Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 21, 2015

ፍ/ቤቱ የናትናኤል ያለምዘውድ ላይ የቅጣት ማሻሻየ አደረገ


መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ.ኤስ.ኤስን ለማውገዝ መስቀል አደባባይ በጠራው ሰልፍ ላይ ስብሰባ አውከሃል በሚል ተከስሶ የ3 አመት ከ3 ወር እስር ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ናትናኤል ያለምዘውድ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ባለው መሰረት የአንድ አመት እስር ቅጣት ተቀንሶ ተወስኗል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ናትናኤል ያለምዘውድ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት 3 አመት ከ3 ወር እስር ተፈርዶበት የነበር ቢሆንም በይግባኝ ክርክሩ ወቅት የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ የቅጣት አወሳሰኑ በከባድ ወንጀል ስር የሚያርፍ አድርጎ መወሰኑን በመንቀፍ ተከራክሯል፡፡
ዛሬ ታህሳስ 11/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ክረክሩን መርምሮ ወንጀሉ በመካከለኛ ደረጃ እንዲመደብ በማድረግ የቅጣት ማሻሻያ አድርጎ የ2 አመት ከ3 ወር እስራትን ፈርዷል፡፡
ናትናኤል የይግባኝ ክርክሩና እና የዛሬውን ውሳኔ ሸዋሮቢት በእስር ከሚገኝበት ሆኖ በፕላዝማ ተከታትሏል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials