Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 12, 2015

ቀንደኛ የማንችስተር ዩናይትድ የ28 አመቱ ደጋፊ እራሱን ከሶስተኛ ፎቅ ፈጠፈጠ! Man United fan sucide after the team knocked out of champions league

Manchester United Fan in Ethiopia threw himself of a Building in Addis after the Team knocked out of champions league - ቀንደኛ የማንችስተር ዩናይትድ የ28 አመቱ ደጋፊ እራሱን ከሶስተኛ ፎቅ ፈጠፈጠ! (በተሻገር ጣሰው)
ወጣቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ለቡ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ነው::
ሙሉ ስሙ ዘይኑ ሸረፋ ይባላል::...
በተለይ ለእግር ኳስ ጨዋታ ልዩ የሆነ ፍቅር አለው:: ዘይኑ ከሃገር ውስጥ ቀንደኛ የቡና ደጋፊ ነው:: ቡና እዚህ አዲስአበባ ብቻ አይደለም ከክልል ክለቦች ጋር ጨዋታ ካለው በራሱ ወጪ ክፍለ ሃገር በመሄድ የኢትዮጵያን ቡና ይደግፋል::

ከባህር ማዶ ደግሞ የእንግሊዙ ክለብ የሆነውን የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ ነው::ክለቡን ለ10 አመታት ያህል ደግፏል የሚለብሰው ቲሸርት በየቀኑ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾችን መለያ እየቀያየረ ነው::
ይህ ማለት ለ28 አመቱ ወጣት ዘይኑ የማንችስተር ዩናይትድ ክለብ በደሙ ውስጥ ሰርፆ ገብቷል ማለት ነው:: ከትላንት በስቲያ ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልፍስበርግ ባደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ከጨዋታው በፊት 10 ሺህ ብር ማንችስተር ዩናይትድ ያሸንፋል በሚል ከአንድ ግለሰብ ጋር ያስይዛል::
በጨዋታው ዎልፍስበርግ ማንችስተር ዩናይትድን በሜዳው 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ውጪ እንዲሆን አደረገው::በዚህን ጊዜ የማንችስተር ዩናይትድ ቀንደኛ ደጋፊ የሆነው ዘይኑ ሸረፋ ተበሳጨ የጎደኞቹም ተረባ ሊያስቀምጠው አልቻለም ትላንት ምሽት ለቡ አካባቢ ከሚኖርበት 3ኛ ፎቅ ላይ ወደ ታች ቁልቁል ተመለከተና እራሱን ፈጠፈጠ::
በሃኪሞች እርዳታም ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል::ዘይኑም በጭንቅላቱና በእግሩ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የጥቁር አንበሳ የህክምና ባለሙያዎች ገልፀውልናል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials