Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 8, 2015

የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በመላው ሃገሪቷ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። አንድ ወጣት ተማሪ ተገሏል

በየምዕራብ ሀረርጌ ጭሮ ከተማ የጸረ ወያኔ ትግል ወጣቶች አደባባይ በመውጣት በወያኔ ላይ ያላቸውን ቁጣ በማሰማት ላይ ናቸው!!
የቡራዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፌደራል ፖሊሶች የተከበቡ ሲሆን ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ::በሃሮማያ ዩንቨርስቲ በር ላይ አንድ ወጣት ተማሪ ተገሏል::የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአከባቢው በዳሞታ ባቴ ፊንቂልጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል::ይህን ተከቶ ከሆርሶ ወታደራዊ ካምፕ በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ካምቢዮኖች ወደ ሃሮማያ ከተማ ገብተዋል::በምእራብ ሸዋ ጮቤ ከተማ ተቃውሞ ተነስቷል::
ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ ታሪክ ሆኗል ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል። ዛሬ በመላው ኦሮሚያ ክልል ቀይ ሽብር በመፋፋም ላይ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች በሰላማዊ ሰልፍ በመሳተፋቸው ብቻ በአደባባይና በጠራራ ፀሀይ የጥይት እራት እየሆኑ ነው። የኦሮሞ ገበሬዎችን በልማት ስም ማፈናቀል አሁኑኑ ይቁም! የሚለው መፈክራችን አሁንም ደጋግሞ እየተሰማ ነው።
ዱግዳ ዳዋ አውራጃ በጅማ፣ አምቦ፣ ቡሌ ሆራና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞዎች ሲያደረጉ፣ በብዙ ከተሞች ነዋሪዎችም ሰልፈኞችን ተቀላቅለዋል። በዛሬው እለት አንድ የ 9ኛ ክፍል ተማሪ በ ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፊትለፊት የተገደለ ሲሆን፤ መንግሥት በሁሉም አካባቢዎች መደበኛ የመከላከያ ሰራዊት በማሰማራት ላይ ነው። በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቋሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ስሙ ሰመራ ግቢ ተብሎ በሚጠራው ግቢ ክፍተኛ ብጥብጥ ተነሰቷ ልዩ ሀይሎች በጥብጡን ለማብረድ በግቢው አካባቢ ከበዋል ተማሪዎች በአሁኑ ስዓት ዲንጋይ መወርወር ጀምረዋል 
ተቃውሞውን የመንግስት ሰራተኞችም እየተቀላቀሉት ነው። የእንጭኒ ሆስፒታል ሰራተኞች በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያና ድብደባ በማውገዝ እንዲሁም ማስተር ፕላኑን እንደሚቃወሙ ዛሬ ጠዋት በዚህ መልኩ እንደገለፀ ለማወቅ ተችሎዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials