ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡
ፓርቲው ‹‹ሕዝባዊ መንግስት መመስረትና የሐገር ሉዓላዊነት መጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ነው›› በሚል ዛሬ ታህሳስ 20/2008 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አበበ አካሉ ናቸው፡፡
ሰማያዊ በመግለጫው፣ ‹‹በሀገራችን የደረሰው ግፍና በደል የማስቆምና ህዝባዊ መንግስት የማቋቋም፣ የሀገርን ብሄራዊ ክብር የማስጠበቅ ኃላፊነት የጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው›› ብሏል፡፡ በመሆኑም ‹‹…ሁሉም ዜጎች አርዓያቸው የሆኑትን የቁርጥ ቀን ልጆች የመስዋዕትነት ጥሪ በመቀበል ቆርጠው እንዲነሱና የድርሻቸውን እንዲወጡ…›› ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ፋና ወጊና የነቁ ዜጎች የእሳት ራት እየሆኑ ነው ያለው ሰማያዊ፣ ‹‹አርዓያዎቻችንን እያስበላን ዝም ማለታችን አገዛዙ እድሜውን ለማራዘም›› ተጠቅሞበታል ሲል ገልጾዋል፡፡ መንግስት ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲ አባላትንና አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችንና ንቁ ዜጎችን በጅምላ እያሰረ መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውሷል፡፡
በሌላ በኩል የሐገር ድንበርንና ሉዓላዊነትን የሚጠብቁ ዜጎችን መንግስት ‹‹ሽፍቶች›› ሲል መጥራቱ ታሪካዊ የክህደት ምስክርነት በገዛ ዜጋ ላይ መስጠት ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው አውግዟል፡፡
(ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዞ ቀርቧል)

No comments:
Post a Comment