ግልፅ ደብዳቤ ለፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር
ለጤናዎ እንዴት ሰንብተውልኛል ጌታየ። አጋነነች ካልተባልኩ ከፈጣሪ ውጭ ለፍጡር ከምሰጠው ክብር በዚህ ወቅት የርሰዎ ግንባር ቀደሙ ነው። ለእናት ሀገረዎ ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅነተዎን አስመስክረዋልና ክብርም ፍቅርም ለርሰዎ እጅግ አድርጎ ይገባዎታል። እኔም እርሰዎ በርሀ መግባተዎን ተከትሎ አገር ቤት በተተከለው የግንቦት ሰባት ህዋስ ውስጥ በህቡ ታቅፊ የተቻለኝን ሁሉ በማድረግ ላይ እገኛለው። የመንግስቱን ጉዋዳ ጎድጒዋዳ በስራ አጋጣሚ አውቄው ስለነበር ለግንቦት ሰባት ለማከናውናቸው ተግባራት እጅግ ጠቅሞኛል ብየ አስባለው።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ሆይ በትናትናው እለት አገር ቤት ለምንገኘው የድርጅቱ አባላት ባለ ስድስት ነጥብ የትግል አተገባበር መመሪያ በይፋ አስተላልፈውልናል። መመሪያውን ተቀብለን ለተግባራዊነቱ እንደምንነሳ ስገልፅለዎ ከትንሽ ማሳሰቢያ ጋር ነው። ይህውም በአሁኑ ሰአት ጠቅላላ በመላ አገሪቱ የተፈጠረው ብሄራዊ አመፅና አለመረጋጋት የግንቦት ሰባት ጦር ሰብሮ እንዲገባ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮአል። ህዝቡ በጉጉት የሚጠብቀው የርሰዎን ጦር ሰብሮ መግባትን እና መግባትን ብቻ ነው። የመጀመሪያውን የጠላት ምሽግ ሰብሮ ማለፍ ከተቻለ ከዛ በዃላ ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሀያአራት ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚአጠናቅቀው ስገልፅለዎ በልበ ሙሉነት ነው። የወያኔ ጦር እርስ በእርሱ ተበላልቶ እንደሚአልቅ ለርሰዎ መገለፁ ለቀባሪ ማርዳት ነው። የእርሰዎ ጦር ጥቃት ከሰነዘረ ወታደሩ ተኩሶ ለመግደል ሳይሆን ሸሽቶ ሂወቱን እንዴት ማትረፍ እንዳለበት ወስኖ የተቀመጠ በቁሙ የሞተ ጦር ሰራዊት ነው። ጭራሽ አሁን አሁንማ ሰውየውም ዘገዩብን እያለ እርሰዎን በሾርኒ ማማት ጀምሮአል። ቶሎ ደርሰው ነፃ እንዲያወጡት ካለው ምኞት የተነሳ።
እናም ጌታየ ዛሬ ነገ ሳይሉ የህዝባችን ስሜት እንደተነሳሳ በቶሎ ይምጡልን። አገር ቤት ያለው ስራ ከበቂው በላይ እንደተጠናቀቀ አሳምረው ያውቁታል ብየ እገምታለው።
እህተዎ ሰርካለም ጌታሁን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
No comments:
Post a Comment