Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 17, 2015

‪በጎንደር‬ ከተማ የልደታ ቤተ ክርስቲያን ዕቃ ግምጃ ቤት ህወሓት/ብአዴን በአስነሳው እሳት ወደመ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
‪#‎በጎንደር‬ ከተማ የልደታ ቤተ ክርስቲያን ዕቃ ግምጃ ቤት ሌሊቱን ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቶ ወደመ፤ በቃጠሎው የህወሓት/ብአዴን እጅ እንዳለበት ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ናቸው፡
====================================================
የጎንደር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የብአዴን ሹሞች በጠነሰሱት ስውር ሴራ በልደታ ቤተ ክርስቲያን የመሬት ይዞታ ላይ በ2001 ዓ.ም በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል የርስበርስ ግጭት እንዲፈጠር የሞከሩ ሲሆን አሁን ደግሞ አገዛዙ ከያቅጣጫው በችግር ስለተወጠረ በሁለቱም አስተዋይና በሳል የኃይማኖት አባቶች የተፈታውን ግጭት በመቆስቆስ እንደገና ለማገርሸት በማለም የዕቃ ግምጃ ቤቱን ሳያቃጥለው እንዳልቀረ የብዙዎች ግምትና ዕምነት ነው፡፡ በአዲስ አበባው አንዋር መስጊድ ለፈነዳው ቦምብም ህዝበ ሙሲሊሙም ሆነ ህዝበ ክርስቲያኑ ጣቱን ወደ ህወሓት እየቀሰረ ነው፡፡
አብዛኛው የጎንደር ህዝብ በግዙፉ የባህታ ወህኒ የደረሰውን የእሳት አደጋ አገዛዙ ሆነ ብሎ እንዳስነሳው ያምናል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials