም በጸሎት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የበለጠ ደግሞ መምህራን ሓላፊነት ወስደው ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»

በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል

በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል
 በገብረመድህን አርአያ


ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው።
ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። በኢትዮጵያና በህዝቧ፣ 1ኛ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አውዳሚ፣ 2ኛ፣ አንድነቱን
ጠብቆ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ በዘር ለመበታተን ተደምሮና ተቀንሶ የተቀነባበረ አደገኛ ፕሮግራም በማለት አውግዘውት ነበር። ከነዚህ ካወገዙት መካከል ለምሳሌ ለመጥቀስ፤ አስገደ ገብረሥላሴ፣ ካህሳይ በርሄ (ዶ/ር ግንጽል)፣ ተሾመ ጉዶ፣ ሲሆኑ እነዚህ በህይወት ያሉ ሲሆን፣ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋእድ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዘርኡ ገሰሰ (አጋአዚ)
ገሰሰው አየለ፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ ዘወንጀል በየነ፣ መሃረ ተክሌ ወዘተ እነዚህ ፕሮግራሙን በጠነከረ አቋም ስለተቃወሙ የተገደሉ ናቸው። ተሓህት የፕሮግራም ዝግጅቱን ንድፈ ሃሳብ የጀመረው ገና በረሃ ሳይወጣ ማገብት ተብሎ በሚጠራበት ከ1966 ጀምሮ ነው። ይህንን ፕሮግራም በሃላፊነት ያዘጋጀው አረጋዊ በርሄ ሲሆን፣ ጥር 1967 ለወታደራዊ ስልጠና ኤርትራ፣ ስህል ወርደው
ፕሮግራሙን በማጠናከር የተሰማሩት የትጥቅ ትግሉ መሪዎች አረጋዊ በርሄ፤ በዋና ሃላፊነት፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አስፍሃ ሃጎስ፣ በህመም የሞተ፣ ዘርኡ ገሰሰ፣ በወያኔ የተገደለ፣ ሥዩም መስፍን፣ ሃይሉ /ነጠበ/መንገሻ ሲሆኑ ብዙ የጎደለው እንዳለ ተስማምተው በይደር ወደ ደደቢት ተዘዋወረ።
የካቲት 11፣ 1967 ታጋዮቹ ደደቢት በረሃ እንደገቡና የትጥቅ ትግሉ እንደተጀመረ፣ ግንባር ቀደም ተግባራቸው ሶስት ነጥቦች ላይ ነበር ትኩረት ይሰጠው። 1ኛ፣ የድርጅቱን ስም ማውጣት፣ 2ኛ፣ ለወደፊቱ ለምትመሰረተው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የግዛት ስፋት ከውጭ ሃገር፣ ሱዳን በሚገኘው መልኩ ማዘጋጀት፤ 3ኛ፣ ፕሮግራሙን ለመጨረሻው ዝግጅቱ ታማኝ ታጋዮችን
በማሰባሰብ ለሚከተሉት ሰዎች፣ ማለትም፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ሥዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ስየ አብርሃ፣ ግደይ ዘርአጽዮን ወዘተ ሃላፊነቱ ተሰጠ። ለዚህ መሰናዶ ከበጌምድር ጠቅላይ ግዛት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ፣ ወልቃይት እንዲሁም ከወሎ ጠ/ግዛት፣ ራያና ቆቦ፣ ወልድያ፣ አላማጣ እስከ ላይኛው ሃሸንጌ ሃይቅ ድረስ በማጠቃለል የትግራይ መሬት ነው ተብሎ በመወሰን የፕሮግራሙን አቋም ደመደመ። ይህ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በእጅ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ወደ 30 ገጽ የሚሆን ተባዝቶ በመጽሓፍ መልክ ተጠርዞ በብዛት ተያዘ።
በሃላፊነት የጻፉት አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ ናቸው። በየቦታው እንዲሰራጭም ተደረገ።
ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ኢትዮጵያን ለመበታተን፣ ሕዝቧን በዘርና በጎሳ የከፋፈለ፣ አማራውን ደመኛ ጠላት ብሎ ያወገዘ ሆኖ የመጣና እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት የሆነ አስተሳሰብ ነበር።
አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው፣ ከሚለው ቀጥሎም ለብዙ ዓመታት ነፃ ሃገር ትግራይ ነፃነቷ ተገፎ በአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ አገዛዝ ወድቃለች፣ በማለት ብዙ ይተነትናል። በአጼ ዮሃንስ ዘመነ መንግሥት ሃይሏ በርትቶ በአካባቢዋ የነበሩትን ነገሥታት በቁጥጥር ስር አውላ ነበር። ይሁን እንጂ አፄ ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ አማካኝነት ትግራይ በሸዋው ማእከላዊ ግዛት ስር ወደቀች። ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው አማራው የመሳፍንት ቡድን እና ተከታዮቹ የትግራይን ነፃነት ገፈው
የህዝቧን አንድነት ያናጉት። በግልጽና ስውር በሆነ ዘዴዎች (ሸዋዊ ዘይቤዎች) የትግራይ ህዝብ በድንቁርና፣ በበሽታ፣ በረሃብ አዘቅት ውስጥ እንዲሰምጥ ያደረጉት እያለ ይቀጥላል።
ከላይ የተጠቀስውና ሌላውን ጨምሮ ተሓህት የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራ ነው፣ ነፃ ሃገር የነበረቸው ትግራይ ሃገርህ በአማራ (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ሆና አንተ ለክፉ መከራ ተረግህ በማለት አመራሩ በሙሉና የተሓህት ታጋዮች ወደ ህዝቡ ተበታትነው ፖለቲካቸውን አስተማሩት። ማንኛውም የትግራይ ህብረተሰብ ይህ የምትናገሩት ሁሉ ፈጽሞ ከእውነት የራቀና የራሳችሁ የፈጠራ
ፖለቲካ ነው። አማራ ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ አይደለም፣ ወንድሙና እህቱ እንጂ። ሁላችንም ተቃቅፈን በጋብቻ ተሳስረን በፍቅርና በሰላም የምንንሮር የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ነን። ከትወልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን ፍቅርና ወንድማማችነትን እህታማችነት አታፍርሱብን። አማራ (ኢትዮጵያ) ትግራይን በቅኝ ግዛት ስር አድርጋለች የምትሉት ከየት ያገኛችሁት እንደሆነ እኛ አናውቅም። ትግራይ ዱሮም አሁንም የኢትዮጵያ የታሪክ ማእከል ናት በማለት የትግራይ ህዝብ ከገጠር እስከ ከተማ ተቃውሞ አደረሰባቸው። በዚህም ምክንያት የገጠርና የከተማ ኗሪው በቀን እና በሌሊት እየተለቀመ በሽብርተኞች ቡድን ተገደለ፣ ቤቱ ፈረሰ፣ ህፃናት በየቦታው ወድቀው ቀሩ። ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ከፋሽስቱ ጣሊያን ጋር የተዋጉ የትግራይ ኢትዮጵያዊ አርበኞች በወያኔ ትሓህት ከየቤታቸው እየተለቀሙ ሃለዋ ወያኔ ገብተው በጥይት እየተረሸኑ መስዋእትነት
ከፈሉ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ በ1969 የተሓህት መሪዎች ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ አባይ ፀሃየ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሥዩም መስፈን፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ ተሰባስበው በትግራይ ውስጥ የሚኖረው አማራ፣ ኦሮሞና ሌላውም ከትግራይ ይውጡ፣ ትግራይ2 ለትግራይ ህዝብ ብቻ ናት የሚል አዋጅ አስተላለፉ። ይህንን ሃሳብ ያልደገፉት ግደይ ዘርአጽዮን እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ብቻ ነበሩ።
በዚህ የዘረኝነት አጥር ውስጥ የገባው የተሓህት አመራር ከ1969 መጨረሻ በፕሮግራሙ ያካተተው የትግራይ መሬት ብሎ ያስቀመጠው ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ቃፍታ ላይ ማነጣጠር ጀመረ። በተቻለ መጠንም በፍጥነት ተቆጣጥረን በትግራይ ውስጥ ገብተው በተሓህት አመረር ስር መተዳደር አለባቸው የሚል እቅድ ያዘ። ከዚህ ቀደም ብሎ በአርከበ እቁባይ የተዘጋጀ ካርታ ከበጌምድር ጠ/ግዛት ከላይ የተጠቀሱትን ቦታዎ ች፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ራያና ቆቦ፣ አላማጣ፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ ለምትመሰረተው አዲሲቷ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትግራይ ሲካተቱ፣ በምእራብ በኩል ደግሞ ወልቃይት፣ ሁመራ ፀለምት፣ ፀገዴ ተጨምረው ትግራይ ከሱዳን ጠረፍ ጋር እንደትገናኝ፣ በደቡብ በኩል ደግሞ ወደውሃ ምላሽ ትግራይ እንድትሰፋ ሲወስን፣ እነዚህቦታዎች ሁሉ ለምና ሃብታም መሬቶች ናቸው። ይህንን ውጥን ለማሳካት በወልቃይት ፀገዴ ተሓህት ህዝቡን እያፈነ ማጥቃት ጀመረ። የወያኔ/ህወሓት/ተሓህት መሰረታዊ የታሪክ ወንጀል የወላቅይት ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ ለብዙ ሺህ ዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ታሪካዊ ቦታዎች የበጌምድር (ጎንደር) ግዛት መሬት ነው። ታሪክም የሚያረጋግጠው ይህ ነው።። በምንም ተአምር ከትግራይ ግዛት ጋር ግንኙነት የለውም። የሚገናኙበት ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊነት ነው። በጌምድርም ሆነ ትግራይ የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። በሃይማኖትና በጋብቻ ተያይዘዋል። ይህ ደግሞ በሁለቱ ህዝብ ማካከል ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ውስጥም ያለ ነው። ኦሮሞው ከትግሬ፤ ትግሬው ከአማራ፣ አፋሩ ከጋምቤላው፣ ጉራጌው ከሌላው ዘር ጋር ወዘተ የተደባለቀ ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በደም የተቆራኘና አንድ ህዝብ ነው።
አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ በመጠባበቅ የቆየው የተሓህት አመራር በየካቲት መጨረሻ በ1968 በድርጅቱ የተሰባሰቡት ታጋዮች ዲማ በተባለው በአጋሜ አውራጃ ውስጥ የዲማ ኮንፈረንስ በመባል የሚታወቅ ኮንፈረንስ በማካሄድ ከ150 የማይበልጡ ታጋዮች በአረጋዊ በርሄ ሊቀመንበርነት በሚመራ ስብሰባ ፕሮግራሙ ቀርቦ እንዲጸድቅ ቢጠይቅም ታጋዩ አልተቀበለውም። ይሁንና፣ ሊቀመንበሩ ጸድቋል ብሎ የድረጅቱ የፖሊሲ አቋም ሆኖ እስከመጨረሻው ቀጥሏል። የተሓህት የሰሜን በጌምድር የወረራ ዝግጅት ተሓህት ወደ ሰሜን በጌምድር/ጎንደር በቀጥታ ሃይሉን አሰባስቦ አልገባም። ምክንያቱም፡
1. በመጀመሪያ ጊዜና ሁኔታውን ማስተከካል ፈለገ፤
2. ኢህአፓ በአካባቢው በስፋት ይንቀሳቀስ ስለነበር በአቅምና በትጥቅ ጥራት ህወሓት ዝቅተኛ ስለሆነ፣ ኢህአፓዎቹ ይመቱናል፣ ያጠቁናል የሚል ስጋት ስለአደረበት፣
3. የወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ህዝብ አይቀበለኝም ብሎ በማመኑ፣ አቅሙን እስኪያጠናክር መዘግየቱን እንደ አማራጭ ወሰደ። ቢሆንም ግን፣ ተሓህት በድብቅ በ1969 መጨረሻ ወደ ፀገዴና ፀለምት መሽሎክሎኩን ቀጠለ። በዚህ ጊዜ ደጀና ውስጥ ሽሬላ ተብላ በምትታወቀው ትንሽ ከተማ የተሓህት ታጋዮች ቅዳሜ ቀን ህዝቡን ሲያንገላቱ በነበሩበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ቡድን ሁለቱን የተሓህት ታጋዮች በገበያው መሃከል ገደሏቸው። በታህሳስ 1972 በሻእቢያና በጀብሃ፣ በወያኔና በኢህአፓ መካከል በተነሳው ጦርነት በኢህአፓ በሰነዘረውጥቃት ተበታትነው ሱዳን ገቡ። በወልቃይት ፀገዴ ፀለምት የኢህአፓን ሠራዊት በበላይነት ሲመሩት የነበሩት ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ታደሰ ቅንጥሾ ወዘተ አስቀድመው ለወያኔ ህወሓት እጃቸውን ስለሰጡ፣ እየመሩም የኢህአፓን ሠራዊት እንዲጠቃ አደረጉ። በጥቃቱም ብዙዎቹ ተገደሉ፣ ተማረኩ፤ የተማረኩትም ተረሸኑ። ለዚህ ተጠያቂቆቹ ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ናቸው። ይህ ጊዜ ወያኔ ህወሓት ፍላጎቱ የተሳካበት ወቅት ነበር። አሁን ያለው የህወሓት አመራር በ1971 የካቲት 5 ቀን የተመረጡት፤ ስብሃት ነጋ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር፤ አረጋዊ በርሄ፣ ወታደራዊ አዛዥ፤ አባይ ፀሃየ፤ ግደይ ዘርአጽዮን፤ ስዩም መስፈን፤ መለስ ዜናዊ፤ አውአሎም ወልዱ፤ አርከበ እቁባይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤ ተወልደ ወ/ማርያም፤ ገብሩ አስራት፤ ስየ አብርሃ፤ ጽድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ በወያኔ የተገደለ፤ አስፍሃ ሃጎስ፣ ታሞ የሞተ ናቸው። የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩና ሁሉን ትእዛዝ የሚሰጡት ደግሞ፣ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ፤ አረጋዊ በርሄ፤ አባይ ፀሃየ፤ ስዩም መስፍን፤ ግደይ ዘርአጽዮን ናቸው። በወልቃይት ፀገዴ ጥቃቱን ያቀነባበሩት አመራሮች፤ ስየ አብርሃ፤ አርከበ እቁባይ፤ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤
አውአሎም ወልዱ ናቸው። እነዚህ በሰሜን በጌምድር፣ ወልቃይት ፀገዴ ትእዛዝ ይጠባበቁ የነበሩ ሲሆኑ፤ ይህንን ሁሉ በበላይነት የመራው ስብሃት ነጋ ሲሆን፤ የቅርብ ተባባሪዎቹ ደግሞ አባይ ፀሃየና አርከበ እቁባይ ነበሩ። ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር የሰሜን ጎንደር ኗሪ ሰላማዊ ህዝብ ለማጥቃት የታየው ሁኔታ አመራሩ ዝግጅት ያደረገው ነበር። በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይት ፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውን
ትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡን በመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣ የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱን የህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩ በማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድ ነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴና የፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድር አማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድር ይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን
3 ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው። ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት በመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይ ግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደር ነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማው ደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩን ብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ
በርስ ግጭ ያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜ ወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝ ነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰን መሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡ ራሱ አረጋገጠ።
ሁመራን በተመለከተ ወያኔ ተሓህት/ህወሓት የትግራይ ነው ቢልም በወቅቱ እስከ ግንቦት 1983 የኢትዮጵያ ምድር ጦር ሰፊ ጥበቃ ስለነበረው፣ ወያኔ ህወሓት መሬቱን የተቆጣጠረው አዲስ አባባን በያዘበት ጊዜ ነው። ወያኔ ህወሃት በትግ ላይ በነበሩበት ጊዜ 17 ዓመታት ሙሉ ሁመራ አልገባም፣ አልተቆጣጠረም። በአካባቢውም ድርሽ አላለም። ከላይ የተጠቀስው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መኮንን ዘለለው የህዝቡን አንበገርም ባይነትና የሰሜን በጌምድር አማሮች ነን ባይነት፣ ለወራት የቆየበትን ሪፖርት ለህወሓት አመራር ለስብሃት ነጋና ሌሎችም አቀረበ። ስብሃት ነጋ በመኮንን ዘለለው ላይ ወረደበት፣ ወዲያውኑም ከሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊነት አወረደው። በዚህ ክስተት ባይታሰርም የአእምሮ በሽታ ሰለባ በማድረግ አሰቃዩት። ከዚህ በመቀጠል የተነሳንበትን ታሪካዊ ትንተና በተጨባጭ ለማረጋገጥ የቀድሞውን የሃገራችን ኢትዮጵያን ካርታ በ “ሀ” እንዲሁም ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ ከያዘ በኋላ ያዘጋጀውን ካርታ በ”ለ”፣ የበጌምድር ጠ/ግዛትን እና የትግራይን ጠ/ግዛት
የወሰን ክልል ደግሞ በ “ሐ” ና “መ” ላይ በማነጻጸር እንመልከት።
(ስእሎቹን ከታች ይመልከቱ )
“ሀ” በሚለው የኢትዮጵያ ካርታ በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታትና ህዝብ ያመኑበት፣ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካአንድነት ድርጅት ተቀባይነት ያለው የኢትዮጵያ ግዛት መልክአ ምድር ካርታ ነው። በኢትዮጵያ በቅደም ተከተል የመጡ መሪዎች እስከ ደርግ ዘመን መንግሥት ይህንኑ ተቀብለውና አምነው ኢትዮጵያና ህዝቧ አንድነቱን ጠብቆ የሃገሪቷን ዳር ድንበር በመጠበቅ
ኢትዮጵያን የመሩበት ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ካርታ ነው። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ የጠቃላይ ግዛቶች የወሰን ድንበር ሳይካልለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ በፈለገውና በመረጠው
ጠ/ግዛት ሄዶ በመንግሥት ሥራ፣ በእርሻ፣ በንግድ፣ በአንጥረኛነት፣ በሸማኔነት ወዘተ በመሥራትና የሃገሪቱን ሕገመንግሥት በመከተል ትዳር መስርቶ፣ ኢትዮጵያዊነትን ከደመ ስጋው ቀላቅሎና ኮርቶ የሚኖር ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ በልጆቿ ተከብራ ለዘመናት የቆየች ሃገር ናት። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባት ሃገርም ነበረች። ዛሬስ? የሚለውን ጥያቄ እንደሚከተለው እንመለከተዋለን። ታሪካዊው የጠ/ግዛቶች የንድንበር ክልል የኢትዮጵያ ጠ/ግዛቶች ድንበር በ “ሀ” ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ካርታን ብንመለከተው በቂ ግንዛቤ ይሰጠናል። ይህ ደግሞ ለዘመናት ጸንቶ የቆየ ነው። ለዚህም ነው ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተቆራኘው። የበጌምድር ጠ/ግዛትና የወሎ ጠ/ግዛትን ስንመለከት
የበጌምድር ጠ/ግዛትና የትግራይ ጠ/ግዛት ድንበርን ያካለለው ታሪካዊው የተከዜ ወንዝ ነው። ተከዜ ወንዝ በምእራብ በኩል በጌምድርን፣ በምስራቅ በኩል ትግራይን ለይቶ በማካለል ለብዙ ዘመናት ጸንቶ የቆየና የኢትዮጵያ ነገሥታትም ያመኑበት ድንበር ነው። ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ስለሚገኙም ሰሜን በጌምደር (ጎንደር) ተብለው ይጠራሉ። ይህ ደግሞ በተልያዩ የታሪክ መጽሐፍት የሚገኝ እውነት ነው። የኢትዮጵያ ግዛቶች በወሰን ክልላቸው የሚታወቁት ከጥንት ተያይዞ የመጣ በመሆኑ በትግራይና በጌምድር፣ በትግራይና በወሎ
እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ድረስ ያስነሳው ግጭትም ሆነ ይገባኛል የሚል ጥያቄ ተንስቶም አያውቅም፣ አይታሰብብምም። የትግራይ ህዝብ ሰሜን በጌምድር የትግራይ ነው አላለም። ይህንን ተስፋፊነት የፈጠረው የተሓህት አመራር ነው።ይህ በህ.ወ.ሓ.ት የተፈፀው ሰባአዊ መብት ረገጣም በከፍተኛ የወንጀል ተጠያዊው ወያኔ ነው።ሰሜን ጎንደር ‹፣አማራ ነው ግዛቱም የጎንደር ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክም የሚታወቀው ወልቃይት..ፀገዴ..ፀለምት..ሁመራ..ወ፣ዘ፣ተ.የጎንደር ግዛቶች መሆናቸው ነው። የድንበርን ቋንቋ በተመለከተ በዚህ ዓለም በድንበር የሚገናኙ የተለያዩ ሃገራት አንዱ የአንዱን ቋንቋ ይናገራሉ። ለምሳሌ፤ ቤልጂየምን ብንመለከት፣ ፈረንሳይና፣
ደች፣ ጀርመንኛ የሚናገሩ ሕዝቦ አሏት። ነገር ግን የቤልጂየም ዜጎች እንጂ ቋንቋውን በመናገራቸው የፈረንሳይ፣ ጀርመን ወይም የኔዘርላንድ ዜጎች አይደሉም። በኢትዮጵያ ውስጥም በድንበር የሚዋሰኑ ጠቅላይ ግዛቶች፣ አፋሩ ትግርኛና አማርኛ ይናገራል፤ ትግራይም አማርኛና ትግርኛ
ይናገራል፤ አማራውም ኦሮምኛና ትግርኛ፣ አርጎብኛ፣ ጉራጌኛ ይናገራል። በቋንቋ ድንበርን ለመወሰን ፈጽሞ አይቻልም። ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት ግን የታላቋን የትግራይ ሪፓብሊክ ለመፍጠር፣ የበጌምድር ጠ/ግዛትን እና የወሎ ጠ/ግዛትን ለም መሬቶች ትግርኛ ይናገራሉ በሚል ቁንጽል አስተሳሰብ በጉልበቱ መሬት ነጥቋል። የሰሜን በጌምድር፣ ወልቃይት፤ ፀገዴ፣ ፀለምት፣
ሁመራ፣ ባህላቸውና ቋንቋቸው አማራ ነው። ይህም ለብዙ ዘመናት እየዳበረ የመጣ ሲሆን፣ በተከዜ ወንዝ ዳር የሚኖሩ ዜጎች ትግርኛ መናገር ቢችሉም ዋናው ቋንቋቸው አማርኛ ነው። ሙሉው የዘር ሃረጋቸውም አማራ ነው። ስለሆነም እነዚህ ዜጎች የአማራ ሕብረተሰብ አካል ናቸው። ከትግራይ ሕብረተሰብ ጋር የሚያገናኛቸው ኢትዮጵያዊነታቸው ነው። በጋብቻ በመተሳሰር በሰላምና በፍቅር የኖሩ፣ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ ህዝብ ናቸው። በዚህም ምክንያት የትግራይ ህዝብም በበጌምድርና በወሎ ህወሓት የፈጸመውን ተስፋፊነት አልተቀበሉትም። በእነዚህ ሶስት ጠ/ግዛቶች፣ ማለትም በጌምድር፣ ትግራይና ወሎ የመሬት ይገባኛል የድንበር ክልል ተነስቶ አያውቅም። የሚነሳበት ምክንያትም የለም። የሕግ መሰረት እነዚህ ከበጌምድር ጠ/ግዛት በተሓህት/ህወሓት የተነጠቁት መሬቶች፣ ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ደግሞ ደቡብ ወሎ የተነጠቁት ቦታዎች ሕገወጥ ናቸው። ተስፋፊው ተሓህት በፕሮግራሙ መቅድም በሚለው አርእስት ያካተተው የትግራይ ቦታዎች ናቸው የሚለው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያው፣ ከ1969 ጀምሮ በቁርጠኝነት የተቃወመው ነው። እኛን ከህዝቡ በመነጠል ችግር እንዲፈጠር አታድርጉ፤ የምትሉት መሬት በታሪክም የትግራይ አልነበረም ባለበት ጊዜ ነበር “ትግራዋይ ሸዋዊ” የሚል ስም የሰጡት። ህዝብ ያልተቀበለው ተስፋፊነት ደግሞ አምባገነን እና ፋሽስትነት ነው። ስለሆነም በሕግ
ተቀባይነት የለውም።ተሓህት/ህወሓት በጉልበት የነጠቃቸው መሬቶች ካለምንም ውጣ ውረድ ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ይመለሳሉ። ህዝብ በጠራራ ጸሓይ መሬቱ አይነጠቅም አይፈናቀልም ።
በህዝብ ሬፈሬንደም ይወሰናሉ፣ ለምን? በካርታ “ሀ” ላይ የተመለከተውን ታሪካዊ የሚያደርገው፣ በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ተቀብለውት የጸና ሆኖ ብዙ ዘመናት ያስቆጠረ ስለሆነ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ አምኖበት የተቀበለው፣ በምንም መልኩ የድንበር ግጭትና ኹከት ያልፈጠረ፣ ዜጎች
ሁሉ አምነውበትና ኮርተውበት ኢትዮጵያውያዊነታቸውን አጠናክሮና አቅፎ የተጓዘም ስለሆነም ነው።
7አንዳንድ የተሓህት/ሀውሓት አመራርና ነባር አባላቱ የድንበሩ ጉዳይ በህዝበ ወሳኔ ይፈታ የሚሉ አሉ። ይህ በተሓህት/ህወሓት የተፈጸመው የመስፋፋት ጉዳይ ሕገወጥ ነው። የሰሜን በጌምድር መሬት፣ የደቡብ ወሎ መሬት ለድርድር ሳይቀርቡ በቀጥታ ወደ ቀድሞ ግዛታቸው ይመለሳሉ። ለህዝበ ውሳኔ ይቅረብ ማለት ፌዝና ቀልድም ጭምር ነው። ስለሆነም ህዝበ ውሳኔ ሕገወጥ ነው። ፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ፀለምት፣ ሁመራ የበጌምድር (የጎንደር) ግዛት ናቸው። በወሎም፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ፣ ራያና ቆቦ፣ አላማጣ የወሎ ጠ/ግዛት ናቸው። የወያኔ ህወሓት አመረራርና አባላቱም ጭምር ይህንን አምነው መቀበል ግዴታቸው ነው። የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጄል ተሓህት/ህወሓት ሲፈጠር ተስፋፊነትን የፖሊሲው አቋም አድርጎ የተነሳ ድረጅት ነው። 5ኛ ፕሮግራሙን እንመልከት።
ተስፋፊነት ደግሞ ፋሽስት፣ አምባገነን፣ ጨካኝ፣ ምህረት የለሽ ነው። ተፈጥሯዊው ባህሪውም ስለሆነ በዚሁ ነው የሚያድገው። ተሓህት/ህወሓት ታህሳስ 1972 በቀጥታ የዘመተው ወደ ሰሜን በጌምድር ነበር። ዘመቻው ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን የአማራ ዜጎችን ለማጥፋት የወጣ እቅድ ነው። በትግራይ ውስጥም አማራ ደመኛ ጠላትህ ነው ሲሉት፣ አማራ ለትግራይ ጠላት አይደለም፣ ወንድማችን ነው፣ በጋብቻና በዘር ደማችን የተቀላቀለ ኢትዮጵያዊ ነን በማለት በቆራጥነት አቋሙን የገለጸ ህዝብ ነው። “የትግራይ የሸዋ” በሚል ከገጠሩ ጀምሮ እሰክ ከተሞች የግድያ እልቂት የሚፈጸምበት ጊዜም ነበር። የትግራይ ህዝብ አማራ ወንድሜ፣ እህቴ፣ ልጆቹ ልጆቼ፣ ሁላችንም የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ነን በማለቱ በስንት ሺህ የሚቆጠር ህዝብ በህወሓት 06 ሓለዋ ወያነ እየገባ በጥይት ተደብድቦ ከባድ መስዋእትነት የከፈለ የአማራው አጋር ኢትዮጵያዊ ነው። ወያኔ ህወሓት ወደ ሰሜን በጌምድር ሲዘምት ዋናው አስተባባሪ ሆኖ እልቂቱ እንዲፈጸም ያስተባበረው የድርጅቱ ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ነበር። ከስብሃት ነጋ ጋር በመተባባር በተግባር የዘር እልቂት እንዲፈጽሙ የተመደቡት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ፣ አርከበ እቁባይ፣ ስዩም መስፈን፣ ዘርአይ አስገዶም፣ ስየ አብርሃ ናቸው። በእልቂቱ የታሰተፉ ተዋጊ ሃይሎች የተመሩት ደግሞ፣ በሳሞራ የኑስ፣ ተከስተ እስጢፋኖስ፣ ታደሰ ወረደ፣ መኮንን አሊሱም ሲሆኑ፤ ክርቢት ተብለው የሚታወቁት ሽብርተኛ ጋንታ የተመሩት ደግሞ፤ በሻሸይ በላይ፣ አሰፋ ማሞ፣ ጸጋይ ቆማጥ፣ መሃሪ፣ ዳሳ ጉግሳ ነበሩ። አምስተኛ ክርቢት ደግሞ
የተመራው በአርከበ እቁባይ ሲሆን፣ ስምሪታቸው በፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ፀለምት ነበር። እዚህ የሚኖረው ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ነው። እኛ በታሪክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን አማሮች ነን በማለታቸው፣ በቀንና በሌሊት እሳተ ነበልባል ወረደባቸው። በስብሃት ነጋ በሚመራው የህወሓት ሰራዊት ከያሉበት እየተለቀሙ በጥይት እየተደበደቡ አለቁ። ሃብት ንብረታቸው፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ የጋማ ከብት፣ ያፈሩት ንብረት ሁሉ በህወሓት እየተዘረፈ ወደ ትግራይ እየመጣ የሰራዊቱ ቀለብ ሆነ። ቤት ፈረሰ፣ ወላጆች፣ ህፃናትን ጨመሮ በህወሓት አለቁ። ቤተሰቦች እየተሰበሰቡ እቤት ወስጥ እየታጎሩ አርከበ እቁባይ በሚመራው ክርቢት እሳት እየተለቀቀባቸው በእሳት አጋይተው ጨረሷቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ፤ በብስራት አማረ የሚመርው ጨካኝና አረመኔ ሰራዊት፣ የቡድኑ አባላት፤ አሰፋ ጉሬዛ፣ ሃይሉ በርሄ፣ ልኡል በርሄ፣ ዘርአይ ይህደጎ፣ ካህሳይ ቆራጽ፣ ዘውዱ፣ ገብረዮሃን ለህወሓት የስለላ ሥራ ወልቃይት ፀገዴ ተሰማርተው ነበር። በፀለምት በኩል ደግሞ በዘአማኑኤል ለገሰ የሚመራና ተጠሪነቱ ለብስራት አማረ የሆነ ቡድን ተሰማርቶ ነበር። የቡድኑ አባላት፣ አደም፣
ታደሰ 06፣ ታደስ መሰረት፣ ተስፋየ አፅብሃ (አፍርሰው)፣ መሃመድ፣ ፍሬ ጎይትኦም (ሴት) ነበሩ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ ሃለዋ ወያኔ እያስገቡ መግደል ስለሚመቻቸው፣ ለወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት አመቺ የሆኑ ሃለዋ ወያኔ ተከፈቱ። እነሱም፣
1. ፍየል ውሃ ፀገዴ፣ በክንፈ ገ/መድህን የሚመራ፣
2. ባኽላ ሳሞረ፣ የፀገዴ ዳር፣ በሙሉጌታ ወዛም (ማይዶ አስክን) ዛሬ በአሜሪካ የሚኖር፣
3. ሱር ለፀለምት አቅራቢያ፣ በአበበ ተክላሃይማኖት የሚመራ (የአየር ሃይል አዛዥ ጄነራል ነበር)
የወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ህዝብ በነብስራት፣ አማራው በቀንና በሌሊት እየታፈነ በሶስቱ ሃለዋ ወያኔ እየገባ በአማራው የሰሜን
በጌምድር ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጄል ህወሓት በመፈጸም ላይ እንዳለ፣ ቦታው በመጣበቡ ምክንያት ሌላ ሃለዋ ወያነ መጀመሪያ በሃሰን ሹፋ የሚመራ ሃለዋ ወያነ የአማራው ሕይወት ተቀጠፈ፤ በጅምላ ጉድጓዶች እየገቡ በፍየል ውሃ፣ በባኸላ፣ በሱር፣ በገሃነብ፣ በህወሓት ጥይት እየተደበደበ ያለቀው ህዝብ ቤት ይቁጠረው። መሬቷና በአካባቢው ከሞት የተረፈው ምስክርነት ይሰጥበታል። ተሓህት/ህወሓት የአማራውን ህዝብ ዘር ማጥፋት የጀመረው ከ1969 መጀመሪያ ቢሆንም በክፉና
አሰቃቂ መልኩ የጀመረው በ1972 ታህሳስ ሲሆን ለረጅም አመታት ግድያው ቀጠለ።
ከዚህ የዘር ማጥፋት እልቂት ከደረሰበት የወልቃይት ፀጋዴ ፀለምት ህዝብ አሁን በእድል ከሞት ተርፎ ቤተሰቦቹ ያለቁበት ዜጋ፣ በዛን ጊዜ የህወሓት አመራር ጠላቶቼ እነማን ይሆኑ? የሚል አእምሮውን የሚረብሹ ጥያቄዎች አሉ። ስለሆነም እዚያ የነበሩ የተሓህት/ህወሓት መሪዎች እነሆ ተቀበሉ። ጊዜውም ከ1967 እሰከ 1977 ነበር።
1. ስበሃት ነጋ፣ የህወሓት ሊቀመንበር ፖሊት ቢሮ
2. አረጋዊ በርሄ፣ ወታደራዊ አዛዥ ፖሊት ቢሮ
3. ግደይ ዘርአፅዮን፣ የህወሓት ም/ሊቀመንበር ፖሊት ቢሮ፣ ፕሮግራሙን ያልጠበቀ
4. አባይ ፀሃየ፣ ፖለቲክዊ ጽ/ቤት ፖሊት ቢሮ
5. ሥዩም መስፈን፣ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ፖሊት ቢሮ
6. መለስ ዜናዊ፣ የፖለቲካ አዘጋጅ ማ/ኮ
7. አውአሎም ወበዱ፣ የሪጅን 1-2 ሃላፊ ማ/ኮ
8. አርከበ እቁባይ፣ ወታደራዊ ማ/ኮ
9. ስየ አብርሃ፣ ወታደራዊ ማ/ኮ
10. ዘርአይ አስገዶም፣ ከተማ ግንኙነት ማ/ኮ
8
11. ተወልደ ወ/ማርያም፣ የገጠር ግንኙነት ማ/ኮ በህመም ምክንያት ሱዳን የሄደ
12. ገብሩ አስራት፣ የሪጅን 3 ሃላፊ ማ/ኮ
13. አስፍሃ ሃጎስ፣ የውጭ ጉዳይ ማ/ኮ
14. አታክልት ቀፀላ፣ በአመራሩ የተገደለ ማ/ኮ፣ በ1971 የተገደለ
15. ጻድቃን ግ/ተንሳይ፣ ወታደር ማ/ኮ
ከዚህ የዘር ማጥፋት ወንጄል፣ የአማርኛ ቁንቋ የአማራው ገዢ መደብ ቋንቋ ስለሆነ አብሮ መጥፋት አለበት ተብሎም ከዘመቻው
አንዱ ሆነ። ከዚህ በተጨማሪ፣ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ስር የሰደደ እምነት አብሮ ይጠፋል ሲሉ ነበር። የህወሓት ፋሽስት ቡድን ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ
ከዚህ ቀጥዬ የማቀርበው፣ እኔ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በወቅቱ የነበርኩት አዲስ አበባ ውስጥ ነበር። እነሱ ኢትዮጵያን ወረው ሲቆጣጠሩ ደግሞ ዩጋንዳ፣ ካምፓላ ስለነበርኩ የማቀርበው ሃተታ በትግሉ ወቅት ጓዳኛዬ የነበረ፣ በ1968 በተሓህት አበርን የተሰለፍን ግለሰብ የነገረኝን ነው። ገና ከመነሻው ጀምሮ የጋንታ መሪ፣ የሃይል መሪ፣ የባታልዮን መሪ፣ የብርጌድ መሪ፣ የክፍለ ጦር መሪ፣ እየሆነ የመጣ በትግሉ ታዋቂ የነበረ ታጋይ ነበር። ኢትዮጵያን እነደተቆጣጠሩ፣ የሽግግር መንግሥት ተብሎ ሲቋቋም በጸረ- መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ተፈርጄ ህዳር 1984 ተባረርኩ ያለኝ የህወሓት ታጋይ የነበረ ነው። ይህ ግለሰብ ከህወሓት ሰራዊት ብቻውን ሳይሆን በርካቶች መባረራቸውን ነግሮኛል። አሁን የምተዳደረው በግሌ በአነስተኛ ንግድ ነውም ብሎኛል። የተገናኘነው ዩጋንዳ፣ ካምፓላ ለግል ሥራ በመጣ ጊዜ ነበር። ወሩና ዓ. ምን ጭምር እቤቴ እንደገባሁ በማስታወሻ ይዤው ነበር። ህወሓት በኔ ላይ በዙ ችግሮች እየፈጠረብኝ የነበረበት ጊዜ ስለነበር፣ እንኳን ለማነጋገር ለመቆም እንኳን አእምሮዬ ሊቀበልልኝ አልቻለም። እሱም እንደተጠራጠርኩት ስላወቀ፣ እኔን አትጠራጠረኝ፣ በኔ ላይ የፈጸሙብኝን ብነግረህ ታለቅሳልህ ሲለኝ በመጠኑም ቢሆን ተቀበልኩት። የተገናኘነው ሚያዚያ 1985 ነበር። ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ምንም ችግር ሳይገጥመን ካለ ምንም ጦርነት ከትግራይ በመኪና ተጭነን አዲስ አበባ መጥተን ነበር። ሃገሪቷ በእጃችን በወደቀችበት ጊዜበየመንገዱና በየቦታው የሃገሪቷን ሃብትና ንበረት ዘርፈናል። ደርግ ዘራፊ ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን አንዲት ብር ሳትነሳ ያገኘነው ባንክ ቤቶች፣ የመንግሥት ግምጃ ቤቶች፣ ያለውን ገንዘብ ጠራርገን ነበር የወሰድነው። አዲስ አበባ ስንገባ ሁለት ክፍለ ጦሮች ባንክና ማንኛውንም የገንዘብ ተቋሞች እንድንጠብቅ ከተመደቡት አንዱ የኔ ክ/ጦር ስለነበር፣ የህወሓት አመራር በቀንና በሌሊት ፖሊት ቢሮ አመራር የበላይ ሆነው የሚቆጣጠሩት ስብሃት ነጋና አዲስ አበባ ስንገባ ለሁለት ቀናት ለንደን የቆየው መለስ ዜናዊ ሆነው ለዘርፊያ ተሰማሩ። በዝርፊያው የተሰማሩት የፖሊት ቢሮ አባላትም፣ ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ አርከበ እቁባይ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ ስየ አብርሃ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ አባይ ፀሃየ፣ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ) በዋናነት የሃገር ሃብት፣ ገንዘብ፣ ወርቅና ልዩ ልዩ ውድ ቅርሳቅርስ ዘርፈዋል። የተዘረፈው ሃብትም መለስ ዜናዊ በሚኖርበት ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ተከመረ። እኛም ዘርፈናል በማለት የጀመረውን ጨዋታ ቀጠለ። ይህ የትግል ጓደኛዬ በአድዋ አውራጃ ቢወለድም አብዛኛው ቤተሰቦቹ ጎድንደርና አዲስ አበባ ይሚኖሩ ናቸው። የትምህርት ደረጃው ከአንደኛ ደረጃ ባይዘልም በኢትዮጵያ ላይ ጥሩ አመለካከት እንዳለው ከፊቱ ይነበባል። ከአጫወተኝ ሁሉ ትኩረት የሰጠሁት፤
1ኛ፣ የህወሓት ፖሊት ቢሮ ኢትዮጵያን እንደሚቆጣጠርና እንደሚመራ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታት በእርግጠኝነት ሲናገሩ፣ የኢትዮጵያ ምድር ጦር፣ አየር ሃይል፣ ባህር ሃይል በቀላሉ እንደማይሸነፉ ያውቁ ስለነበር፣ ሁለቱ መንግሥታት ይጨነቁ ስለነበር፣ በርካታ የጦር መሳሪያ ለህወሓት ይሰጧቸው ነበር። 2ኛ፣ የህወሓት የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ተብሎ ኢትዮጵያን ለመምራት ስለማይችል በፍጥነት ስማቸውን እንዲለውጡ ማድረግ። በዚህ መሰረትም የህወሓት ፖሊት ቢሮ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ገብሩ አስራት፣ ስየ
አብርሃ፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አርከበ እቁባይ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተክለሃይማኖት፣ አውአሎም ወልዱ፣ አረጋሽ አዳነ፣ ተወልደ ወ/ማርያም ህዳር 1982 መቀሌ ከተማ ተሰብስበው የሚፈለገው ስም ለማውጣት አራት ቀን ተዘግተው በጭንቀት ላይ
ቆዩ። በመጨረሻም ተወልደ ወ/ማርያምና አለምሰገድ ገ/አምላክ የመጨረሻ አማራጭ በለው ያቀረቡት ስም፣ “የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” (ኢህአዴግ) እንዲባል ፖሊት ቢሮ ተቀብሎ አጸደቀው። እንደ ወጥ ማጣፈጫ የሚጠቀሙበት ብአዴን በግንባሩ ውስጥ ከተቀላቀለ ኢህአዴግ አስተማማኝና ተቀባይነት ያለው ስም ይሆናል ተባለ። ውሳኔውን እንግሊዝና
አሜሪካም ተቀብለውታል። ብአዴን የተጨመረው አማራ ብሄር ሆኖ፣ “ህዝቦች” የምትለው ቃል ስትሸፍን፣ ‘አብዮት’ የምትለው ቃል ደግሞ ወያኔን ትሸፍናለች። የህወሓትን የበላይነትንም ታረጋግጣለች። በሌላ መልኩ ደግሞ፣ ህዝቦች የሚለው ቃል የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ኢትዮጵያ ሳይሆን በዘፈቀደ የተሳባሰበ ነው ለማለትና በዘርና በቋንቋ ከፋፍለው ለመግዛት
የሚጠቀሙበት፣ ለሥልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ የሚያደርጉበት ነው። 3ኛ፣ ህወሓት በሚከተለው ፖሊሲ መሰረት የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ አለ መሆኑ ሻእቢያም የኤርትራ መሬትና ወደብ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ነው፣ በማለት ስለአረጋገጡ አሰብን ወደ ኢትዮጵያ አካለለች። እንግሊዝ ሃገር ልካችሁ ካርታችሁን አዘጋጁ የሚል ሃሳብም ቀርቦላቸዋል። ፖሊት ቢሮው በሙሉ ወደ እብደት ወሰዳቸው። አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም፣ አሰብን
አናካትትም በማለት፣ በተለይም ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን፣ ብርሃን ገ/ክርስቶስ ወዘተ በጥብቅ በማውገዛቸው የተነሳ እንግሊዝና አሜሪካም ሃሳባቸውን በመቀልበስ ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ አደረጓት።
9 ይህንን ሁሉ የነገረኝ ይህ የቀድሞ ጓደኛዬ በንጹህ ልቦና ቢሆንም፤ እኔ ግን የህወሓትን እርኩስ ተግባር ስለማውቀው እስክንለያይ ድረስ መጠርጠሬ ከፍተኛ ነበር። ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ከማንም የማላገኘው እውነታ በመሆኑ ጥሩ ግንዛቤ ስጥቶኛል። ቀደም
ብዬ የማውቀው የወያኔ ህወሓት ፀረ-ሃገርና ፀረ-ህዝብ የመሆኑን እምነቴን አዳብሮልኛል። በተለይ በአማራውና በኦሮም ህዝብ ላይ የሚፈጸምውን ክፈተኛ ግፍ በጽናት አውግዞታል።
ይህንን ካልኩ በኋል ወደ ወናው ሃሳቤ ስመለስ፣ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ፣ ፋሽስቱ ህወሓት ወያኔ ከሰኔ 1983 ጀምሮ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ካርታ ሃገር የሚያፈርስ፣ ህዝብ የሚበትን፣ ደመኛ ጠለትነቱን ያረጋገጠ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በትክክል ያውቃል። ሆኖም፣ ሃሳቦቼን በገጽ 5 ስላስቀመጥኩት፣ በትኩረት እንመልከተው። በ “ለ” ላይ የተመለከተው የኢትዮጵያ ካርታ የተዘረዘሩት የህወሓት አመራር ያዘጋጀውና ሆን ተብሎ የተሰራና የተወጠነ ነው። ምክንያቱም፣
1ኛ፣ ካርታው እንደሚያመለክተው፣ የአማራውን ነገድ በታትኖ ዘሩን ለማጥፋት፣ ሰሜን በጌምድር ፀለምት፣ ፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ በቀጥታ ወደ ትግራይ ግዛት ሲካለሉ ከወሎ ደግሞ ራያና ቆቦን፣ አላማጣን፣ አፍላ ደራ፣ ወልዲያ፣ እነዚህንም ወደ ትግራይ ግዛት ተካለሉ። ህወሓት ታላቋን ትግራይ በጉልበቱ ነጥቆ ፈጠራት። ወሎ አሁንም ቀድሞ ከነበረው ግዛቷ ከግማሽ
በላይ ወደ አፋር ተካለለ። የቀድሞዋ ጠ/ግዛት ወሎ አሁን የለችም። የቀድሞዋ የበጌምድር ጠ/ግዛት አሁን የለችም። ጎጃም፣ ሸዋ የሉም። መተማና ሌሎች ወረዳዎች ወደ ቤኒሻንጉል ተካለዋል። ወያኔ ህወሓት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ አማራው ተበታትኖ መኖሪያ አልባ ሆነ። ከተወለደበት፣ ካደገበት ቀዬ ተባረረ። ከርታታና ማደሪያ የሌለው ሆኖ ለረሃብ፣ ለበሽታና ለብዙ ችግር ተዳረገ። የአማራው ህዝብ የሚኖርባት ክልል ከአንድ አውራጃ ያነሰች ሆነች።
2ኛ፣ ይህ የህወሓት የካርታ ክልል ኢትዮጵያዊነንት ፍጽሞ የሚያጠፋ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አንድ ህዝብ ሆኖ በአንድነቱና በኢትዮጵያዊነቱ እንዳልኖረ ሁሉ፣ የህወሓት አመራር ይህን እውነታ በመጻረር ሃገርን በጎሳ፣ በቋንቋ ከፋፍለውታል። የቀድሞው የወያኔ ግፈኛው ፋሽስት መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ በጻፈው “TPLF’s Strategies for Establishing its Hegemony and
Perpetuating its Rule” በሚለው ጽሁፍ የህወሓትን ዓላማ፣ ማለትም ሁሉንም የሃገሪቷን ጉዳይ በመቆጣጠር በቀጣይነት መግዛት ነው፣ በማለት አስቀምጦታል። ይሄንን ከገቡ ለማድረስ፣ ተቃዋሚ ሃይሎችን ማጥፋት፣ ነፃ ሚዲያን በማጥፋት የህወሓት ልሳናትን ማሳደግ፣ የህወሓት ደጋፊዎችን የሥራ እድል መስጠት፣ ቁልፍ የፕሮፓጋንዳ መሥሪያ ቤቶችን፣ ማለትም፣ ትምህርት
ቤቶችን፣ የሃይማኖት ተቋማትን፣ የብዙሃን መገናኛዎችን፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ሬዲዮ፣ ቲሌቪዥን ወዘተ በመቆጣጠር የህወሓት አገልጋይ ማድረግ በማለት ጽፏል። በዋናናት ያስቀመጣቸው ደግሞ፣ ሃይማኖት ከአድሃሪው ህብረተሰብ ጋር የተቆራኙ ስለሆነ ያ መቋረጥ እንዳለበት ጽፏል። መለስ ዜናዊ አድሃሪ ህብረተሰብ የሚለው፣ ሙስሊሙን፣ ክርስቲያኑን፣ ወዘተ ነው። አስከትሎም፣
አድሃሪ፣ የለውጥና የእድገት ተቃዋሚ የሚላቸው ደግሞ መላውን ኢትዮጵያዊ ሲያንቋሽሽ ነው።
3ኛ፣ ያለፈው የአማራው ትምክህተኛ አገዛዝ ኢትዮጵያዊነት ዘልቆ የተዋሃደውና ከደመ ነፍሱ ጋር የተሳሰረ ነው። ይህንን ከህዝቡ ሰነአእምሮ ነቅለን ለመጣል፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቁንቋ ማደራጀትና በዚህ ዓላማ የሚመሩ ድርጅቶችን መፈጠር ይላል። እነዚህ ከላይ የተጠቀስኳቸው የህወሓት መርሆዎች ገና ትግሉ እንደተጀመረ በኢህአፓ ላይ የፈጸመውን ወንጀል ማስታወስ
ይበቃል። ኢህአፓ በኢትዮጵያዊነቱ ያመነና የተደራጀ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ፣ ማለትም አፋን፣ አማራውን፣ ትግሬውን፣ ኦሮሞውን፣ ጉራጌውን፣ ኦጋዴኑን፣ ጋምቤላውን ወዘተ ያቀፈ፣ በዘር፣ በቋንቋ የማያማን ድርጅት ነበር፤ ለዚህም ነው በህወሓት የተደመሰሰው። በሃይማኖቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍም ህወሓት ገና በትግሉ ጊዜ እስልምና እና ክርስትናን ለማጣፋት ታጥቆ
የተነሳ እንደነበርና አሁንም በትገባር እያሳየው ያለ ጉድይ ነው። ህወሓት ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳውም ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ነው። እንደዋናው ዓላማው አድርጎ የተጠቀመበት
ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አስቀድመን አማራውን ማጥፋት ብሎ ከ1969 መጀመሪያ ጀምሮ ነበር። አማራውን ከትግራይ ውጡ በማለት የግፍ ግድያ የተፈጸመባቸው በዚህ ምክንያት ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ህወሓት የአማራን ዘር ማጥፋቱን ቀጠለበት፣ አሁንም አላቋረጠም።
የካርታው ዓላማ ህወሓት በዘር፣ በጎሳና በቋንቋ የከፋፈለው፣ የህወሓት መሪዎችን የግዛት እድሜአቸውን ለማራዘም ነው። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የመግባቢያ ቋንቋ እንዳይኖር ለማድረግ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛ የህዝብ መግባቢያ ቋንቋ በመሆኑ ይህንን በማጥፋት ኢትዮፕያዊነቱን እና አንድነቱን ለማጥፋት የሸረበው ተንኮል ነው። አዲሱን ትውልድ በጥቅማ
ጥቅም በመያዝ ሊያዘናጋ ቢሞክርም፣ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዱሮው በበለጠ አማርኛ ቋንቋን በንግግርና በሥነጽሑፍ አስፋፍቶ በኢትዮጵያ ውስጥና ውጩንም ጨምሮ ኢትዮጵያዊነቱን በማጠናከርና በማቀፍ በበለጠ እድገት እየተራመደ ነው። የወያኔ ህወሓት መሪዎች እቅድ ከሽፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ይበልጥ ኢትዮጵያዊንቱን በማጠናከር ተከፋፍለን አንገዛም በማለት
ሁሉም በሃይማኖቱ፣ ሙስሊሙ፣ ካቶሊኩ፣ ፕሮቴስታንቱ፣ ኦርቶዶክሱ አንድነት ፈጥረው የህወሓት ፋሽስቱን መሪዎች መፈናፈኛ ያሳጣቸው ጊዜ አድርገውታል። ከዚህም የተነሳ የመለስ ዜናዊ ጽሑፍ ውድቅ ሆኖ ቀረ። (ይህንን የመልስ ዜናዊን ጽሑፍ ያገኘሁት፣ Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) ድረገጽ ሲሆን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው የህወሓት ወያኔን ዓላማ ለማወቅ ያስችለዋል። አርእስቱ፣ “TPLF’s Strategies for Establishing its Hegemony and Perpetuating ኢts Rule” ነው።
10 በህወሓት አመራ የተፈጸመ የዘር ማጣፋት ወንጄል
ወደ ዘር ማጥፋት ከማቅናታችን በፊት ህወሓት ማን ነው የሚለውን በአጭሩ እንመልከት፤
1ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ከመጀመሪያ ጀምፎ ቅጥረኛ ነፈሰ ገዳይ ሆኖ የተፈጠረ፣ የባእዳንን ተልእኮ ለማስፈጸም የተደራጀ
ድርጅት ነው። ጥቁር የአፍሪካ ናዚ።
2ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ተስፋፊ ድርጅት ነው። ታላቋን የትግራይ መንግሥት ለመመስረት ከበጌምድር ጠ/ግዛትና ከወሎ ጠ/ግዛት በህገወጥ መንገድ የነጠቀውን ቦታዎች እንመልከት፣
3ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ጠባብ፣ ዘረኛ፣ ፀረ-የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ፀረ-የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነና በባእዳን የተፈጠረ ድረጅት ነው፣
4ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ሽበርተኛ ድርጅት ነው። ከ1969 ጀምሮ በጠራራ ፀሃይና በሌሊት ፈዳያን ብሎ ባሰለጥገናቸውና በብስራት አማረ በመመራት ህዝብ ፈጁ
5ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ፀረ-ዲሞክራሲ፣ ጸረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-ሕዝብ ሆኖ የተፈጠረ ድረጅት ነው። ይህ የማፊያ ድረጅት ኢትዮጵያን ለ24 ዓመታት እየገዛ ያለ ድርጅት ነው።
6ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት የሰው ሃብት ቀማኛና የሃገር ታሪካዊ ቅርሶችን፣ የሃገር ሃብትን ዘራፊ ድርጅት ነው። ከዚህም አልፎ፣ ህዝብ እያፈናቀለ ኢትዮጵያን ለባለሃብት ባእዳን ሃገሮች በመሸጥ የተሰማራ ድርጅት ነው። ይህ የባእዳን ቅጥረኛ ደርጅት ብዙ የከፋ ባህሪ ያለው ድርጅት ነው። ኢትዮጵያ ለዘመናት ብዙ ነገሥታትን ያሳለፈች፣ ዝነኛና ባለታሪክ ሃገር ናት። እንደ ወያኔ ህወሓት የመሰለ በታሪኳ አጋጥሟት አያውቅም። በ845 በዮዲት ጉዲት፣ በ15ኛው ክፍለ ዘመን
በግራኝ መሃመድ አጥፊ ወራሪ ቢገጥማትም፤ ህወሓትን የመሰለ አረመኔና ፋሽስት፣ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለማጥፋት የተሰማራ፣ ተወዳዳሪ የሌለው እኩይ ድርጅት ህወሓት ብቻ ነው።
የህወሓት የዘር ማጥፋት ዓላማና ተግባር ህወሓት በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጄልን ስራዬ ብሎ የተያያዘው ከ1969 ጀምሮ ነው። በትግራይ ሰላማዊ ዜጎችና ታጋዮችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ጎን ለጎን ማካሄዱን ቀጠለበት። ማሰቃየትና መግደል የተጀመረው በዚሁ ወቅት ነበር። ህወሓት
በአሁኑ ወቅት ከሚጠቀምባቸው የዘር ማጣፍት ወንጄሎች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት፤
1ኛ፣ በየክልሉ በወያኔ ሰራዊትና ካድሬዎች ዜጎችን በግልጽ በመትረየስና በነብስ ወከፍ ጠመንጃ መጨፍጨፍ፣
2ኛ፣ ቤት ውስጥ አሰባስቦ በሩን በመዝጋት በእሳት ማጋየት፣
3ኛ፣ አፍኖ በመሰወር፣
4ኛ፣ ብርሃን እና ነፋስ በማይገባበት የጉድጓድ እስር ቤቶች ወስጥ በማጎርና በማጨናነቅ በተላላፊ በሽታ እንዲያልቁ
ማድረግ። ዓይነ ስውር እንዲሆኑና አእምሮአቸውን በመሳት እንዲያብዱ ማድረግ፣
5ኛ፣ ኦሮሞ፣ አማራ ወዘተ በመሆኑ ብቻ ያለምንም ፍርድ ወህኒ ቤት ተሰቃይቶ እንዲሞት ማድረግ፣ ከዘመድ አዝማድ
በማራቅ በሌላ ክልል ወስዶ ማሰር፣
6ኛ፣ በዘጠኙ ክልሎች በወያኔ የተቋቋሙት እስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ታሳሪዎች ሲታመሙ ህክምና ማግኘት
ስለማይፈቀድላቸው፣ ብዙ ታሳሪዎች በዚህ ምክንያት በበሽታ እንዲያልቁ ማድረግ፣
7ኛ፣ በፈዋሽ መድሃኒት ስም ጽንስ የሚያሰውርድና የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት ዘር ማጥፋት፣
8ኛ፣ የህወሓት መሪዎች እንደትልቅ ፖሊሲ አድርገው የያዙት ድርጊት፣ ወጣት ሴቶችና ወንዶች ሃገር ጥለው እንዲሰደዱ
በማድረግ ሃገሪቱን የወደፊት ተረካቢ በማሳጣት የሥልጣን ጊዜአቸው እንዲራዘም ማድረግ፣
9ኛ፣ መሬት ነጠቃ፣ ህወሓት (ወያነ) ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ፣ በእድገትና ሰላም ስም ሕዝቡን በግዴታ
ከተወለደበትና ከሚኖርበት ቀየው እያፈናቀለ ለባእድ ሃገሮች ለምና ሰፋፊ መሬቶችን በርካሽ በሊዝ በመስጠት ኗሪውን
ህዝብ፣ ለረሃብ፣ ለችግርና ለስደት መዳረግ። ይህ ግፈኛና ፋሽስት መንግሥት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸመውና
በመፈጸም ላይ የሚገኘው ግፍ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም።
11
የኦሮሞ ህዝብ በፋሸስቱ ገዢ ህወሓት የደረሰበት ግፍና ሰቆቃ
የኦሮም ህዝብ ትልቁ የኢርዮጵያ ነገድ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ በሙሉ ልቡ የሚያምን እና የሚኮራ ዜጋ ነው። እናት ሃገሩን ኢትዮጵያን ከተለያዩ የጠላት ወራሪዎች በመከላከል ለብዙ ዘመናት ከኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በመሰለፍ ደሙን ያፈሰሰና
አጥንቱን የከሰከሰ ጀግና ህዝብ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ጠብቆ ለትውልድ ያስተለለፈ ህዝብ ነው። ልጆቹም በኢትዮጵያ በተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች ውስጥ፣ በውጭ ሃገር ከፍተኛ ትምህርት ተምረው፣ በአየር ሃይል፣ በምድር ጦር፣ በባህር
ሃይል፣ በፖሊስ ወስጥ ተሰማርተው ሃገራቸውን ያገለገሉና የወገን ኩራትና አለኝታ የሆኑ ናቸው። ለአብነት ጥቂቶቹን ብንጠቅስ፣ ጄነራል ጃገማ ኬሎ፣ ጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ጄነራል ደምሴ ቡልቶ፣ ጄነራል ዋቅጅራ ሳርዳ፣ ጄነራል ገብረክርስቶስ ቡሊ፣ ጄነራል አስራት ብሩ፣ ጄነራል ቀልቤሳ ቤካ፣ ጄነራል አበበ ገመዳ የመሳሰሉትን ማንሳት ይበቃል። የኦሮሞ ህዝብ በተለያዩ
የትመህርት መስክ ተሰማርተው በቀሰሙት እውቀትና ብቃት እናት ሃገራቸው ኢትዮጵያን ያገለገሉና በማገለጋል ላይ የሚገኙ ዜጎች ናቸው። የህወሓት መሪዎች ዛሬ የኦሮሞን ህዝብ ሽብርተኛ ብሎታል። ሽብርተኛው ግን ራሱ ህወሓት ነው። ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠር ከ1984 መጀመሪያ አንስቶ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል በርካታ ጥቃት ፈጽሞበታል።
ግድያ ፈጽሞበታል፣ ሰቆቃ በመፈጸም አፍኖ አጥፍቶታል፣ ከየሥራው አፈናቅሎታል፣ ወንድ ሴት ሳይለይ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩትን ወጣት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አባርሯል፣ በወታደርነት፣ በፖሊስ ወዘተ ተሰማርተው የሚያገለግሉትን የኦሮሞ ተወላጆች ከሥራ በማባረር ለችግር ዳርጓቸዋል፣ ከመሬቱ ተፈናቅሎ መሬቱን በእድገትና
በልማት ስም ለውጭ ባእዳን አገሮች ሸጦበታል። ኢትዮጵያዊው የኦሮሞ ህዝብ አሁንም በህወሓት እየተሰቃየና እየተገደለ ነው። ህወሓት የኦሮሞ ህዝብ በሙሉ የኦነግ ደጋፊና አፍቃሪ ነው በማለት በተለያዩ ቦታዎች በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞና የሌሎች ነገድ ሰዎች የወያኔን እስር ቤቶች አጨናንቀውታል። እንዲሁም ማንም በማያውቃቸው ድብቅ ወህኒ ቤቶች፣ ማለትም፣ ገሃንነብ
(ቃሌማ)፣ ፍየል ውሃ የመሳሰሉ፣ በወልቃይት ፀገዴ የሚገኙና ከመሬት በታች ሁለት ሜትር ጥልቀት ባላቸው እስር ቤቶች በማጎር ያሰቃያቸዋል። በአጠቃላይ እስር ቤቶች በሞላ በኦሮሞ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ተጣበዋል። በወህኒ ቤቶች ካለፍርድና
ፍትህ የሚማቅቀው የኦሮሞ ህዝብ ቁጥሩ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ እስር ቤት ያልገባውም ኦሮሞም የህወሓት እስራኛ ነው። አማራው ወያኔ ተሓህት/ህወሓት ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊውን የአማራ ህዝብ ለማጥፋት ያቀደ ነው። ይህንንም በፕሮግራሙ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል። ተሓህት/ህወሓት ለውጭ ጠላት የሚውለውን ‘ጠላት’ የሚል ቋንቋ በአማራው ኢትዮጵያዊ ላይ መጠቀሙ የሃገርና የወገን ከሃዲዎች መሆናቸውን በግልጽ ያመለክታል። ወያኔ ተሓህት/ህወሓት አማራው ጠላቴ ነው በማለት
ዘሩን ለማጥፋት የተነሳው ከ1969 ጀምሮ ሲሆን፣ አሁንም በአማራው ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት እየፈጸመበት ይገኛል።
1. ተስፋፊው ህወሓት በ1967 ይዞት ወደ ደደቢት በረሃ በወረደው ፕሮግራሙ ላይ፣ ሰሜን በጌምድርን በሙሉ፣ ወልቃይት ፀገዴን፣ ሁመራን፣ ፀለምትን ወደ ትግራይ ለማቀላቀል መሬቱ ከአማራ መጽዳት አለበት በማለት በታህሳስ 1972 ገልጾታል። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት፣ በሰሜን በጌምድር ጾታን ሳይለይ፣ ከህጻናት እስከ ሽማግሌ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። እቤት ወስጥ እየታጎሩ በእሳት ጋይተዋል። ወያኔ ህወሓት በተለያየ ዘዴ አማራ የተባለውን እያደነ የዘር ማጥፋት ድርጊት ፈጽሞበታል። ነፍሳቸውን ያተረፉት ለስደት ሲዳረጉ፣ የቀሩት ጥቂቶቹ ደግሞ ከቤት ንብርታቸው እንዳይፈናቀሉ በመፍራት የሚደርስባቸውን ስቃይ እየተቀበሉ እየኖሩ ነው።
2. ወያኔ ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠረ ‘ለ’ ተብሎ እንደተምለከው ካርታ አይነት በማዘጋጀት ሆን ብሎ አማራውን
በዘዴ ለማጥፋት ያቀደ ክልል የሚል ስምና ካርታ አዘጋጅቶ አማራውን በዚሁ አጠፋዋለሁ በማለት። ይህንንም ለማሳካት ከበጌምድር፣ ከወሎ፣ ከጎጃም ለም መሬቶችን እየመረጠ ወደ ትግራይ አካሏል። በነዚህ ለም መረቶች ላይ ሲኖር የነበረው የአማራው ህዝብ አብዛኛው ተገድሏል፤ ቀሪውም ተሰዷል። ያማራው ሕዝብ በቀጥታና ዘዴ በተላበሰ መንገድ በወያኔ ህወሓት የግፍ እልቂት ተፈጽሞበታል። አለመታደል ሆነ እንጂ አማራ እኮ የኢትዮጵያ ጋሻ መታ ነው። ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ዳር ድንበር ከወራሪ ጠላት እየተከላከል የመጣ ባለታሪክ ህዝብ
ነው። ወደ ሌላ ሃሳብ ከመግባታችን በፊት፣ ኢትዮጵያውያን በብሄር ብሄረሰቦች በመተባበር ለረጅም ዘመናት አብሮ የኖረና በዳበረ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ትስስር የቆየ ህዝብ ነው። አሁንም ወያኔ የሚፈልገውን መንገድ አንከተልም በማለት የተጠናከረ
ህብረት ፈጥሮ በሙሉ ልቦና እና ኢትዮጵያዊነት ተሰባስበው እየተራመዱ ነው። እምቢ ለወያኔ አልገዛም እምቢ ለወያኔ የእድሜ መግዣ አልሆንም አማራ ነኝ አማራነቴም የሚነጥቀኝ ሀይል የለም ።የመብት ገዴታየም በህዝባዊ አመፅ አከብራሉ የኦሮሞ ህዝብም እንደዚሁ ፡ሌላው ኢትዮጵያዊ ህዝብም እንደዚሁ ተነስተዋ ግለቱ እየጨመረ ።የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት ስርአት በዚች አመት ከርሰ መቃብሩ መግባቱ እይቀሬ ነው።ህዝብ ሀያል ነው፤ህዝብ ከተነሳ የሚመልሰው ሀይል በዚች አለም የለም።የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን የትቀጣጠለው ህዝባዊ አመፅ ሀገር አቀፍ ሆኖ ዳሩን እናድርስው ነፃነታች እናስመልስ ። ህ.ወ.ሓ.ት የመሰለ ክፉ ጠለት የለም።
ጋሜቤላ
የጋምቤላ ኢትዮጵያዊ ዜጋም ልክ በአማራውና በኦሮሞው ህዝብ ላይ የሚደርሰው ዓይነት ሰቆቃ፣ እስራት፣ ግድያ፣ አፈና በወያኔ ህወሓት እየተፈጸመበት ዘሩ እንዲጠፋ እየተደረገ ነው። በአማራው ላይ የተፈጸመው በመድሃኒት ስም በግድ ለወንዶችና ለሴቶች
የሚሰጠው የማምከኛ መድሃኒትም ለጋምምቤላ ሕዝብ እየተሰጠ ዘሩ እየጠፋ ነው። በህወሓት የሚመራው ሽብርተኛ ስርዓት በጋምቤላው አኝዋክ ህዝብ ላይ በጄነራል ጸጋዬ የሚመራው 43ኛው ክፍለ ጦር በቀን ከ425 በላይ ገበሬዎችን፣ ሴቶችን እና ህጻናትን ገድሏል፣ ቤታቸው ተቃጥሏል፣ የተረፈውም ተሰዷል።
12 ይህ ሳይበቃው፣ የህወሓት ሽበርተኛ ስርዓት የጋምቤላ ህዝብ በእርሻ ላይ ተሰማርቶ የሚኖረውን ገበሬ የሚጠቀምበትን መሬት
ለባእዳን ባለሃብቶች በመስጠት ለችግርና መከራ ዳርጓቸዋል። ዛሬ፣ የጋምቤላ ህዝብ በደረሰበት የዘር ማጥፋት ምክንያት ህልውናው የተመናመነ ሆኗል።
ኦጋዴን
ወያኔው የህወሃት ፋሽስት መሪዎች በኦጋዴን ህዝብ ላይም ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጄል ፈጽመዋል። ይህ ኢትዮጵያዊው ህዝብ የኦነግ አባል ነህ በሚል ሰንካላ ምክንያት በቀን እና በሌሊት እያደነ መጠን የሌለው ግድያ በመፈጸም ዘሩን አጥፍቷል። እቤት ውስጥ አሰባስቦ ቤቱን በመቆለፍ በህይወት እያሉ በላያቸው ላይ እሳት በመለኮስ በእሳት ጋይተው እንዲሞቱ አድርጓል። በሌላው
ዘር ላይ እንደተፈጸመው አይነትም ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉና እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል። አስገድዶ የማምከኛ መርፌና ኪኒን በመስጠት ዘሩ እንዲጠፋ አድርጓል። በየቦታው በማይታወቁና በሚታወቁ የወያኔ ህወሓት ወህኒ ቤቶች በበሽታ፣ በረሃብ ቤተሰባቸው በማያውቀበት ሁኔታ ታስሮ ዘሩ እያለቀ ነው። አፋር የአፋር ኢትዮጵያዊው ዜጋም ከላይ በተጠቀሰው ዓይነት በህወሓት የዘር ማጥፋት ደርሶባታል። ከመሬቱ ተፈናቅሎ በገዛ ሃገረ ሰደታኛና ባይተዋር ተደርጓል። ትግራይ የትግራይ ህዝብ ገና ወያኔ ሲፈጠር ይዞት የመጣውን ፕሮግራም አልቀበልም በማለት፣ አማራው ደመኛ ጠላትህ ነው ሲባል፣ አማራው ወንድሜና እህቴ፣ ደሜና ስጋዬ ነው፣ አማራው ለትግራይ ህዝብ ጠላት አይደለም፣ እናንተ የወያኔ መሪዎች የምታወሩትና ከወገናችን ለማቃረን የሸረባችሁት ዘዴ ነው እንጂ፣ ሁለቱ ህዝቦች ለብዙ ዘመን በፍቅር፣ በሰላም ተጋብቶና በደም ተቆራኝቶ የኖረ ህዝብ ነው። አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ሳይሆን ወንድምና እህት እንዲሁም ወገንና መመኪያ ነው። ትግራይ
የኢትዮጵያ አካል እንጂ ነፃ ሃገር ነበረች የምትሉትን ተረታችሁን አንቀበለውም በማለቱ ከባድ መሰዋእትነት የከፈለ፣ ወገኔን አትንኩ በማለቱ “የትግራይ ሸዋ” የተባለ ህዝብ ነው። በዚህም ምክንያት በወያኔ ተሓህት/ህወሓት ከፍተኛ ጥቃት ደርሶባታል፣ ተገድሏል፣ ንበርቱ ተወርሶ ለከፋ ችግር ተዳርጓል። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለደረሰው ለዚህ ሁሉ ጥቃት ተጠያቂዎቹ እነማን ናቸው? በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጄል በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላው፣ በኦጋዴኑ፣ በአፋሩ፣ ወዘተ ላይ ተፈጽሟል። ከተወለደበት ካደገበት መሬት ተፈናቅሏል፤ በመድሃኒት
አንዳይዋለዱና እንዳይባዙ ተደርገዋል፣ ንጹሃን ወገኖች በጅምላ ተገድለዋል፤ እንዚህ ሁሉ ከዘር ማጥፋት ድርጊት ያላነሱ ተግባሮች ናቸው። እስከ አሁን በወያኔ ህወሓት አመራር የተገደለው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከ9 ሚሊዮን በላይ እንደደረሰና ቁጥሩ በማደግ ላይ እንድሆነ ጥቆምዎች ያመለክታሉ። ከ34 ሚሊዮን በላይ ደግሞ ከመሬታቸውና ከትውልድ ቦታቸው ተፈናቅለው መኖሪያ አልባ በመሆን ለስደት፣ ለረሃብ፣ ለበሽታና ለሞት፣ ተዳርገዋል። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ነው። በእኩይ ታግባራቸው ታሪክ ሊረሳቸውና ሊፋረዳቸው የሚገባቸውን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፤መለስ ዜናዊ፣ ቢሞትም የሰራው የወንጄል ድርጊት ተጠያቂ ያደርገዋል፣ አዜብ መስፈን፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፈን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ገብሩ አስራት፣ ፃድቃን ገብረተንሳይ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ ሳሞራ የኑስ፣ ሃየሎም አርአያ፣
ብስራት አማረ፣ አርከበ እቁባይ፣ ፀጋይ በርሄ፣ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ አባዲ ዘሞ፣ አረጋሽ አዳነ፣ ተወልደ ወ/ማርያን፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ ገብረአብ ባርኖባስ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ የማነ ኪዳነ ጃማይካ፣ ብርሃን ገብረክርስቶስ፣ ሙሉጌታ አለምሰገድ፣ ቢተው በላይ፣ አባይ ወልዱ፣ በየነ ምክሩ፣ አዲስዓለም ባሌማ፣ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ ታደሰ መሰረት በዋናነት ተጠያቂዎች ናቸው። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በነዚህ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት። በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊፋረዳቸው የሚገቡ፤
- ከ1967 ጀምሮ እስከ ዛሬ ያለው የማ/ኪሚቴ አባላት በሙሉ፣
- ከላይ እስከታች ያሉት የደህንነት አባላት፣
- በማእካላዊ ወህኒ ቤት ያገለገሉና የሚያገለግሉ በሙሉ፣
- የህዝብ ግንኙነት ካድሬዎች በሙሉ፣
- በዘራቸው ምክንያት የተሾሙት የህወሓት ጄነራሎች በሙሉ።
-
የብአዴን ሥራ አስፈጻሚ የነበሩና የሆኑ፣
ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ በረከት ስምኦን፣ አየለ ጎበዜ፣ ዓለምነው መኮንን፣ ብናልፍ አንዱዓለም፣ አህመድ አብተው፣ ተፈራ ደርቤው፣ አምባቸው መኮንን፣ በተጨማሪም የማ/ኮሚቴው አባላት በሙሉ። የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩና የሆኑ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሶፍያን መሃመድ፣ በዙ ዋቅቢያካ፣ አስቴር ማሞ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሙክታር ከዲር፣ ዲሪባ ኩማ፣ አከይል አዚዝ
መሃመድ፣ ኡመር ሁሴን፣ አለማየሁ ቶምሳ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ግርማ ብሩ፣ እነዚህና ጠቅላላው የማ/ኮሚቴው።
13
የደቡብ ህዝብ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩና የሆኑ፣
ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ መኩሪያ ሃይሉ፣ ሲራጅ ፈጌሳ፣ ሽፈራው ተ/ሃይማኖት፣ አለመየሁ አሰፋ፣ ደሴ ዳልከ፣ እነዚህና ጠቅላላው የማ/ኮሚቴው።
ከላይ ከተጠቀሱት ባልተናነሰ ሁኔታ በዘር ማጥፋት መጠየቅ ያለባቸው፤ የትግራይ ክልል፣ የአማራ ክልል፣ የአፋር ክልል፣ የሶማሊ ክልል፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የሃረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአዲስ አባባ አስተዳደር፣ የድሬደዋ አስተዳደርም ተጠያቂዎች ናቸው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የቅጥረኛ ቅጥረኛ ሆነው በማገልገል፤ የህወሓት ተባባሪ በመሆን የኢትዮጵያን ሉአላዊንት አፍርሰዋል፤ በዘር ማጥፋት ድርጊት ተካፋይ ሆነዋል፣ ኢትዮጵያውያንን ከመሬታቸው በማፈናቀልና በመግደል እንዲሁም ንብረታቸውን
በመንጠቅ ከፍተኛ ግፍ ፈጽመዋል፤ ከወያኔ በመተባባር የማምከኛ መድሃኒት እየወጉ ዘር በማጥፋት ድርጊት ተሰማርተዋል፤ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን መንግሥት እንዲሸጥ በማድረግ ተባብረዋል፤ በየክልላቸው ድብቅ እስርቤቶችን በመሥራት ተቃዋሚዎችን እና ንጹሃን ዜጎችን ያለፍርድ አስረዋል፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ስብአዊ መብቱን በመንፈግ ለግፍና መከራ
ዳርገውታል። ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!! ከትግራይ የመጣውና አሁን በሥልጣን ላይ ያለው ፋሺስቱ ህወሓት ሃገራችንን ተቆጣጥሮ በቅኝ ግዛት መዳፍ ውስጥ ካደረጋት እነሆ ዛሬ 24 ዓመታት አልፈዋል። በነዚህ ዓምታት ውስጥ ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ ሃገር
ሆናለች፣ ለም መሬቷ ከሁመራ እስከ ሞያሌ ያለው የድንበር ሃገራችን ለሱዳን በምልጃ ለወያኔ ጥቅም እየተሰጠ ነው፣ ህዝብ ሊፈናቀል ነው፣ ከሃገሩ ከተወለደበት ካደገበት ተፈናቅሎ የት ሊገባ ነው? ይህ የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጋ የሚመለከት ነው፣ የኢትዮጵያ ዜጋ በሙሉ ካለአንዳች ልዩነት በአንድነት በመነሳት የሚፈለገውን የህይወት መስዋእትነት
ከፍሎ፣ ኢትዮጵያ ሃገራችንን የመሬት ወረራ እናድን። ታሪካዊ መሬት፣ ለም መሬት አሳልፈን ለሱዳን ወራሪ መንግስት በወያኔ የባንዳ ስርአት ኢትዮጵያ በሱዳን አትወረርም። በየቦታው ያሉት ለም መሬቶች ለባእዳን ሃገሮች እየተቸበቸቡ ነው፣ በዚህም ምክንያት የሃገራችን ህዝብ መሬትና ሃገር አልባ በመሆን፣ ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለበሽታና ለሞት ተዳርጓል፣ ግፉና በደሉ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ስለዚህ፣ ረሃብና በሽታ በየጊዜው እየተፈራረቁብህ እስከመቼ በባርነት ትኖራልህ? ነፃነትህ ያለችው በእጅህ ላይ ስለሆች እምቢ ለወያኔ፣ አሁንስ በቃኝ ብለህ ተነሳ፣ አሁን የተጀመረውን ህዝባዊ አመጽ በሀይልና በግለት አጠናክር። የህዝብን ቁጣ ምንም ዓይነት ሃይል ስለማይቋቋመው ሆ ብለህ በመነሳት ሃይልህን በማሳየት ሃገራችን ኢትዮጵያን ነፃ አውጣ። የወያኔ ባርነት፣ ግድያ፣ ረሃብ፤ ስደትና ተመጽዋችነት ይብቃህ። ከኢትዮጵያዊ ዜግነትህ አልባ ሆነህ የባንዳ ልጆችና ባንዳዎች አገርህን እየዘረፉ፣ የኢትዮጵያን ሉእላዊነት እያፈረሱና እየሸጡ እያየህ እስከመቸ ነው ዝምታው? አሁንስ በቃ። ፋⶥሽቱን ወያኔ የተዘረጋውን ክንዳችንን አናሳርፍበት። ድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነው
ፐርዝ፣ አውስትራሊያ
ታህሳስ 2008 (ዲሴምበር 2015)

wanted officials