Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 22, 2015

ቀበሌ በስብሳባ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ነዉ የተባሉ ግለሰቦች ህወሃት አድራሻቸዉን አጠፋዉ

ዜና ከጎንደር - የሚሊዮኖች ድምጽ
በታች አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ቀበሌ በስብሳባ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ነዉ የተባሉ ግለሰቦች ህወሃት አድራሻቸዉን አጠፋዉ።
የቀበሌዎን ህዝብ አቶ አዲሱ ለገሰ እና አቶ አለምነዉ መኮነን ለማነጋር ከሰበሰቡ በሃላ በፀረ ሰላም ሃይሎች ጥቃት ሊፈፀም ነዉ በማለት ስብሰባዉ ተቆርጧል። የስብሰባዉን መቋረጥ
ተከትሎ ህወሃት በርካታ አርሶ አደሮችን ወዴት እንደወሰዳቸዉ አልታወቀም። የወያኔ ቡድን መገናኛ ብዙሃን ሰላም ነዉ እያሉ ቢለፉፉም አሁንም ድረስ አካባቢዉ ሙሉ በሙሉ የጦር ቀጠና እንደሆነ ነዉ።
በተያያዘ ዜና ወያኔ፣ በአማራው ክልል መስተዳደር ጣልቃ በመግባት፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከሃላፊነት በማንሳት የአማራው ክልል ህዝብን "ልፋጭ" ብለው የሰደቡትን. በሕዝብ የሚጠሉትን፣ አቶ አለምነህ መኮንን ለማስቀመጥ እየዶለቱ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
አቶ ገዱ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ጠመንጃ አካባቢያቸውን ይጠብቁ ዘንድ ለገበሪዎች ማደላቸው በህወሃት አልተወደደላቸውም። ከትግራይ ክልል መሪ ጋር ብዙ ጊዜ እንደተጋጩ የሚነገርላቸው አቶ ገዱ በወያኒዎች ጥርስ ዉስጥ መግባታቸው ቢታወቅም፣ ታች ባለው እና ከጊዜ ወደጊዜ በሕወሃት ላይ ተቃዉሞ በሚያሰማው የብአዴን አባል ድጋፍ አላቸው።
ብአዴን በባህር ዳር ባደረገው ጉባኤ አባልቱ ከፍተኛ ተቃዉሞ በህወሃት ላይ ሲአይሰሙ እንደነበረ ይታወሳል። "እነርሱ ባለ ፎቅ እኛ ግን ሎተሪ ሻጮች ነው የሆነው" ሲሉ የነበሩት የብአዴን አባላት ሕወሃት በሚወስዳቸው አገር ጎጂ ፖሊሲዎች ከሕዝብ ጋር እነርሱ መጣላት እንደሌለባቸው ሲናገሩም ነበር።


No comments:

Post a Comment

wanted officials