Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, December 2, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ዛሬ ዋልድባ ላይ ተዋጋ * 29 ወታደሮችን ገደለ








መነሻውን ኤርትራ ያደረገው አርበኞች ግንቦት 7 ከቀናት በፊት በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አካባቢ በሚገኙ ከተሞች በምሽት ቀስቃሽ ወረቀቶችን ሲበትን መክረሙን ከገለጸ በኋላ ዛሬ በለቀቀው መረጃ ዋልድባ ላይ ከመንግስት ኃይሎች ጋር መዋጋቱን ገለጸ::

ዘ-ሐበሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ያገኘችው መረጃ እንደሚጠቁመው ሰራዊቱ ዛሬ ዲሴምበር 1, 2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ከመንግስት መከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ጦር ጋር ተዋግቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ነው:: ከመንግስት በኩል ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ስለመዋጋቱ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተሰጠ መግለጫ የለም::

የአርበኞች ግንቦት 7 በራድዮው በኩል እንዳሰራጨው መረጃ በድንገት በከፈትኩት ጥቃት ዋልድባ ላይ ለሰዓታት ያህል ሰራዊቴ ሲዋጋ ውሎ በትሹ 29 ወታደሮችን ገድያለው እንዲሁም ከ40 በላይ ደግሞ አቁስያለሁ ብሏል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials