Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 1, 2015

በሳዑዲ የተደፈረች ሴት 200 ጅራፍ ተፈረደባት

በሳዑዲ የተደፈረች ሴት 200 ጅራፍ ተፈረደባት 
-------
የሳዑዲ ፍርድ ቤት በሰባት ወንዶች አስገድዶ የመደፈር ወንጀል በተፈፀመባትና ይህንኑ ለሚዲያ በተናገረች ሴት 200 የጅራፍ ግርፋትና የ6 ወራት እስራት በያዝነው ወር ወስኖባታል።
ዘ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ከሆነ የ19 ዓመትዋ ሻዒት የተማሪ ቤት ወዳጅዋ በሆነ ወጣት መኪና ውስጥ ነበረች ።ሁለት ሰዎች እርስዋ ወደ ነበረችበት መኪና ከገቡ በኋላ ቀደም ብለው ወዳዘጋጁት ቦታ በመውሰድ ለሰባት ደፍረዋታል ።
ዘመድዋ ባልሆነ ሰው መኪና ውስጥ በመጒዋዝዋ 90 ጅራፍ በመጀመሪያ ተፈርዶባታል።በሳዑዲ ህግ መሰረት አንዲት ሴት ከባልዋ ወይም ከቤተሰብ አባልዋ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር በአደባባይ እንድትታይ አይፈቀድም ።
ፕሬስ ቴቪ ደፋሪዎችዋ በአምስት አመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን በአግራሞት ዘግቧል ።የሞት ቅጣት ሊተላለፍባቸው እንደሚችል ሲታሰብ እስካሁን ድረስም ሰዎቹ እንዲህ አይነት ቀላል ቅጣት እንዴት እንደተበየነላቸው ግልጽ አይደለም ።
የተደፋሪዋ ጠበቃ አብዱል ራህማን ለሳዑዲ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ባቀረቡበት ወቅትም ዳኛው የተጣለባትን የ90 ጅራፍ ቅጣት ወደ 200 ከፍ አድርገውታል ።
ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ያሳደገው ተደፋሪዋ የተፈፀመባትን ለሚዲያዎች በመናገርዋ ነው ።የጠበቃዋ ፈቃድ ታግዶም ጉዳዩ ለዲስፒሊን ኮሚቴ ተመርቶበታል።
ከውሳኔው በኋላ የፍርድ ቤቱ ኃላፊዎች በፍርድ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው ማንም ሰው ወደ ሚዲያዎች ሳይሄድ ይግባኝ ማለት ይችላል ብለዋል ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials